>

"ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ...!!!" (ወዲ ሻምበል ዘ ብሄረ ኢትዮጵያ)

ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ…!!!”

ወዲ ሻምበል ዘ ብሄረ ኢትዮጵያ

የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ የሚለው ብሒል በዚህ ሰዓት በትክክል መሬት ላይ አለ። ለዚህም ትልቅ ማሳያው  በትግራይ ምድር ላይ ህወሓት በስልጣን እያለ ፊት ለፊት የታገሉትና የተጋፈጡት  ወደ ዳር ተገፍተው ትላንት ጀግኖች ታጋዮችን ሲያሳድዱ የነበሩ ባለስልጣናት ሆነው ማየት ያማል ለማንኛውም እቺን ከስር ያለች መልእክት የፃፋት ወደ ዳር ተገፍተው ከሚያዩት አንዱ የሆነው የማከብረው ወንድሜ የቀድሞው የህወሓት ታጋይ የነበረ ኃይለኪሮስ ታፈረ ነው የፃፈው።
የትግራይ ህዝብ እልቂትና ሰቆቋ በዋነኝነት ተጠያቂ ህወሃት ቢሆንም። በዓለም ታይቶ የማይታወቅ ወጣቶች እንደ ቅጠል የረገፉበት ዘግናኝ ታሪክ እንዲከሰት ያደረጉት አካላት ግን:-
በቅደም ተከተል ሊቀመጡ ይገባል።
በ1ኛደረጃ ህወሃት ሲሆን ።
በ2ኛ  ደረጃ በስመ ፓርቲ የተደራጁ  ሴረኞተች እነ
ባይቶና፥ውናት፥ሳወትሲሆኑ።
በ3ኛ ደረጃ ደግሞ አክትቢስቶችና  ሙሁራንነን ባዮቶ እንደነ  መረሳ ፀሃየ እንደነ መ/ር ሙሉወርቅ እንደነ  መ/ር ገ/ኪዳን ደስታና መሰሎቹ ሲሆኑ።
በ4ኛ ደረጃደ ደግሞ በስመ የትግራይ ጊዜያዊ መስተዳደር የተደራጁ  ቱባ ቱባ የህወሃት  ድብቅ አጀንዳ አራማጆች ሲሆኑ በተለይ ደግሞ በሁለተኛ ዙር የትግራይ ወጣቶቾ እልቂት የአንበሳ ድርሻ የተጫወቱትና  ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ መስዋእት የከፈሉበት እንዲከሽፍና ወደ ሁለተኛ እልቂትና መስዋእት እንድንገባ የዳረጉን ያልተነቃባቸው ሴሮኞችና ወንጀለኞች ናቸው። ሰለሆነም እነዚህ  ተኩላዎች በየደረጃቸው መድበን አስፈላጊ እርምጃ ካልተደረገባቸው  እልቂቱና ሴራው ይቆማል የሚል እምነት ፈፅሞ የለኝም።
ከህወሃትና ከህወሃት ጀኔራሐሎች በላይ ከፍተኛ ሴራና እልቂት በአገራችንና በተለይ በትግራይ ህዝብ ላይ እንዲፈፀም እያደረጉ ያሉትን ከሁለተኛ እስከ አራቱኛ የተቀመጡ ብልጣ ብልጥ ሴሮኞች ናቸውና  መንግስት የውስጥ አስመሳይ ሴሰሮኞች  ማፅዳት አለበት
ኢትዮጵያ አገራችን  የቁርጥ ልጆቿና የውስጥ ሴሮኞቿ  ልትለይ ይገባል!!
ኢትዮጵያ የገደላትን እየበላና እየተንደላቀቀ። የሞተላትን ደግሞ እየተዋረደና እየደቀቀ መኖር የለበትም።
የኢትዮጸጵያ ሞኝነት ይቁም!!!
Filed in: Amharic