>

አፍሪካ እስካሁን በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር እንደሆነች ታውቃላችሁ? (ሄርሜላ አረጋዊ)

አፍሪካ እስካሁን በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ስር እንደሆነች ታውቃላችሁ?
ሄርሜላ አረጋዊ

14 የአፍሪካ ሀገራት በፈረንሳይ እጅ የወደቁት  ለፈረንሳይ  መንግት ታክስ እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የሚከተሉት ይሆናል፡፡
ቤኒን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ጋቦን፣ ጊኒ- ቢሳው፣ አይቮሪኮስት፣ ኮንጎብራዛቪል፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ሴኔጋል፣ ቶጎ፣ ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኢኳቶሪያል-ጊኒ፣ ካሜሮን እና ቻድ ናቸው።
ጅቡቲም ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ በፈረንሳይ ሞግዚትነት ነው የምትደዳደረው። ያለ ፈረንሳይ ፍቃድ አዲስ ሕግ ማውጣት አትችልም። ባለስልጣናት መግለጫ ሚሰጡት በፈንሳይ ቋንቋ ነው ።
ይህ በጥንቃቄና በዘዴ የተዋቀረ “Compulsory Solidarity” 14 የአፍሪካ ሃገሮችን ያካተተ ሲሆን፣ ግዴታውም በቀኝ ግዛትና በባርነት ወቅት ፈረንሳይ ለገነባቻቸው መንገዶች መሰረተ ልማቶች ላወጣቻቸው ወጪዎች ካሳ ይሆናት ዘንድ ከነዚህ አፍሪካ ሃገሮች ከውጭ ምንዛሪና ተቀማጫቸው ላይ 65% ለፈረንሳይ ቀጥታ Treasury ድጎማ ያስገቡላታል። (500billion$)
ይህ ብቻ ሳይሆን 20% financial Liability ይከፍላሉ። ይህ ማለት ከጠቅላላ ገቢያቸው 15% ብቻ ነው ለራሳቸው ሚያውሉት ማለት ነው።
ገንዘብ ካስፈለጋቸውም ብድር ከፈረንሳይ መንግስት የራሳቸውን ብር መልሰው ይበደራሉ።
ይህ እንግዲህ ከ1960 G.C ጀምሮ እየተተገበረ ያለ ግፍ ነው።

ለምን አንከፍልም አይሉም?

