>

ዶ/ር ደረጀን ለመሳደብ  የተከፈተ አንደበት አማራ  እንደ ከብት ሲታረድ ከቀዬው ሲነቀል የት ነበር??? (ሸንቁጥ አየለ)

ዶ/ር ደረጀን ለመሳደብ  የተከፈተ አንደበት አማራ  እንደ ከብት ሲታረድ ከቀዬው ሲነቀል የት ነበር???
ሸንቁጥ አየለ

“አፈር ገፊ የአማራ ገበሬዎች፣  ለምን ይገደላሉ ይሳደዳሉ በማለቱ ነው ዶ/ር ደረጀ ላይ ያልተገራ አንደበታቸውን እየከፈቱባቸው..!!!”
አቻምየለህ ታምሩ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ነኝ። እውነተኛ የሃይማኖት አባት የሆነ አንድ ሰው ጥራ ብባል ግን የምጠራው ከግፈኞች ጋር ሳይሆን ከግፉዓ ጎን ሲቆሙ የማውቃቸውን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑትን ዶክተር ደረጀ ከበደን ነው። ዶክተር ደረጀ ከበደ የአገዛዙ ውታፍ ነቃዮች ከሰሞኑ ያልተገራ አንደበታቸውን እየከፈቱባቸው ያሉት አፈር ገፊው የአማራ ገበሬ፣ የአማራ ሕጻናትና የአማራ እናቶች በተለይም በወለጋና በመተከል በማንነታቸው ተለይተው በናዚ ኦነግ አረመኔዎች በየቀኑ በጅምላ ሲፈጁ ዝም ብለው ባለማየታቸው ነው።
በዶክተር ደረጀ ከበደ ላይ ያልታረመ አፋቸው የሚከፍቱት የአገዛዙ ውታፍ ነቃዮች በጅምላ ለሚፈጀው አማራ ድምጽ ቢሆኑ ኖሮ ዶክተር ደረጀ ከበደን ያገኟቸው የነበረው “ወደ ነበርህበት አገልግሎት ተመለስ” በሚሏቸው ቦታ ነበር። በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ አረመኔ ነፍሰ ገዳዮች በየቀኑ በጅምላ እየተፈጀና የተረፈው ሜዳ ላይ ተጥሎ የሚገኘውን የአማራ ሕዝብ የጅምላ እልቂትና ፍዳ አዲስ አበባ ውስጥ በሞቀ ቤታቸው እየኖሩ በቴሌቭዥን መስኮት በሩቁ መመልከትን የመረጡ እንደ ሶፍያ ሽባባው አይነት ምን እየሆነና ምን እንደተደረገ እንዳለ እውቀቱ ቀርቶ ግንዛቤው የሌላቸው የአገዛዙ ውታፍ ነቃዮች የሚጣላ ኅሊና ባላቸው በዶክተር ደረጀ ከበደ ላይ አላዋቂ አፋቸውን የመክፈት የሞራል ልዕልና የላቸውም። ቀድሞውንም የአማራ ቀንደኛ ጠላቱ እንደ ሶፍያ ሽባባው አይነቱ ሆዳም አማራ መሆኑን እናውቃለን!
 ዶ/ር ደረጀን ለመሳደብ  የተከፈተ አንደበት አማራ  እንደ ከብት ሲታረድ ከቀዬው ሲነቀል የት ነበር???
ሸንቁጥ አየለ
ዶ/ር ደረጀን የመሳደብ ሞራል ለመሆኑ ከየት ነው ያመጣችው? እረ በታዋቂነትና በአዋቂነት መካከል ያለውን ትልቅ ልዩነት እንዳለ ቢያንስ እንወቅ? ዶ/ር ደረጀ እኮ በኢትዮጵያ ውስጥ የፕሮቴስታንት እንቅስቅሴ ውስጥ አምድ ከሚባሉት ጥቂት ሰዎች አንዱ ነው።
 መዝሙሮች አውጥቶ ከዛ የተገኘውን ገንዘብ አንድ ቀን ወደኪሱ ከቶ የማያውቅ ሰው ነው። ሆዱ አምላኩ፣ ምቾት ብርቁ፣ ገንዘብ ሀቁ ያልሆነ የእውነት ሰው። ዶ/ር ደረጀ ከበደ በእምነት የማይመስሉት ሰዎች ዘንድ እንኳን የከበረን ሰው አንቺ ልታዋርጂው ስትነሺ ማየት መቼም የዘንድሮው እብደት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ጥሩ ማሳያ ነው።
