>

ከመቀሌ ሾልኮ የወጣው የጦር እቅድ (ነጋሪት)

ከመቀሌ ሾልኮ የወጣው የጦር እቅድ
ነጋሪት

የምርምርና ሰነድ ማዕከል (Center for Research and Documentation) በሚል የኤርትራዊያን ገጽ ሰሞኑን ትህነግ ያደረው ግምገማ ምስጢር
የትህነግ  ከጋሸና፤ ወሎ፤ ካሳጊታ፤ ጭፍራ፤ ወረኢሉ ሽንፈት በኋላ እቅዷ ወዴት ዞረ? ካለፉት ሁለት ሳምንታት የትህነግ የከሸፈ ወታደራዊ ዝላይ በኋላ የኢትዮጵያ ፌዴራል ኃይል ፤ ልዩ ኃይሎች እና ሚሊሻ የቅንጅት ጥቃት በእውቀት ላይ ተመስርተን ስንገልፅላችሁ ቆይተናል ።
በተለይ ስትራቴጂካዊት ወሳኝ  ቦታ የሆነችውን ሚሌን በመቁረጥ ወደ አሰብ ወደብ ለመቆጣጠር እና እንዲሁም  በደብረብርሃን አድርገህ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ያካሄደው የጦርነት ሙከራ የወጣቶች ደም በግፍ በከንቱ መፍሰስ ያስከተለበትና ጠላት የሽንፈት ካባ የተከናነበበት እና እንዲሁም የጠላት ቁመና ተመቶ ወደ ኋላ ለመሮጥ የተገደደበት ሁነት ነጥብ በነጥብ አስቀምጠነዋል ።
የዚህ የጠላት የጦር ቁመና መመታትበኋላ  ከአፋርና ከአማራ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ እየወጡ በኢትዮጵያ ኃይሎች እጅ ስር መውደቅ ጀምረዋል ።
በዚህ የሁለት ሳምንት የጦርነት ክንውን ከ100,000 /ከአንድ መቶ ሺህ /በላይ ተዋጊ ኃይል ሟችና ቁስለኛ እንዲሆን የተገደደው ማሌሊት /የሻዕቢያ አጠራር ነው/ የተረፈ ኃይሉ ከጋሸና ግንባር እስከ ሚሌ በተዘረጋው የእሳት ቀለበታዊ ሰንሰለት ተከቦ መውጫ ቀዳዳ አጥቶ እየረገፈ ነው ።
ይኼ ነው እንዲህ ለጃንዳ ማሌሊት የጦርና የፖለቲካ አመራሮች /ይህ አጠራር የኤርትራ ኃይሎች አጠራር ነው የአማራ ኃይሎች ትህነግ እያልን እንደምንጠራት ማለት ነው እንቀጠል በኤርትራዎች አጠራር /  ከባድ ንውፅውፅታ ከመፍጠሩም በላይ  ስትራቴጂያቸውን እንዲቀይሩም አስገድዷል ።
በዚህም መሠረት በሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ ) የሚመራው ከፍተኛው  የጃንዳ ማሌሊት የወታደራዊ ዕዝ ፤ ( በPLAN A ) ስትራቴጂ ተቀምጦለት  ከከሸፈው ወደ አዲስ አበባ የመግባት ወታደራዊ ህልም ወደ (PLAN B)  )ለመግባት ሳይወድ በግዱ  መርጧል ።
በመሠረቱ እጃችን ላይ የገባው ወታደራዊ ሚስጥር በሁለተኛ ደረጃ (PLAN B ) ተብሎ ተቀምጦ የቆየው ወታደራዊ ስትራቴጂካዊ ሚስጢር  እነሱ የምዕራብ ትግራይ እያሉ የሚጠሩት ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ፦ ጠገዴ ፤ አዲ ረመጥ፤ ቃፍታ ሁመራ፤ ዳንሻ፤ የባአከር  አየር ማረፊያን በመያዝ በነሱ አጠራር ምዕራባዊ  ትግራይ የሚሉትን ወልቃይት – ሁመራን ነፃ ማውጣት ነው ።
ከማሌሊት የጦር አዋቂ ወታደራዊ ተንታኞች የተደረሰው ድምዳሜ የሚሌ ግንባርን መቁረጥ ስላልተቻለ ይኼ (በPLAN A)  ይዘውት የነበረ ስትራቴጂ የጦር ግብ ነው ፤ ያ ስላልተቻለ ቀጣዩ የጦር አማራጫችን የተከፈለው መስዋእትነት ተከፍሎ የምእራብ ትግራይን በመቆጣጠር ከሱዳን ጋር የግንኙነት መስመር መክፈት የሚል ነው ። ይኼም ወታደራዊ ስትራቴጂክ ሚስጢር እጃችን ላይ ገብቷል ።