ቀላል የሚመስል ጥያቄ ነው። ሴራው ግን ውስብስብና በተንኮል የታጨቀ ግፍ ነው።
ሴኩ ቱሬ የጊኒ ፕሬዝደንት ሞከረ። “አልከፍልም እንቢ!” አለ። ከኮሎኒ ኢማፓየርም እራሱን አገለለ።
ፈረንሳይ ተቆጣች። በጊኒ ያለው የፈረንሳይ ጦርና አስተዳደር ሁሉንም ነገር” በፈረንሳይ ኃብት የተገነባ” ያሉትን ሁሉ ማውደም ጀመሩ።
3000 ፈረንሳውያን ሃገሪቷን ጥለው ሲሄዱ ተንቀሳቃሽ ንብረት አንድም አልቀራቸውም። ማይንቀሳቀሱትን ት.ቤት፣ ሆስፒታል፣ መንገድ፣ ህንፃዎችን አወደሙ።
መድኃኒት፣ መኪኖችን፣ ትራክተሮችን፣ መፅሐፍትን አቃጠሉ።
እንስሳት በሬዎች ላሞች ፈረሰችን #ገደሉ። በመጋዘኖች ያሉትን እህሎች ቀበሩ፤ መረዟቸው። ሃገሪቱን እንዳልነበረች አደረጓት።
ይህም የሆነው ማንም ሃገር ፈረንሳይ ላይ አምፃለሁ ቢል የጊኒ እጣ እንደሚደርሰው ማስጠንቀቂያ ነው።
የጊኒው ሴኮ ቱሬን “we prefer freedom in poverty to opulence in slavery” የሚለውን መፈክር ማንም ሃገር በፍርሃት ሊያስቀጥለው አልወደደም።
በ612$ #መፈንቅለ_መንግስት የቶጎው ተመራጭ ፕሬዝደንት Olympion የራሱን መገበያያ ማተም ከጀመረ በሦስተኛው ቀን ፈረንሳይ ባሰማራቻቸው #የገዛ_ወታደሮቹ ተገደለ።
ለገዳዩቹም ፈረንሳይ በኢምባሲዋ በኩል #612_ዶላር ጎሽ! ብላ ከፍላቸዋለች።
Olympion ህልሙ ነፃ፣ ራሷን የቻለች አዳጊ ቶጎን መገንባት ነበር። ፈረንስይ ሃሳቡን አልወደደችለትም እንጂ…
መፈንቅለ መንግስት
ባለፉት ሃምሳ አመታት በ26 አፍሪካ ሃገራት ውስጥ ከተደረጉት 67 መፈንቅለ መንግስታት 16ቱ የፈረንሳይ የቀድሞ ቀኝ ግዛት ሃገሮች ውስጥ ነው። ይህ ማለት 67% መፈንቅለ መንግስታት የተደረጉት በፈረንሳይ ድጋፍ ነው ማለት ነው።
ቶማስ ሳንካራን የበላው ጅብም የፈንሳይ ስሪት ነው።
የግፍ ክፍያዎች
1. Colonial_Deb~ፈረንሳይ ለገነባቻቸው መሰረተ ልማቶች የሚከፈል።
2Automatic_Confiscation of national reserve~ ሃገራቱ ብሔራዊ መጠባበቂያ ገንዘባቸውን France Central Bank ማስቀመጥ።
3 Right of First refusal (raw or Natural Resource)~ፈረንሳይ በሃገራቱ መሬት ላይ ያለን የትኛውንም የተፈጥሮ ኃብት ቀድማ የመግዛት መብት አላት “አልፈልገውም” ካለች ብቻ ነው ሌላ ገበያ ማፈላለግ ሚጀምሩት።
4 Priority_to _France~የፈረንሳይ ካምፓኒዎች የህዝብ መገልገያ የሆነን የትኛውም ህንፃ ቅድምያ የማግኘት መብት አላቸው።
5. Military_Equipment & Trainings ~የትኛውም ወታደራዊ ስልጠናም ሆነ ቁሳቁስ በፈረንሳይ በኩል ብቻ ነው በክፍያ ማግኘት ሚችሉት።ፈረንሳይ ወታደሮቿን ማሰማራት ቤዝ ማግኘት ትችላለች።ፈረንሳይ ችግር ካጋጠማትም ከጎኗ የመቆም ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
6 Obligation of French Language አፀያፊ ባህልም ቢሆን።
7 Report ~ለፈረንሳይ ዓመታዊ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታም አለባቸው።
ምእራባውያን በእርዳታ ስም ከፍተኛ ልገሳ የሚያደርጉልን አዝነውልን፣ ወይም ጥሩ ሰዎች ስለሆኑ  ወይም ደግሞ ህሊናቸው ስለሚቆጠቁጣቸው አይደለም። በሚሰጡን እርዳታ ልክ እንደሚቆጣጠሩን ስለሚያውቁ ነው።
በአጭሩ ነጮቹ ከአፍሪካ ጥቅም ሲፈልጉ እና ለእነሱ ትርፍ ካለው እጃቸውን አስገብተው የፈለጉትን ከመውሰድና የነሱን ጥቅም የሚያስከብር አፍሪካዊ መሪ ለማስቀመጥም ሆነ ከስልጣኑ ለማስነሳት ምንም አያግዳቸውም ነገር  ግን ለነሱ ጥቅም ከሌለው በችግር ሰአት አፍሪካ እርዳታ ብትጠይቃቸው ምእዕራባውያን እየሳቁ ይመለከቷታል።
Filed in: Amharic