>

"ባልደራስ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአቤቱታ ደብዳቤ ጻፈ....!!!"

“ባልደራስ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአቤቱታ ደብዳቤ ጻፈ….!!!”

እስረኞች እንዲፈቱ እና በእስር ቤት የሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበር ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አቤቱታ አስገባ።
     ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በግፍ ታስረው የሚገኙ የባልደራስ መሪዎችን ጠይቀው ሲመለሱ “ፎቶ አንስታችኋል”በሚል ሰበብ ኅዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም አምስት የባልደራስ አባላት መታሰራቸው ይታወቃል።
   በመሆኑም እስካሁን ድረስ ያለጠያቂ ቂሊንጦ ክራውን ሆቴል ጀርባ ታሰረው የሚገኙ አባላት ባስቸኳይ እንዲፈቱ እና በእስር አያያዛቸው ወቅት ሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበር  የሚጠይቅ አቤቱታ ባልደራስ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስገብቷል።
አባሎቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈቱ ይገባል !!!
Filed in: Amharic