>

ከ"አለም አቀፍ  ኢትዮጵያውያን የተባበረ ዳያስፖራ ጥምረት "   የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ 

ከ”አለም አቀፍ  ኢትዮጵያውያን የተባበረ ዳያስፖራ ጥምረት ”   የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ 

 እኛ በመላው አለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን፣ ዳያስፖራ ማህበራት በአሸባሪ ቡድኖች አማካኝነት በሉአላዊነታችን ላይ የተከፈተብንን ጦርነት ለመመከትና በምዕራባውያን ሚዲያ የሚሰራጭብን የተሳሳተ ቅስቀሳ በመፋለም፣ ለአለም አቀፉ ሕብረተሰብ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት፣ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲያደርግ የድጅታል ዲፕሎማሲ ስራንና ሰላማዊ ሰልፎችን በማዘጋጄት ቀጣይነት ያለው ጠንክራ ሰራ እየሰራን እንገኛለን።
 የዲያስፖራው ማህበረሰ ይህን የተየተጋረጠብንን የሉአላዊነት አደጋ ለመመከት፣ ሁላችንም በጋራ መቆም አስፈላጊ ወቅታዊ መሆኑን በማመን በጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ የተጠራውን የክተት ዘመቻ ተከትሎ የተለያዩ ብሔረሰቦች፣ ልዩ ሀይልና ፣ፋኖ ፣ ከመከላከያ ኃይላችን ጎን በመተባበር  የሉአላዊነት አደጋን የቀለበስንበትና ጁንታውን ወራሪ ሀይል ከመሸገባቸው ጉድጏዶች ጎሮሮውን አንቆ በማውጣት አከርካሪውን ሲሰብሩ እኛም በደጀንነት ከጎናቸው ተሰልፈን ሐገራዊ ጥሪውን ተቀላቅለናል።
 ይህ አገራዊ ጥሪ አብሮነታችንን ያጠናከርንበት ታላቅ ሕዝባዊ የሕልውና ዘመቻ በመሆኑ ወደፊትም በነፃነት ለመኖር የተስማማንበት  መስዋዕትነት እየከፈልንበት ያለና የአብሮነት አሻራችንን ያሳረፉንበት  ዘመቻ በመሆኑ በመላው አለም የምንገኝ የኢትዮጵያ የዳስፖራ አባላት በአንድነት ለአንድነት ህብረት በመፍጠር ከሕዝብና ከመንግስት ጋር መቆማችንን በድጋሚ የተረጋገጠበት  ኢትዮጵያጵያዊነት ያሸነፈበት ዘመቻ በመሆኑ የወደፊቱ የበጎ ታሪካችን ገፅታ ማሳያ ነው ብለን እናምናለን።
በተለይም የዚህ ዘመቻ አካል የሆነው 1 ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ ሐገር ውስጥ እንዲገቡ ጠቅላይ ሚ/ አብይ አህመድ በአለም ላይ ለሚገኙ የዳያስፖራው ማሕበረሰብ ያደረጉት ጥሪ፣ የስደት ማብቂያ ደወል አድርገን ስለተቀበለነው ልቦናችን መንፈሳችን ለቅድስት ሐገራችን ለኢትዮጵያ በልግስና ፍቅር በመስጠት በአንድነት ቆመናል።
ስለዚህ የምናደርገው ጉዞ አላማ  ግቡን እንዲመታ ” ፍቅር ለወገኔ.” በሚል መሪ ቃል እየተመራን ሐገራዊ ተልዕኮውን  ውጤታማ ለማድረግ ወደፊት መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ ተባብረን ለመስራት እቅድና ግባችንን ለማሳካት ” የአለም አቀፍ  ኢትዮጵያውያን የተባበረ ዳያስፖራ ጥምረት ” ስድስት አላማዎችን ለማሳካት ዛሬ ተመስርቷል።
1ኛ፣ ለሐገራችንን የገፅታ ግንባታ ማድረግ 
እንደሚታወቀው በአሜሪካን አስተባባሪነት ምዕራባውያን ሐይሎች ሲኤንኤን (CNN)፣ ሬይተርስ(Reuters)፣ ቢቢሲ(BBC) እና አሶሺዬትድ ፕሬስ (Associated Press) ሚዲያዎቻቸውን
ተጠቅመው የከፈቱብንን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ለማክሸፍና: አንድነታችንን የምናሳይበት፣ ጠላቶቻችንን አንገታቸውን የምንሰብርበት፣: የሚያሰራጩትን በሬ ወለደ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የምናመክንበት፣ የውጩን ሕብረተሰብ በተግባር እውነቱን በማሳየት የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲያደርግ ጭንቅላቱን መቀየር የምንችልበት ትልቅ መልእክት ለማስተላለፍ ነው።
 