የአማራ ህፃናት እንደ ከብት ሲታረዱና ጥሬ ስጋ አማረኝ እስቲ አማራ አድኜ ልምጣ ተብሎ በሚወጣበት ዘመነ አብይ እኛ ብልፅግና ላይ ነን ከፍታ ላይ ነን ሰቆቃ አያወራቹ አትበጥብጡን ስትል የኖረችው ሶፊያ ሽባባው ዛሬ እያለቀሰች ብልፅግናችንን የምትረብሸን፣ ከከፍታ የምታወርደን ለምንድነው? ብላለች።
አዝማሪው ሁሉ የኪነ ጥበብ ሰው ስትባሉ ጠቢባን የሆናችሁ መሰላችሁ ይሆን?
ለባለ ስልጣን ተገዙ ማለትና ባለስልጣን ሲያጠፋ አሜን ብላችሁ ተቀበሉ ማለት ለየቅል ነው።
መጥምቁ ዮሐንስ <<የወንድምህን ሚስት መውሰድ አይገባህም>> ያለው ባለ ስልጣንን እና የሀገር ገዢን እንደሆነ አንዘንጋ።
ነብዮ ሳሙኤል ንጉስ ሳኦልን<<የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሀልና ንጉስ እንዳትሆን ንቆሀል ያለው>> ባለስልጣኑን ነው።
ነብዮ ናታንም የኦሪዮን ሚስት ነጥቆ ያነወረውን ንጉስ ዳዊትን በሀይለ ቃል የገሰፀው መፅሐፍ ቅዱሳዊ ሀቅ ነው።
 የምትደግፊውን መደገፍ መብትሽ እንደሆነ ሁሉ ሌላውም የሚቃወመውን መቃወም መብቱ እንደሆነ ማወቅ እንዴት ተሳነሽ።
 ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ብለሽ ለዶ/ር ደረጀ ከመስበክሽ በፊት አማራው እንደዛ ሲሰቃይ፣ ሲታረድ፣ አስክሬኑ ሲቃጠል፣ በመንገድ ላይ ሲጎተት ብልፅግና ላይ ነን እያልሽ በህዝብ ሰቆቃ ስታላግጪ እንዳልኖርሽ አሁን የጨነቀ እለት ሆነና አንቺም እንባ ለመራጨት በቃሽ።
ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማነው? ለሚለው መልስ የመልካሙ ሳምራዊን ታሪክ እስሬ የምትጠሪው መፅሐፍ ቅዱስ ላይ መልሰሽ አንብቢው።
በዘር በጎሳ ወይም በሌላ አይነት ቅርበት ወይም ርቀት ሳይሆን በክፋ ጊዜ በመራራት፣ እርዳታ በሚያሻ ጊዜ በመድረስ ለእስራኤላዊው ባእድ የሆነው ሳምራዊ ከካህኑና ከሌዋዊው በልጦ ባልንጀራ እንደተባለ ትረጂ ነበር።
ዳሩ ምን ያደርጋል መፅሐፋ የሚናገረውን ትተሽ መፅሐፋን እንደፍቃድሽ ማናገር ከጀመርሽ ሰንበትበት ብለሻል።
ለዛም ነው ዶ/ር ደረጀ ከበደ ላይ አፍሽን ስታላቅቂ ምላስሽ ያልተደናቀፈው።
እዛ ቤት የሚነድ እሳት አንቺው ቤት፣ ያንቺው ጥቅም ላይ መጣ።
የናንተ ግብዝነት በእግዚአብሔር እና በሰይጣን መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠፋ ነው።
 አንቺ የምትጠሪው የግብዞች እግዚአብሔር እኔ የማውቀው እግዚአብሔር አይደለም።
 ለማንኛውም በሰው የደረሰው ደርሶ አንቺም የመመፃደቂያ ዘመንሽ አልፎ ስታለቅሺ እንደ ማየት የሚያዝናናኝ ነገር የለም።
ቅዱሱን መፅሐፍ ያነወራችሁ ከንቱዎች ዛሬ ጭንቅ ጥብብ ብላችሁ ማየት ፍትህ ነው። በሰው የደረሰ መጨነቅና መጠበብን ማየት ርትዕአዊ ነው።
ለኢትዮጵያም ለኢትዮጵያዊነትም አይደለም እንባችሁ።
 ጥቅማችን ይቀራል የሚል ነው ስጋታችሁ።
 ስላረረባችሁ ነው የምታማስሉት።
 ኢትዮጵያዊነት ቢሆን ኖሮማ ያ ሁሉ ሰው እንደ ከብት ሲታረድ አብረሽ በጮህሽ ነበር።
Filed in: Amharic