>

ኢትዮጵያ በማታዉቀዉ ህገ-መንግስት ኢትዮጵያን ለማፍረስ መነሳት...!?! (ሸንቁጥ አየለ)

ኢትዮጵያ በማታዉቀዉ ህገ-መንግስት ኢትዮጵያን ለማፍረስ መነሳት…!?!
ሸንቁጥ አየለ

–የኢትዮጵያ ህዝብ ባላጸደዉ ህገመንግስት ኢትዮጵያን ለመበታተን እንደ መደራደሪያ አጀንዳ አድርጎ መቅረብ ትልቅ ወንጀል ነዉ
-የወያኔን ህገመንግስት አስፈጻሚ ነኝ ብሎ የሚከራከረዉ ብልጽግና ከወያኔ ጋር ስለተጣላ ብቻ ትግራይን ከኢትዮጵያ ቆርጦ ለመጣል ብዙ ርቀት እየሄደ ነዉ::
-ወያኔ ቢቻል ከኢትዮጵያ ቢነቀል መልካም ነበር::ወያኔ የኢትዮጵያ ነቀርሳ መሆኑ አያጠራርጥርም:: ሆኖም በወያኔ አስታኮ ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመነጠል መስራት ግን እጅግ ትልቅ ታሪካዊ ወንጀል ነዉ::ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ነች::
-ሲጀምር አሁን ያለዉን ህገመንግስት ያጸደቀዉ ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነዉ::የትኛዉም የኢትዮጵያ ህዝብ የመከረበት እና የተስማማበት ህገመንግስት አይደለም::
-እናም ኢትዮጵያ በማታዉቀዉ ህገመንግስት ኢትዮጵያን ለማፍረስ መነሳት ታላቅ የሀገር ክህደት ነዉ::
-አቶ ሬድዋን ሁሴን የመንግስት ቃል አቀባይ ሚኒስቴር ዴታ “ድርድሩ ሪፍረንደም አንቀፅ 39ን ጨምሮ ሁሉንም አጀንዳዎች ያካትታል ” ብሎ የገለጸዉ እና ወ/ሮ አዳነች አበቤ ከተናገረችዉ  “ከፈለጋችሁ በህገ መንግስቱ መሰረት ተገንጥላችሁ ሂዱ”  ስትል የገለጸችዉ አቅጣጫዎች የሚያሳዩት ብልጽግና የወያኔን የተንኮል ሀገር ማፍረሻ ሀገመንግስት አሁንም ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደ መሳሪያ ሊተቀምበት እንደተነሳ ነዉ::
—————-
ምክር
——
የብልጽግና ሀይሎች ምክር የምትሰሙ ከሆነ ይሄን አይነት አካሂያዳችሁን አቁሙት::ከህዉሃት ጋር ስለተጣላችሁ ንዴት ዉስጥ ብትሆኑም ትግራይ የኢትዮጵያ ፍጹም አካል መሆኗን ግን አትዘንጉ::
Filed in: Amharic