>
5:13 pm - Thursday April 18, 3675

ስለ ድርድሩ....!!! (ዘላለም ጥላሁን)

ስለ ድርድሩ….!!!

ዘላለም ጥላሁን

– ከ450 ቢሊዮን በላይ ንብረት አውድመው፤
– ከ200 ቢሊዮን በላይ ንብረት ዘርፈው፤
– ብዙ ንፁሃንን ረሽነው፣ ደፍረው፣ አጎሳቁለው፤
ድርድር እንዴት? ድርድሩስ ከማን ጋር? ሰላም የሚጠላ የለም ግን እንዴት? 
 
*…. እንግዲህ ድርድሩ ግድ ከሆነ  አንድ እግራችሁን አሸንጌ፣ ሌላ እግራችሁን ተከዜ አድርጋችሁ ተደራደሩ። ኮስተር በሉ። ከዚህ የባሰ ምን ይመጣል። የቆምነው እኮ ደምና አጥንት ላይ ነው
 
ድርድር 1-ከህውሃት
ድርድሩ ከህውሃት ጋር ከሆነ፣ መንግስት አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው ቡድን ጋር ይደራደራል የሚል እምነት የለኝም። ከሆነም መንግስት ራሱን የአሸባሪ አቻ አድርጎ ቆጥሯል ማለት ነው ተብሎ ይተረጎማል። ይህ ህዝባዊም ህገመንግስታዊም ንቀት ነው። “በፍፁም” ብሏል መንጌ!
 ሰሞኑን አሸባሪውና አፈቀላጤዎቹ በህልማቸው ሳይቀር “ድርድር” እያሉ ነው። አቡነ አረጋዊ አንደርድሮ ይድፋችሁ!! ይሄን ያህል ካወደሙና ከዘረፉ በኋላ ድርድር:-)
ድርድር 2-ከትግራይ ህዝብ
የወንበዴው ዋሻ ከሆነው ከትግራይ ህዝብ ጋር በመደራደር፣ ወንበዴዎችን አሳልፎ እንዲሰጥ፣ የተረፉትን ልጆቹን ትጥቅ እንዲያስፈታ፣ የዘረፈውን ንብረት መርፌ ሳይቀር መመለስ ከቻለ ድርድር ሊደረግ ይችላል። የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። አለቀ። ብዙ እሾህ ቢያበቅልም ቅሉ።
 ድርድር 3-የአማራና የአፋር ህዝብ ከፌደራል መንግስት
አማራ ክልል ለወደመው፣ ለደረሰው ውድመት በተለዬ እቅድ (Marshall Plan) የበጀት ድጋፍ በማድረግ መልሶ እንዲያቋቁም ድርድር ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህም የትግራይ ክልል የዘረፈውን ካልመለሰ➔ የትግራይን በጀት በማዞር፣ ከሌሎች ክልሎች በጀት በማዞርና የአማራና አፋር ክልልን የግብር ተሰብሳቢ ለተወሰነ አመታት ለፌደራል እንዳይዞር በመወሰን ጭምር ሊሆን ይችላል። በየአመቱ የውድመት ማካካሻ በጀት መመደቡ የግድ ሆኖ፣ መልሶ ማቋቋሙ ባልተራዘሙ ሁለት ሶስት አመታት ማለቅ አለበት።
ከዚህ ውጭ የሌሎችን ተፅዕኖ ተቀብሎ መንደፋደፍ አያስፈልግም።
የብልጽግና ፓርቲ የሰላም ሰነድ ያካተታቸው ጭብጦች፣
 
1. የሰላም ጎዳና አቅጣጫችን ፣
1.1. በሰላም ጎዳና ላይ የምንከተለው አቅጣጫ እና ስልት ሁሉን የሚያሳትፍ፤ የግጭቱን ብቻ ሳይሆን ከግጭቱ ባሻገር ያለውን ምክንያቶች ያካተተ፤ የሕዝብ ጥቅምና የአገር ሉዓላዊነትን ያስቀደመ መሆን ይገባዋል።
1.2. በራሱ እምቢተኝነት ካልሆነ በስተቀር ከሰላሙ መድረክና ጎዳና ላይ ማንም ሊከለከል አይችልም።
1.3. የኢትዮጵያውያን ጉዳይ የኢትዮጵያውያን ነው።
2. ጦርነቱን በውይይት ማጠናቀቅ በተመለከተ፣
2.1. ጦርነቱን የሆነ ቦታ ማስቆም የማንችል ከሆነ እንደ አገር የማንቀጥልበት ሁኔታ ማጋጠሙ አይቀርም።
2.2. ጦርነቱ በሂደት የብሔር መልክ እየያዘ በመሔዱ ጉዳይ ከተገመተው በላይ ስፋትና ጥልቀት እንዲኖረው አድርጓል።
2.3. ከህውሃት ጋር የሚኖረው ትግል ዘርፈ ብዙና በአጭር ጊዜ የሚቋጭ እንደማይሆን መገንዘብ ያስፈልጋል።
2.4. ለሰላም ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር ለዓለም ማሳየት አለብን።
2.5. በጦርነቱ የተያዙ አካባቢዎችን ሙሉ በሙሉ ነፃ ካወጣን በኃላ ዋናውን ደጀናችንን ይዘን ስናበቃ ተገደን የገባንበትን ጦርነት ለመቋጨት ወደ ሰላማዊ ውይይት መግባት ይኖርብናል። ይህንን በማድረጋችን አሰፍስፈው ሊውጡን የተዘጋጁ የውጭ ኃይሎችን ማለዘብም ማሸነፍም እንችላለን።
2.6. እንኳንስ የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ህብረት መስራች አባል ሆነን ይቅርና ባንሆንም ጦርነቱን በውይይት መፍታት አለም አቀፍ መርሆ ነው።
2.7. ይህን አማራጭ መውሰድ ማለት የሚቆረቁሩ፣ የሚያም፣ የሚጐረብጥ ነገር የለም ማለት አይደለም።
እንግዲህ ድርድሩ ግድ ከሆነ  አንድ እግራችሁን አሸንጌ፣ ሌላ እግራችሁን ተከዜ አድርጋችሁ ተደራደሩ። ኮስተር በሉ። ከዚህ የባሰ ምን ይመጣል። የቆምነው እኮ ደምና አጥንት ላይ ነው
ጠንከር ብላችሁ ተደራደሩ!!
Filed in: Amharic