>

የአማራን ህዝብ ስጋ ትበሉትና ደሙን  ትጠጡት ይሆን? (ሸንቁጥ አየለ)

የአማራን ህዝብ ስጋ ትበሉትና ደሙን  ትጠጡት ይሆን?

ሸንቁጥ አየለ

1.ከምስራቅ ወለጋ 26 ተሽከርካሪዎች ከነ ሙሉ ተሳፋሪዎቻቸዎ በኦነግ ሸኔ እና በኦህዴድ ትብብር ታግተዉ የት እንደተሰወረ አይታወቅም።ከአካባቢዉ ለመሸሽ ቢሞክሩም በመንግስት ተባባሪነት ህዝቡ እንዲጨፈጨ እየተደረገ ነዉ።
2. ሊሙ ወረዳ ላይ ከኦነግ ጭፍጨፋ ያመለጡ አማሮች አምስት ሽህ ብር ክፍሉ ከተባሉ ብኋላ ከአካባቢዉ እንዳይወጡ በሊሙ ወረዳም እየታፈኑ እና እየተጨፈጨፉ መሆኑ ተዘግብቧል። ከኦነግ ሸኔ ቢያመልጥም ሊሙ ወረዳ ደግሞ ሌላ የአማራ ህዝብ የእርድና የእልቂት ቦታ መሆኑ በተወሰኑ እዉነተኛ ሚዲያዎች በስፋት እየተዘገበ ነዉ።
3.ከወለጋ ወደ አዲስ አበባ አልጠዉ የገቡ አማሮች ከአዲስ አበባ በግዳጅ በኦህዴድ ካድሬዎች እየታፈሱ መልሰዉ ለኦነግ ሸኔ ፍጅት ተላልፈዉ እየተሰጡ ነዉ።
4.በአዲስ አበባ ለመረዳት እና ለመጠለል የሞከሩ ቀሪ የወለጋ ተፈናቃዮች ደግሞ በኦህዴድ ትዛዝ በየትኛዉም ቀበሌ እና ተቋም እንዳይጠጉ እየተደረጉ መሆኑ በብዙ መረጃ እየተዘገበ ነዉ
5. ከምስራቅ ኦሮሚያ ብቻ በአጭር ጊዜ ብቻ ከሁለት መቶ አምሳ ሽህ /250, 000/ አማሮች በላይ መጨፍጨፋቸዉን እና መፈናቀላቸዉን በሀገር ቤት እና በዉጭ ያሉ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነዉ
6. በአማራ ህዝብ ላይ በኦህዴድ በኦነግ ሸኔ ቅንጅት ስለሚጨፈጨፈዉ አማራ ማንኛዉም አክቲቪስት፡ የመንግስት ሚዲያ እና የግል ሚዲያ መዘገብ የለበትም የሚል አቅጣጫ በመስጠቱ ከብአዴን አህዮች እስከ ሆዳም የአማራ ብሄረተኞች እና አስመሳይ የኢትዮጵያ አንድነት ሀይሎች የጋራ የጆሮ ዳባ ልበስ ፡ ኦህዴድ ከሚከፋ የአማራ ህዝብ ይለቅ የሚል ቁርጥ አቋም መያዛቸዉ ግንዛቤ ተይዟል።
7.በምስራቅ ወለጋ ስላለዉ የአማራ ማህበረሰብ እልቂት የዘገቡ የሀገር ዉስጥ በርካታ ሚዲያዎች እና ጋዜጠኞች ከፍተኛ አፍና እየተደረገበት መሆኑ እና ጥቃት እየደረሰባቸዉ መሆኑ እየተዘገበ ነዉ።
 
ከትናንቱ ይልቅ ዛሬ  በወንጀል አፈጻጸም እጅግ ከፈተኛ እድገት አሳይታችኋል:- በተለይ የአማራን ነገድ ከምድረ ገጽ በማጥፋት እና በማስጠፋት
————————
ኦህዴዳዉያን እና ብአዴናዉያን ሆይ የወያኔን ሰዉ አራጅነት ለኢትዮጵያ ህዝብ ምን ትነግሩታላችሁ? ሃያ ሰባት አመታት እናንተ እራሳችሁ
 ዋናዉ የወያኔ የሰዉ ማረጃ ማሽን ነበራችሁ::
———-
አሁን ግን የናንተ የሰዉ አራጅነት:አሳራጅነት: የህዝብ አስፈጅነት ወንጀል በወለጋ በትንሹ ከ250,000 ህዝብ በላይ በጥቂት ወራት ዉስጥ ብቻ ጨፍጭፋችኋል::አፈናቅላችኋል::እስኪ ስለሱ ወንጀላችሁ ንገሩን::
ይሄዉ ወንጀላችሁ አሁንም በየቀኑ ቀጥሏል:: በወያኔ ጊዜ ትሰሩት ከነበረዉ ወንጀል የአሁኑ ወንጀላችሁ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል::እሱ ብቻ ሳይሆን ህዝብ ስለ ወንጀላችሁ እንዳይናገርም ህዝብን ዝም ማሰኘት ተቃዋሚ የሚባሉትንም በጥቅም ገዝታችሁ ዝም ማሰኘት ችላችኋል::
የአማራን ነገድ በጅምላ እያጠፉና እያስጠፉ ህዝብን ማደንዘዝ እና ተቃዋሚዉን ዝም ማሰኘትን ከወያኔ ይልቅ በጣም በጣም እጅግ በጣም ተክናችሁበታል::በዚህም በወንጀል አፈጻጸም እጅግ ከፈተኛ እድገት አሳይታችኋል::
—–
ስለወያኔ ጭካኔ እና አራጅነት እየነገራችሁ እራሳችሁን እንደ ጻድቅ አታቅርቡ::ትናንትም አራጅ እና አሳራጅ ነበራችሁ::
የዛሬዉ ወንጀላችሁ ደግሞ የከፋ እና የከረፋ ሆኗል::
—-
——
አሁን እዚህ ፖስት ስር ማን መጥቶ እንደሚሳደብ ልብ በሉልኝ::አዳዲሶቹ የኦህዴድ ወዶ ገቦች የአሳማ ብሄረተኝነት ንቅናቄዎች ናቸዉ::
የስድባቸዉ ዋና ምክንያት ደግሞ አማራ አሁን በወለጋ ይታረድ::ስለሱ አሁን አያገባንም::አሁን ዝም በሉ የሚል ነዉ::የግንቦት ሰባት አስተምህሮት አዳዲሶቹን አሳማ ብሄረተኞች አሳዉሯቸዋል::
ግንቦት ሰባት ለአስራ ሁለት አመታት አማራ ሲፈናቀል አማራ ተፈባቀለ ካላችሁ የኢትዮጵያን አንድነት ትጎዱታላችሁ እያለ የደነቆረዉን የአማራ ምሁራን አፉን ይዞት ኖረ::
አሁን የተነሱት የአሳማ ብሄረተኝነት ንቅናቄዎች ደግሞ በግንቦት ሰባት አስተምህሮት ተጠልፈዉ: ለኦህዴድ ወዶ ገባ ሆነዉ በአማራ ስም ተደራጅተዉ አማራዉ ይለ ዝም በሉ ባይ ሆነዋል::
—-
ቱፍ….ይሄን ሁሉ በህዝቤ ላይ የሚቀልድ አሳማ እማ በቀላሉ አልፋታዉም::
Filed in: Amharic