>

"ጋዜጠኞቹን ፍቷቸው! የታሰሩበትም ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው ይገለጽ...!!!" (ያሬድ ሀይለማርያም)

“ጋዜጠኞቹን ፍቷቸው! የታሰሩበትም ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው ይገለጽ…!!!”
ያሬድ ሀይለማርያም

*…  ያስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጋዜጠኞችን ለማሰሪያ እና ማፈኛ እንደ ምክንያት መጠቀም የአዋጁን አላማ ያስታል።
ጋዜጠኞች በተናገሩትም ሆነ በጻፉት ጉዳይ ክስ መስርቶ ማስቀጣት እየተቻለ እስሮ መሰወር፣ ፍርድ ቤት አለማቅረብ፣ ቤተሰብ እንዳይጎበኛቸው እና ያሉበትን ሁኔታ እንዳያውቅ ማድረግ እና ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቀውን ጋዜጠኛ ሰውሮ አላየሁም ማለት የህውሃት/ኢሀድግን የ27 ዓመት ስህተት መድገም ነው።
 ታምራት ነገራ እና ክብሮም ወርቁ የታሰሩበት ቦታ እና የሚገኙበት ሁኔታ አለመታወቁ እጅግ ያሳስባል። ታምራት ከታሰረ 5 ቀኑ ቢሆንም ቤተሰቦቹ ያለበትን ስፍራ እንዳያውቁ ተደርገዋል። ክብሮም በዋስ ከተለቀቀ በኋላ ያለበት ሳይታወቅ 27 ቀናት ተቆጥረዋል።
የአሀዱ ሬዲዮ ዜና አርታይ ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ላይ እየደረሰ ያለው በደል እና የመብት ጥሰት እንደ ሀገር ወዴት እየሄድን ነው ያስብላል። ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቀው ጋዜጠኛ ቤተሰቦቹ የ15ሺ ብር ዋስትናውን ቢያሲዙም ክብሮምን ሊያገኙት አልቻሉም። ክብሮም የዋስትና መብቱ በፍርድ ቤት ቢረጋገጥም  ከእስር ሳይለቀቅ 26 ቀናት ተቆጥረዋል። ቤተሰቦቹም አካልን ነጻ የማውጣት ክስ አቅርበው ፖሊስ ቢጠየቅም ለቅቄዋለሁ ብሏል። ይሁንና ቤተሰቦቹ ፖሊስ ክብሮምን ለቅቄዋለሁ ባለበት ወቅት ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ውስጥ እንዳዩትና በሚኒባስ መኪና ተጭኖ ወደሌላ ስፍራ መወሰዱን ማስረጃ እንዳላቸውም ገልጸዋል። ጋዜጠኛ ክብሮም የት ገባ? የፍትህ ሥርዓቱ ወዴት እያቆለቆለ ነው? ፍትህ ለጋዜጠኞች!
ያስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጋዜጠኞችን ለማሰሪያ እና ማፈኛ እንደ ምክንያት መጠቀም የአዋጁን አላማ ያስታል።
ጋዜጠኞቹ ይፈቱ!!!
Filed in: Amharic