>

"ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ቁጥር አንድ ሃያል ሆና ትወጣለች....!!!" (እስሌይማን አባይ )

“ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ቁጥር አንድ ሃያል ሆና ትወጣለች….!!!”

እስሌይማን አባይ 

     *… አሜሪካ ወሳኙን ድል ለቻይና አስረክባለች‼
 
የጆ. ባይደን እና ብሊንከን ታላቅ የዲፕሎማሲ ሽንፈት‼
“ቻይና ለኢትዮጵያ የማሸነፊያ መሳሪያዎች ስትሰጥ አሜሪካ ግን እየከሰመ ካለው የትግራይ አማፂ ቡድን ጎን ነው የተሰለፈችው” ይህን ያሉት የፔንታጎን የቀድሞ የደህንነትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ፀኃፊ የነበሩ ናቸው። በሮናልድ ሬገን የስልጣን ዘመን። ዶክተር ስቴፈን ብረይን ይባላሉ። አለም ላይ ስመጥር የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ባለሙያ መሆናቸው የሚነገርላቸውም ናቸው ዶክተር ስቴፈን።
ቻይና በጂኦፖለቲካ አካሄድ የአሜሪካን ጥቅም የነጠቀችባቸውን ሂደቶች ተከታትለው በመተንተንና ለዋሽንግተን ምክረ ሐሳብ በማቅረብ ታዋቂ የሆኑት ዶክተር ስቴፈን ቤይጂንግ በኢትዮጵያ ቀውስ ላይ ስኬታማ ውሳኔ ማድረጓን በቁጭት ገልፀዋል። የዶክተሩን ትንተና እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።
የኢትዮጵያ መንግስት ሃይሎች የሚያደርጉትን ዘመቻ የባይደን አስተዳደር የርስ በርስ ጦርነት እያለ በመጥራት በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ግፊት እያደረገና የአውሮፕላን ትኬት መግዛት ለማይችሉም ድጋፍ እያደረገ ነው።
በሌላ በኩል የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ አዲስ አበባን ጎብኝተው ቻይና የኢትዮጵያን መንግስት ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ ግልጽ አድርገዋል። ይህ ደግሞ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ከጣለችው በተቃራኒው ግን በአመፀኛው ትግራይ ላይ አይደለም።
አሜሪካ የትግራይ ሃይሎች የፈፀሙትን ግፍ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቀረበውን የእርዳታ ቁሳቁስ መዝረፋቸውን ለማውገዝ አልፈለገችም።
ቻይና ለኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት (ENDF) የታጠቁ፣ መካከለኛ ከፍታ ያላቸው፣ ረጅም ጊዜ የሚቆዩ ዊንግ ሎንግ ድሮኖችን ጨምሮ የጦር መሳሪያዎችን እያቀረበች ነው።
በኢትዮጵያ የተፈጠረውኝ ክፍተት የተረዳችው ኢራን ደግሞ ሙሀጀር-6 የተሰኙትን ድሮኖቿን እያቀረበች ነው።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ቀደም ሲል የቻይናውን ዊንግ ሎንግን ጨምሮ ሰው አልባ አውሮፕላኖችና እስራኤል ሰራሽ ጦር መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ አቅርባለች።
ኤምሬትስ የአሜሪካ አጋር መሆኗ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለምታደርገው ተሳትፎ ተፅዕኖ እንዳይደርስባት ረድቷታል። ቻይናም ኤምሬትስ በቀደደችው በመግባት በግልፅ እየተጠቀመችበት ትገኛለች። በጉዳዩ ዙሪያ የአሜሪካ አጋሮችን ለማራቅም አገልግሏታል።
ከሳምንታት በፊት ህዝባዊ ህወሓት ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ 209 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በነበረበት ወቅት የኢትዮጵያ መንግሰት ወደ ሊሸነፍ ተቃርቧል ቢባልም ወደነበረው መንግስት በቅርቡ ተቀይሯል። በአጭር ጊዜ ወደ ነበረበት ተመልሷል።  ኢትዮጵያ ሰራዊቷን አሰባስባ ከቻይና እና ከሌሎች አጋሮች የፖለቲካና የጦር መሳሪያ ድጋፍ ጋር የጦርነቱን መልክ ቀይራለች።
የአሜሪካ መንግስት በግጭቱ ውስጥ ገለልተኛ ነኝ ብትልም መስከረም 17 በኢትዮጵያ ላይ እና ህዳር 12 ኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለተመለከተ ዋሽንግተን ከማን ጎን እንደቆመች በግልፅ የሚያሳይ ነው።
ይልቁንም የባደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ጉዳይ በሩን ለቻይና ከፍቶ የሰጠው ከአሜሪካም ሆነ ከአሜሪካ አጋሮች ጋር ኢትዮጵያ አማራጭ የላትም ብሎ የደመደመ ጊዜ ነበር።
አሜሪካ የኢትዮጵያውን ቀውስ ለራሷ ጠቀሜታ ለማዋል የፖሊሲ አቅመ ቢስነት ታይቶባታል። ጦርነቱን ለጀመሩት ሐትግራይ አማፂያን ያሳየችው የምቀኝነት ድጋፍ የኢትዮጵያን መፃኢ ዕድል በቻይና እጅ በግልፅ እንዲቀመጥ አድርጓል። ይህም ለባይደን እና ብሊንከን ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ሽንፈት ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ENDF ወደ ወደ ትግራይ የሚያደርገውን ጉዞ እንደሚቀጠለ ሲሆን ግጭቱን ለመፍታት አሜሪካ መፍትሄ እንደማትሆነው ታውቋል።
ኢትዮጵያ ህወሃትን ማሸነፏ እና ትግራይን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ከህወሃት ካፀዳች የአፍሪካ ቀንድ ዋነኛ ሃያል ሆና ትወጣለች።
Filed in: Amharic