>

አምርረው ቢጠላሉም፣ ጥላቻ አስተሳስሯቸዋል‼ (አወድ መሀመድ)

አምርረው ቢጠላሉም፣ ጥላቻ አስተሳስሯቸዋል‼
አወድ መሀመድ

ኢትዮጵያ እንደ ሃገር እንዳትቀጥል የሚሹ የተለያየ ዓይነት አመለካከት ያላቸው ሰዎች በውስጣችን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል እነዚህ ሀይሎች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ህውሓትን ለማትረፍ የሚያደርጉት ትግል ይመስለኛል። እነዚህ ሃይሎች ህውሓትን የማትረፍ ትግሉን በስውር እና እራሳቸውን የሰላም ሰባኪ አድርገው የሚቅረቡ ናቸው። አንዴ እራሳቸውን በብሄር ካባ ስር ሲደበቁ ቀጥለውም በሀይማኖት ካብ ሲርት ሲወሸቁ ይታያሉ። እነዚህን ሀይሎች አብይ Variety የሚል ገፅ በተወሰነ መልኩ ዘርዝሮ አቅርቦዎቸዋልና እኔም ትወያዩበት ዘንድ ከታች በገፄ ላይ አውጥቼዋለው።
ህውሓትን ለማትረፍ የሚታገሉ ሀይሎች፦
1- ኢትዮጵያ የአማራ፣ ትግሬና ኦርቶዶክስ አገር ስለሆነች፣ እስላምና ጋ* ኢትዮጵያን ከገዛ አገር ትፈርሳለች የሚሉ። እነዚህኛዎቹ እስላምና ጋ* ገዝቶ አገር ከምትኖር ብትፈርስ ይመርጣሉ። ኢትዮጵያ ከግራኝ አሕመድና የኦሮሞ መስፋፋት ከተረፈች አሁንም መትረፏ ስለማይቀር የዘመነ መሳፍንቱን ዓለም በዚህ ዘመን ለማምጣት የሚጥሩ ናቸው።
2- አሁን ያለችዋ ኢትዮጵያ የአማራ፣ ትግሬ እና ኦርቶዶክስ ስለሆነች መቀጠል የለባትም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህችን ኢትዮጵያ እያስቀጠለ ስለሆነ ኦሮሞ ተጠቃሚ አይሆንም የሚሉ ኦሮሞ ብሔርተኞች።
3- ኢትዮጵያ የአማራ፣ ትግሬና ኦርቶዶክስ ውጤት ስለሆነች ሙስሊሞችን ስትበድል ኖራለች። ይህች ኢትዮጵያ ከቀጠለች የሙስሊሙ በደል ይቀጥላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህችን ኢትዮጵያ እያስቀጠለ ነው። ስለዚህ ይህች ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት ብለው የሚያምኑ ከወሃቢዝም/ኢኽዋን ተከታይ ሙስሊሞች በርካቶቹ።
4- በህውሓት ተጠቃሚ የነበሩ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቅም ጠብቀው የቀረባቸው። እነዚህ ይህች ኢትዮጵያ ከቀጠለች ጥቅማችን ይቀርብርናል፤ የተዳከመች ኢትዮጵያ ኖራ ጥቅማችን ቢቀጥል ብለው የሚያምኑ ጥቅመኞች ናቸው።
እንግዲህ እነዚህ እጅጉን ቢለያዩም፤ በተለይ የመጀመሪያዎቹና ቀጣዮቹ ሁለቱ አምርረው ቢጠላሉም፣ ጥላቻ አስተሳስሯቸዋል። ህውሓትን ለጥቅማቸው ሲሉ አምርረው ቢጠሏትም እንድትቆይ ይፈልጋሉ።  በየሚዲያዎቻቸው እየተናበቡ መንግሥትን ለማዳከም ይሠራሉ፤ ህዝብን ለመክፈል ይጥራሉ።
የነዚህ ተቃራኒዎቻቸው 
ኢትዮጵያ የተመሠረተችው በህዝብ ትሥሥር ነው። የተለያዩ ማንነቶች በዘመናት ሂደት እየተጋመዱ፣ እየተሳሰሩ የገነቧት፤ ወደፊትም የሚገነቧት። በዚህ ሂደት ልክ እንደቤተሰብ ልንጣላ እንችላለን። አንዳችን ሌላችን ላይ ተፅዕኖ ልናሳድር እንችላለን። ኢትዮጵያ ግን ወደ አሪፍነት እየተለወጠች ነው። ዛሬው ከትላንቱ ይሻላል ብለው የሚያምኑ ናቸው። ከኢትዮጵያ ጎን የተሠለፉት ኢትዮጵያችን የሁላችንም ነች፤ የሁላችንም ትሆናለች ብለው የሚያምኑ ናቸው።
እናም ከግንባሩ ወዲህና ወዲያ የተሰለፉት ሃይሎች እነዚህ ናቸው። ጠዪዎችና ወዳዶች፤ አፍራሾችና ገንቢዎች፤ ጨለምተኞችና ተስፈኞች ናቸው። ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው በሁለቱ ሃይሎች ነው።
Filed in: Amharic