>

"የመብት ተሟጋቹ ተከሰሱ...!!!"( D W)

“የመብት ተሟጋቹ ተከሰሱ…!!!”

D W


በጀርመን የኢዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚቴ መስራችና መሪ አቶ ሥዩም ኃብተማርያም አንድ የጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣንን ድርጊት በመቃወማቸዉ መከሰሳቸዉን አስታወቁ። ኢትዮጵያ ዉስጥና በኢትዮጵያዉያን ላይ ይፈፃማሉ የሚሏቸዉን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በመቃወም የሚታወቁት አቶ ሥዩም እንደሚሉት የተከሰሱት የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዉ የታጩትን አናሌና ቤርቦክን «ዘረኛ» በሚል መፈክር  በመቃወማቸዉ ነዉ። የአሮንጓዴዎቹ ፓርቲ ባለስልጣን የሆኑት የ40 ዓመቷ ፖለቲከኛ ቤርቦክ ባለፈዉ መስከረም ፍራንክፈርት ዉስጥ የምረጡኝ ዘመቻ ላይ እያሉ አቶ ሥዩምና አጋራቸው “አናሌና ቤርቦክ ዘረኛ ናት” የሚል የጹሑፍ መፈክር ይዘው መቃወማቸውን አቶ ሥዩም ተናግረዋል። በወቅቱ ፀጥታ አስከባሪዎች መፈክሩን ቀምተዉ አቶ ሥዩምና አጋራቸዉን ለ45 ደቂቃ በቁጥጥር ስር አቆይተዉ ለቀዋቸዋል። አቶ ሥዩም እንደሚሉት ፖለቲከኛዋን የተቃዋሙት፣ ባኤርቦክ ከማዕከላዊ የይሁዲዎች ምክር ቤት ጋር  በቴለቪዥን  ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጥቁሮችን የሚሰድብ ቃል በመጠቀማቸው ነዉ። «ቃለ መጠይቁ የሚሰራጨዉ ከሳምንት በኋላ ቢሆንም፤ ከመተላለፉ በፊት ባለማስቀረታቸዉና ይባስ ብለዉ በማባዛታቸው በወቅቱ ለማረም የነበራቸውን ጊዜ አልተጠቀሙበትም» ብለዋል። አቶ ሥዩም “እስሯኤል የጥቁር የሁዳውያንም ሃገር ሆና ሳለ ፍራንክፈርት የሚገኘው ማዕከላዊ የይሁዲዎች ምክር ቤት  ቃለምልልሱን ሳያርም ማሰራጨቱ አሳዛኝ» ብለዉታል። የጥቁር ቤተ እስሯኤላውያን ማኅበራትና  የፓርላማ አባላት የፍራንክፈርቱን  ማዕከላዊ የይሁዲዎች ምክር ቤት መጠየቅ ይገባቸዋል» ሲሉም ተናግረዋል።
Filed in: Amharic