>

"ተሸንፈናል" ላለማለት  ደብረፅዮን ለትግራይ ሕዝብ ያቀረበው ተማፅኖ!!!! (ወንዴ ብርሀኑ)

ተሸንፈናል” ላለማለት …,.

ደብረፅዮን ለትግራይ ሕዝብ ያቀረበው ተማፅኖ!!!!
ወንዴ ብርሀኑ
*…. (“ለምን ሸሻችሁ” በሚል ከትግሬ ሕዝብ በኩል ለሚቀርበው ከፍተኛ ትችትና ጥያቄ ደብረፅዮን አቀረበው  ከተባለው ተማፅኖ)
~ወደኋላ ለማፈግፈግ ያስተላለፍነው ውሳኔው የኛንም የጠላትንም የሁኔታ ግምገማ አድርገን የወሰነው ውሳኔ ነው። መመለስ አለብን፣ ባለንበት ልንቀጥል አይገባም፤ ተጨማሪ ማስተካከያዎችና መስተካከሎች ያስፈልጋሉ የሚል ትልም አስቀምጠን ነው የወሰነው።
~ውሳኔው ቀላል ውሳኔ አይደለም፣ እጅግ ከባድ ውሳኔ ነው፤ #ፍላጎታችን አዲስ አበባ ለመግባት ቢሆንም ውሳኔያችን ማፈግፈግ ነው። ውሳኔያችን ከፍላጎታችን ተቃራኒ ነው። ፍላጎታችን አአ መግባት ነው፣ የወሰነው ግን መመለስ ነው፤ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ስላሉ መመለስና ማስተካከል አለብን ወደሚል ገብተናል።
~የማፈግፈግ ውሳኔውን በድርድር ወይንም በጫና ሳይሆን በራሳችን ያደረግነው ነው፣ ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ብለን ነው።
~የማፈግፈግ ውሳኔው  ቀድማችሁ አላሳወቃችሁም የሚል ወቀሳ መጥቷል። ይሄ ወታደራዊ ጉዳይና እንቅስቃሴ ነው ስለዚህ ቀድመን ልናወራ አንችልም
~ጠላትን በቀላሉ የምታሸንፈው አይደለም። ስንት ታግለን፣ ላይ ታች ለፍተን፣ ስንት መስዋዕትነት ከፍለህ ነው ድል የምታገኘው። ስለዚህ ጠላትን ለማሸነፍ አቅጣጫ እንቀይር ሜዳ እንለውጥ እያልን ነው።ጠላትኮ ዝም ብሎ አይጠብቀንም። በተለይ ሞቱና የሞት ጉድጓዱ ስትቀርብ ያለ የሌለ ሃይሉን ይጠቀማል። አሁን ላይ እያየን ያለነው ይሄንን ነው። እጁ ላይ ያለውን (መሣሪያ) ብቻ ሳይሆን ከውጭ አገርም እያስገባ እየተዋጋ ነው። ውጊያው ቀላል አይደለም፤ ጠላትም የሞት ሽረት እያረገ ነው። ስንት ሃይል እንዳንቀሳቀሱብን አይታችኋል። አሁንም የውጭ (አገራት) እጆች ወደ ጦርነቱ መግባት እየጨመረ መጥቷል፤ ይሄ #ጫና የለውም ማለት አይቻልም። ስለዚህ እንዳይሞት ሁሉንም የአገር ውስጥ ገንዘብ፣ ኢኮኖሚ፣ የሰው ሃይል፣ መሣሪያ ፣ ሚዲያ ሁሉንም ነገሮች እየተጠቀመ ነው። ||ሽንፈቱን ያመነበት ንግግር||
~ አማራ በሚዲያ የሚያስተላልፈው መልዕክት ይታወቃል። የሰው ልጅ ሊናገረው የማይችለው የአረመኔ ንግግር ፣ የአረመኔ ሀሳብ እየሠማን ነው። ለትግራይ ህዝብ ያላቸውን ግልጽ ጥላቻ እያየን ነው።ለነገ የሚል ንግግር እንኳን የለም። ይህቺ ንግግር ድሮም የቆየች ነች። ስለዚህ እኛም አምርረን ልንታገል ይገባል ማለት ነው። #ልናቃልለው አንችልም፣ አምርረንና አክብደን ልንታገለው ይገባል። ጠላት እስኪጠፋ ትግላችን ከባድ ነው። የጀመርነውን ትግል የተወሰኑ ማስተካከያዎች አድርገን መጨረስ አለብን።
~ድልን ዝም ብለን ሰተት ብለን የምንገባበት ጉዳይ አይደለም።  ደርግን ለማሸነፍ 17አመታት ነው የፈጀብን።
~አሁን ደግሞ ሰ.ሸዋ ደርሰን ግን ማስተካከል አለብን ብለን ነው የተመለስነው። በደብረታቦር ጫፍ ደረስን እንመለስ ብለን ተመለስን፣ሃይቅ ደረስን እንመለስ ብለን ወደ ውጫሌ ተመለስን፣ በደባርቅ ሄድን እንመለስ ብለን ተመለስን፣አሁን በምናካሂደው ጦርነት እንኳን ሄደን ነው የተመለስነው።
~ ሁሉም ያውቀዋል፣ አሁን ላይ ምንም ይዘህ ብትሄድም ላለመሞት ሲል ሊመልስህ(ሊያሸንፍህ) ይችላል። ስለዚህ የትግራይ ሕዝብ በዚህ መልክ ሊረዳው ይገባል።
~የትግራይ ህዝብ ትግል አያቆምም። ግቡም የመጀመሪያው ደህንነቱ ቀጥሎ ህልውናው ቀጥሎ ወንጀለኞችን ተጠያቂ ማድረግ  የራሡን እድል በራሱ መወሰን ነው፣ #አገር መቆጣጠር አይደለም። የኛ ትግል አገር መቆጣጠር አይደለም የትግራይ ህዝብ ጥያቄ አአ በመቆጣጠር አይመለስም። አአ መግባት ጠላትን ሊያስወግድ ይችል ይሆናል እንጂ መልስ አይሰጥም።
~ስለዚህ ጠላትን የበለጠ ለመምታትና በተለይ #የደጀን መስመራችን በጣም ትልቅ ችግር ፈጥሮብን ነበር። ማሻሻል አለብን። አሁንም የትግራይ ህዝብ ግፍ እንደቀጠለ ነው። ጠላትን ለማሸነፍ እስከመጨረሻ መታገል ፤ ወይም ተገዶ ወደ #ድርድር እስኪመጣ መረባረባችንን እንቀጥላለን። የዚህ ውሳኔ አላማም ይሄው ነው።
~አሁንም ድረስ ተከበን ነው ያለነው፣ ይሄንን መስበር አልቻልንም፤ ችግር ውስጥ ነን፣ በርሃብና በበሽታ እየሞተ ነው፣ ይሄንን መስበር አለብን። ስለዚህ አንድነታችንን ጠብቀን፣ እጅግ ከባድ ችግር ውስጥ እንደሆንን ታውቃላችሁ። በርግጥ ከጦርነቱ አይበልጥም እና መታገል አለብን። ተከዜን መብራት መተውታል፣ የድሮን ድብደባ እንደቀጠሉ ናቸው፤ ትግሬን ማጥፋት ቀጥለውበታል። እነዚህን ችግሮች ተሸክመን ለማለፍና ለመታገል ነው ለማፈግፈግ የወሰነው።” (ለቅሶ ብቻ!)
Filed in: Amharic