>

በሰሜኑ ጦርነት ድጋፍ ስለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የተላለፈ መልዕክት ! (ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ)

በሰሜኑ ጦርነት ድጋፍ ስለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የተላለፈ መልዕክት !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ

 

“እንደ አቅሜ፤ ድጋፍ ለሀገሬ!!!” 
 እኔ  እያለሁ  ወገኔ  አይደፈርም፤ አይራብም፤ አይሰደድም።
 
“እንደ አቅሜ፣ ድጋፍ ለሀገሬ!!!”
    በጦርነቱ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን እና ከአሸባሪው የወያኔ ኃይል ጋራ ፊት ለፊት እየተፋለሙ ላሉት የወገን ጦር አባላት ኑ በጋራ ድጋፍ እናድርግ!!!
    በጦርነቱ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን እና ከወራሪውና ከሽብርተኛው ኃይል ጋራ ፊት ለፊት እየተፋለሙ ላሉት የወገን ጦር አባላት ድጋፍ ማድረግ ማለት ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን፣ ዕርስትህን እና ማንነትህን መታደግ ማለት ነው።
    ይህንን ወራሪ ኃይል ከኢትዮጵያ ምድር በማጥፋት  የተረጋጋች፣ አንድነቷ እና ታላቅነቷ የተጠበቀ  ኢትዮጵያን ለመገንባት ሁላችንም በምንችለው  ሁሉ የተፈናቀሉ ዜጎቻችንን እና የወገን ጦር አባላትን እንደግፍ ።
      በመሆኑም በገንዘብ፣ በዓይነት እና በቁሳቁስ ይደግፉ።
      አድራሻችን 6 ኪሎ ከምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም 200 ሜትር ከፍ ብሎ ከሚገኘው የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጽ/ቤት ሥር ባለው የድጋፍ ማሰብሰቢያ ድንኳን።
 ለበለጠ መረጃ ፦
 – 0983 01-77-69
 – 0911 98-22-21
 – 0911 30-04-37
     ቢደውሉልን  አሉበት አካባቢ መጥተን  የቁሳቁስ ድጋፉን መቀበል  የምንችል መሆኑን እንገልጻለን።
     በተጨማሪም በገንዘብ መርዳት ለምትፈልጉ በአቢሲኒያ ባንክ የአካውንት ቁጥር 8405 34 81 እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000445394045 ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚቻለው ለዚሁ ዓላማ በተከፈተው የሒሳብ አካውንት ብቻ ይሆናል።
       የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ
Filed in: Amharic