የከፍተኛው ወታደራዊ የትግራይ ሴንትራል ኮማንድ  ባለፉት አምስት ወራት ያደረጓቸውን ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች መሠረት በማድረገ የግምገማቸው ምስጢር ይህን ይመስላል።
1- ቀደም ብሎ በሌ /ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ የተሰጠው
” ጦርነቱ በእኛ ድል አድራጊነት ተጠናቋል” የሚል ድምዳሜ ስህተት መሆኑን በማመን በትግራይ ህዝብ ላይ ያልተባ ተስፋ በማሳደሩ ምክንያት በህወሓት የመሪነት ድርሻ ላይ ይኼ ተብሎ ሊገለፅ በማይችል እና ልንቋቋመው የማንችለውን ጫና የፈጠረብን መሆኑ ፤እንዲሁም ከዚህ መነሳት በተፈጠው የህዝብ ጫና ከፍተኛ ወታደራዊ ኃላፊዎች ላይ በስነልቦናዊ ጫና ምክንያት ለመክዳት ስሜት የሚያነሳሳ እና አንዳንድ ክስተቶች የፈጠረ መሆኑ ገምግሟል።
2- ቀደም ሲል በነበረው ግምገማ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፤ የአማራ ልዩ ኃይል ፤ የአማራ ሚሊሺያ ፤ የአማራ ፋኖ ፤ የአፋር ልዩ ኃይል  ሁለንተናዊ አቅም ላይ በከፍተኛው ወታደራዊ ሴንትራል ኮማንድ የተሰጠው ግምገማና ወታደራዊ ትንተና መሬት ላይ ካለው ሀቅ ፍፁም የራቀ ሆኖ መቆየቱና በተግባር ከገጠመን እና ካየነው ኃይል ጋር ፍፁም ተቃራኒ እና ከፍተኛ መስዋእትነት ያስከፈለን መሆኑ ፤
በተለይ የኤርትራ ኃይሎች  ከኢትዮጵያ የፌደራል ኃይሎች ጋር የፈጠሩት ጥምረት በኢትዮጵያና በኤርትራ የሚቃጣብንን ማጥቃት ልንከላከለው አይደለም ልንቋቋመውም አልቻልንም ።
ስለዚህ የኃይል ማፈግፈግ ማድረግና የመከላከል ቁመና መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ ገምግሟል ።
3- የትግራይ ሰራዊት እስከአሁን ከደረሰባቸው ቦታዎች በላይ ወደፊት ለመገስገስ የሚያችል አቅም የሌለው በመሆኑና የሚበዛው ኃይል ከትግራይ እርቆ በመሄዱ ትግራይን አደጋ ላይ እንድትወድቅ እንዳደረጋትም ገምግሟል ።
4- በሚሌ ግንባር ያጋጠመን መራር ሽንፈት በትግራይ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ የሞራ ስብራት ያወረደ በመሆኑ በስትራቴጂ ( PLAN A)  ተቀምጦ የነበረው ግብ ተፈፃሚነቱ ከዜሮ በታች መሆኑም ገምግሞ ወደ ቀጣይ የትግል ስትራቴጂ መሄድ ግድታ እንደሆነ ገምግሟል ።
5- PLAN B ብለን ያስቀመጥነው ስትራቴጂክ የጦር ግብ ወደ ምዕራብ ትግራይ ሰፊ የዘመቻ እንቅስቃሴ በመጀመር ከሱዳን ጋር የሚያገናኝ  ኮሪደር (መስመር) በመፍጠር ማስተንፈሻ የምንናገኝበት ወቅት ላይ በመገኘታችን የተከፈለው መስዋእትነት ተከፍሎ ያለ የሌለ ኃይላችንን በመጠቀም ኮሪደር የማስከፈት  ግዴታ ላይ የተገኘን በመሆኑ ይህን ማድረግ ወሳኝና የህልውና ዋስትናችን ነው በሚል ገምግሟል ።
Filed in: Amharic