>

ትላንት ዛሬ አይደለም...!!!  (አቶ አብርሃም አለኸኝ )

ትላንት ዛሬ አይደለም…!!!

 አቶ አብርሃም አለኸኝ 

ደሴ፣ ኮምቦልቻና ባቲ ከተሞች ከወራሪው ኃይል ነጻ መውጣታቸውን አሰመልክቶ ከተናገሩት


 

👉 ደሴ፣ኮምቦልቻና ባቲ ከተሞች ብቻ አይደሉም ነፃ የወጡት፤ ነጻ የወጣው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ህሊና ጭምር ነው፣
👉 የእነዚህ ከተሞችና አከባቢያቸው ከወራሪው ነጻ መውጣት የደሴ፣ ኮምቦልቻና ባቲ ነዋሪዎች ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰድ ብቻ አይደለም፣ በዚህ ውስጥ በርካታ እስራት ነው የሚፈታው፣
👉 ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር አብሮ የዘመተው መላው ህዝብ ነው፣
👉 ወጣቱ፣ አዛውንቱ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎችና  ሁሉም ግምባር ላይ ናቸው፤ ይህንን ድል ሁሉም መሰማት ይፈልጋሉ፣
👉 አሸባሪው የህወሓት ቡድን መረዳትና መገንዘብ ያልቻለው ከኢትዮጵያ ጋር ነው እየተጣላ፣እየተዋጋ ያለው፣
👉 ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያዊነት ስሜት፣ በወንድማማችነትና በአንድነት ተሰልፈው ጠላትን ቅልጥም ቅልጥሙን እየሰበሩ ከተሞቹ ብቻ ሳይሆኑ ህሊናችንም ጭምር ነው ነጻ ወጣው፣
👉 ከመከላከያ ኃይላችን ጋር ከጫፍ ጫፍ ተሰልፈው ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ለሚዋደቁት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፤ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ባቲን፣ ቀርሳን፣ ገርባን፣ ደጋንን ነጻ ያወጣ ሲሆን በሐርቡ ግንባር  ቃሉ ወረዳን ሙሉ ሙሉ ከወራሪው ኃይል ነጻ መውጣታቸው ይታወሳል።
Filed in: Amharic