>
5:28 pm - Friday October 9, 0753

"የትግራይ ሚዲያዎች ትናንትና ዛሬ ....!!!" (ወንዴ ብርሀኑ)

“የትግራይ ሚዲያዎች ትናንትና ዛሬ ….!!!”

ወንዴ ብርሀኑ

 

*… ሰናይት መብራህቱ  ‘አይዞን እናገግማለን ተስፋ አትቁረጡ” ስትል ጌታቸው አሁንም “ለስትራቴጂ ነው የምንሸሸው” ብሏል
– መቀሌ የሚገኘው ጋዜጠኛ ፍጹም ” የትግራይ ህዝብ ባጠቃለይ በተለይ እኔ ባለሁበት መቀሌ የመደናገርና ተስፋ የማጣት ነገር አለ። ነገር ግን አሁን በተፈጠረው ነገር ምንም መደናገጥና ሞራላችን መውደቅም የለበትም።” እያለ ይቀጥላል። በትግራይ ሰራዊት ተስፋ አንቁረጥ እናሸንፋለን …እያለም ሞራል ግንባታ ላይ ነው።
– የትግራይ ቴቪ ዜናዎች በሙሉ ከተንቤን ወጥተው መቀሌ በገቡባቸው ወቅቶች የተጠቀሙበትን ፕሮፓጋንዳ ጀምረዋል።
ካቀረቧቸው ዜናዎች 80%ቱ ተደፈርን፣ ተመታን፣ ተዘረፍን፣ ሊያጠፉን ነው…. የሚሉ ሴቶች የቀረቡባቸው  ዜናዎች ናቸው። በነዚህ ዘገባዎች የተደፈሩ ሴቶች ከልጆቻቸው ጋር ወደ አማራ ክልል ለመዝመት እንደተዘጋጁ ሲፎክሩ ይደመጣሉ። ይህም ትግላችን ገና እየጀመርን እንደሆነ የሚያሣይ ነው።
 ያኔ ህዝቡን በሌለ ናሬሽን ቆስቁሰው ወደጦርነት ለመማገድ የተጠቀሙበት መንገድ ነበር፣ አሁንም እንደ አዲስ ጀምረውታል። ባለፈው ከ1.8ሚሊዮን ህዝብ በላይ አንቀሳቅሰው እስከ ሸዋ ለመድረስ ከ500,000 በላይ ሃይላቸው እንዳለቀ የራሣቸው ሰው (የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር) ተናግሯል። ከሸዋና ወሎ እየወጡ ባለበት በዚህ ወቅት ሞቱ ከተባለው ቁጥር ቢብስ እንጂ አይቀንስም።
ከዚህ በፊት በተለይ ወራሪው ቆቦን እንደያዘ ከ90% በላይ ያለው ዜናቸው የድል ብቻ እንደነበር ልብ ይሏል።
– ዲጂታል ወያኔ በኢትዮጵያውያን በተረገ ርብርብ ተከርችሟል። የዩትዩብ ቻናሉን ለማዘጋት 5የተመረጡ ቪዲዮዎች በኢትዮጵያውያን ሪፖርት ተደርገውበት ነበር።
– የትግራይ ህዝብ በፈጣሪና በመላዕክት መካከል ላይ የሚገኝ ፍጡር ነው እያለ ያደርቀን የነበረው ካሣ ሃይለማርያም የጋሸና ምሽግ ሲከፈት እሱ ተዘጋ፣ 5ቀን አለፈው።
– የሳልሳይ ወያኔው ተስፋኪሮስ በትናንት ማታ ልጥፉ “ህወሀት የተባለ ነቀርሳ ስርአት እስካለ ድረስ አያልፍልንም፤ ሰዎችን በመቀያየር የማሌሊታውያንን እተሳሰብ ማጥፋት አይቻልም፤ እነሱ ከነስርአታቸው መጥፋት አለባቸው” የሚል ጽሁፍ አስቀምጧል።
– ሰናይት መብራህቱ  አይዞን እናገግማለን ተስፋ አትቁረጡ ስትል ጌታቸው አሁንም ለስትራቴጂ ነው የምንሸሸው ብሏል።
– አሉላ የባህል ጫወታውን ዘንግቶ የባህል መጠጥ እየጠጣ ነው።
– TMH የለም 4ቀን ሆነው
– ርዕዮት ከ5ቀናት (ጋሸና ከተሰበረ በኋላ) ጠፍቶ ብቅ ብሏል።
– ሌላው በየFBው በየቲውተሩ በየክለብ ሃውሱ ይጮኽ የነበረው መ..ጋ በሙሉ ጠፍቷል!
Filed in: Amharic