>

ኢትዮጵያ የምትዋጋው ስለአፍሪካም ሉዓላዊነትና ነፃነት ጭምር ነው !!!  [መስፍን ማሞ ተሰማ ]

ኢትዮጵያ የምትዋጋው ስለአፍሪካም ሉዓላዊነትና ነፃነት ጭምር ነው !!!

[መስፍን ማሞ ተሰማ ]

የሃያአንደኛውን ክፍለ ዘመን የኒዮ ኮሎኒያሊስቶችን ጥምር ዘመቻ እነሆ ኢትዮጵያ ብቻዋን ለመመከት፣ መክቶም ታሪካዊውን የአስራ ዘጠነኛውን ክፍለ ዘመን የአድዋ ድል በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለመድገም መሪዋ አብይ አህመድ የቀደምት ነገሥታት መሪዎቹን አርማ አንስቶ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ጦር ግንባር እንገናኝ” ብሎት ዘምቷል !!! ይህ ጦርነት በዓለም የኢኮኖሚና የፖለቲካ አውድ ጡንቻቸው ከፈረጠመው ግንባር ቀደም አድመኞች – አሜሪካ፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ – ጋር የሚካሄድ ለኒዮ ኮሎኒያሊስቶች ያለመንበርከክ የነፃነትና የሉዐላዊነት ጦርነት ነው!!! በዚህ ዘመን አፍሪካ በእንግሊዝ የCommon Wealth Countries ማዕቀፍ ሥር፣ ፈረንሳይ ደግሞ በፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛቶች ህብረት ሥር፣ አሜሪካ በበኩሏ  አሻንጉሊት መንግሥታትን በዲሞክራሲ ስም በመፈንቅለ መንግሥትና በአመፅ በማስቀመጥ አፍሪካን በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ቁጥጥር ስር ከኬኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ አውለዋል – ከኢትዮጵያ በቀር!!!
ከትግራይ ምድር የበቀለው ናዚስት ህወሃትን አዲስ አበባ ላይ ተክለው ለሃያ ሰባት ዓመት ሲንከባከቡትና ኢትዮጵያን በእጅ አዙር መንግሥታቸው ወያኔ ኢህአዴግ ሲያሽከረክሩዋት ኖረዋል። ዛሬ የኒህ የክፍለ ዘመኑ ኒዮ ኮሎኒያሊስቶች የትሮይ ፈረስ ሆኖ ናዚስት ትህነግ ኢትዮጵያ ላይ ያዘመተውን የሲዖል ሠራዊት ከምኒልክ ቤተ መንግሥት መልሶ ለማስገባት ከፍተኛ መረባረብ ላይ የሚገኙበት የተለየ ምሥጢር የለውም። ከእንግዲህ ኢትዮጵያ የኒዮ ኮሎኒያሊስቶች አሻንጉሊት መንግሥት የፀረ ኮሎኒያሊዝም ቀንዲል መሪ በሆነው የምኒልክ ቤተመንግሥት ውስጥ አይኖርም ብላ አሻፈረኝ በማለቷ ነው ምዕራባውያንና አሜሪካ የከበቧትና በመናጆ ፈረሳቸው ትህነግ አጋፋሪነት አሰቃቂ ጦርነት የከፈቱባት። ናዚስት ህወሃት የሲዖል ሠራዊቱን አሰልፎ ዘግናኝ ግፍና ጥፋት የሚፈፅመውም በእኒህ የአፍሪካ የዘመኑ የእጅ አዙር ቅኝ ገዢዎች እየተጋለበ ነው።  ለዚህም ነው ኢትዮጵያ በዚህ ጦርነት ስለ ራስዋ ሉዓላዊነትና ነፃነት ብቻ ሳይሆን ስለ አፍሪካም እምቢ ባይነትና ነፃነት ስትል ከአሜሪካ እንግሊዝ ፈረንሳይና ተለጣፊዎቻቸው ግብፅና ሰሜን ሱዳን ጋር የእጅ አዙር ጦርነት የገጠመችው።
የኢትዮጵያ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ጦር ግንባር መውረዱና የፍፃሜውን ጦርነት ነጋሪት መጎሰሙ የአድዋን መሪ ተምሳሌነት የአርበኞችን የድል ተጋድሎ አርአያነት አስቀድሞ ነውና ኒዮ ኮሎኒያሊስቶችና ፈረሳቸው ናዚስት ወያኔ ያለ ጥርጥር ድል ይሆናሉ። ህወሃት ያለ ጥርጥር ከሲዖል ሠራዊቱ ጋር ወደ ሲዖል ይወርዳል። በኢትዮጵያ ምድርም የኒዮ ኮሎኒያሊስቶች ቅምጥ መንግሥት ከእንግዲህ ምኒልክ ቤተ መንግሥት አይገባም። አፍሪካም የኢትዮጵያን ቀንዲል ከፍ አድርጋ ኒዮ ኮሎኒያሊስቶችን #nomore ትላለች!!!  የፍፃሜው ጦርነት አዝማች ጠ/ሚር አብይ በድል ወደ አዲስ አበባችን ይመለሳል!!! ድል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት!!! ድል ለልዩ ኃይላት፣ ለሚሊሺያ፣ ለፋኖና ለኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት!!! ኢትዮጵያ በልጆችዋ ከፍ ትላለች!!!
Filed in: Amharic