2ኛ፣ የደረሰብንን የውጭ ምንዛሪ እጥረት መመከት
የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለዓመታት የአገሪቱ አንገብጋቢ ችግር ሆኖ ዘልቋል። ለ27 አመታት የወያኔ ስርአት  የአገሪቱን ሐብት ዘርፎ ወደ ባእድ ሐገር በማሸሽ  የተዛባ የንግድ ሥርዓት በማድረግ ሲያንገላታን የኖረ ቢሆንም በልፅገን ሐብታም ነን የሚሉት ሐያላን አገሮች ያሴሩቡንን ሴራ  ለማሳካት የመሪዎቻችንን እጅ ለመጠምዘዝ የእርስ በእርስን ግጭቶች በመደገፍ አለመረጋጋቶች እንዲፈጠሩ  አድርገው የውጭ ምንዛሪ በመከልከል  ለእጥረቱ መባባስ ትልቅ አስተዋፅዎ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ዳያስፖራው ይህንን ፣ በመመከት አገራዊ ግዴታውን ለመወጣት ዝግጁነቱን ያረጋግጣል።
3ኛ፣ የኢትዮጵያዊነት አንድነትን ማጎልበት
ኢትዮጵያዊነት፤ የምንደምቅበት ክብራችን ነው፤፣ ኢትዮጵያዊነት የጋራ አብሮነት ውጤት ነው!”  የጋራ መሰረት ያለን፣ የጋራ ጉዳይ ያለን፣ ለወደፊትም የጋራ እድል ያለን ሰዎች ነን፤ ስለዚህ በአንድነታችን የጋራ ጠላቶቻችንን አንበርክከን በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ተሰባስበናል።
4ኛ፣ የዲያስፖራ ቱሪዝምን ማበረታታትና ማሳደግ 
ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳሉት ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ የአገራቸው አምባሳደሮች ሆነው ማስተዋወቅ አለባቸው።
ስለዚህ የቱሪዝምን ዘርፍ በማዘመን የሕዝቡን ኑሮና የሐገሪቷን እድገት ከፍ ለማድረግ  የዳያስፖራ ቱሪዝም ለአገራዊ ኢኮኖሚ መጎልበት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ በዚህ ረገድ የጉዟችን ስትራቴጂካዊ አጀንዳ አድርገን በመውሰድ ከመንግስት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት ኢንቬስተሮችን ወደ ሐገር ውስጥ ለማስገባት ዳያስፖራውን  የቱሪዝም አምባሳደር ማድረግ ነው።
5ኛ፣  ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሀ ግብር መፈፀም 
 ውድ ሕይወቱን ለአገሩ እየሰጠ ለሚገኜው የመከላከያ ሰራዊት ደማችንን በመለገስ ኢትዮጵያዊነት በደም የተገመደ የማይበጠስ ሰንሰለት እንደሆነ አጋርነታችንን ማሳየት ሲሆን የደም መፍሰስ አደጋ ለገጠማቸው የመከላከያ ሰራዊት አባሎች ” ደማችን ለመከላከያችን ” በማለት ሕዝባዊ ደጀንነታችን በማስመስከር ሕይወታቸውን መታደግ ነው።
6ኛ ፣ የጦር ጉዳተኞችንና ቁስለኞችን መጎብኜትና ማበረታታት
የአገርን ሕልውና ለማስከበር በሚደረገው ዘመቻ ጉዳት የደረሰባቸውን ዘመን የማይሽራቸውን ጀግኖች በፈፀሟቸው ጀብዱዎችና መስዋእትነት ኢትዮጵያ ምንግዜም ስታከብራቸው እንደምትኖር በቦታው በመገኜት አልባሳትንን የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች ገዝቶ በማበርከት ማበረታታትና ድጋፍ መስጠት ናቸው።
** ተልእኮአችንና ግባችን  **
የፕሮጄክታችን መሪ ቃል ” ፍቅር ለወገኔ ” በመሆኑ ዛሬ በሐገራችን የሚካሄደው የህልውና ጦርነት ወያኔ የወሰደው የአጥፍቶ መጥፋት አላማ ብዙዎቹን የታሪክ ጮራ ፈንጣቂ የነበሩ፣ አንጋፋ ከተሞችንና የሐይማኖት ተቋማትን፣ እየመረጡ በእሳት በማቃጠል አመድ አድርገው አፈራርሰዋቸውል።
እነዚህን ከተሞች መልሶ ለማቋቋም  በትንሹ 300 ቢሊዮን ብር በላይ ይፈጃል የሚል ግምት አለ። ስለዚህ የጉዟችን ግብና አላማ ለአገራችን የምንሰጠው የፍቅር ስጦታ ነው።  እውነተኛ የሐገር  የፍቅር ደግሞ በጎ አድራጎትና ርህራሄ በመሆኑ፣ ዋና ተልዕኮአችን ቤት ንብረታቸው የፈረሰባቸውና በጦርነት በግፍ የተፈናቀሉ ወገኖቹን መልሶ ማቋቋምና  የፈረሱ ከተሞችን መገንባት ነው።
እነዚህን በጎ አድራጎት ስራዎችን ለመስራት ከዲያስፖራው ሕብረተሰብ ግባችን 500 ሚሊዮን ዶለር መሰብሰብ ነው።
 ሐገራዊ ጥሪውን የተቀበለ ማንኛውም ዳያስፖራ ቢሔድም ባይሔድም 1ሚሊዮን ዳያስፖራ 100 ዶለር ቢከፍል 100 ሚሊዮን ዶለር. ከጉዞው በፊት ለመሰብሰብ ጥረት እንዳርጋለን ::
 ቀሪውን 400 ሚሊዮን ዶለር ደግሞ አገር ቤት ውስጥ በሚዘጋጅ ፈንድረዚግና የኮንሰርት ምሽት ከመንግስት አካላት ጋር በመተባበር  በውጭ ከሚገኙ የዳያስፓራ ማሕበራትና ጋር የተቀናጄ ስራ
በመስራት ያሰብነውን 500 ሚሊዮን ዶለር ለመሰባሰብ የጉዟችን አላማና ግብ ማድረጋችንን በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ እናረጋግጣለን።
ኢትዮጵያ በተባበሩት ልጆቿ አንድነት ታሸንፋለች
አለም አቀፍ  ኢትዮጵያውያን የተባበረ ዳያስፖራ ጥምረት “
Filed in: Amharic