>
5:15 pm - Sunday May 1, 1250

ከመንገድ ላይ ታፍሰው የታሰሩ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ይፈቱ...!!!! (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ)

ከመንገድ ላይ ታፍሰው የታሰሩ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ይፈቱ…!!!!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

 እነ እስክንድር ነጋን ለመጠየቅ ወደ ቂሊንጦ በሄዱበት ከህግ አግባብ ውጭ በግፍ የታሰሩ  እስረኞች በአስቸኳይ ይፈቱ።
በቂሊንጦ እስር ቤት በግፍ የታሰሩ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮችን እስክንድር ነጋንና ስንታየሁ ቸኮልን ጠይቀው ሲመለሱ መንገድ ላይ ፎቶ ተነስታቹሃል በሚል ህዳር  16 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ አቃቂ ፖሊስ መምሪያ ተወስደው የታሰሩት 5 የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች እስካሁን አለመፈታታቸው አሳስቦናል።
1. አቶ ፋሲል ውሂብ
2. አቶ  ምትክ ካሳሁን
3. አቶ ዬርዳኖስ እንዳለ
4. አቶ ብሩክ ጫኔ
5. ወ/ሪት ሰላም ታደለ በአዲስ አበባ ፖሊስ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ26 ቀን በሕገወጥ መንገድ ታስረው ይገኛሉ።
ከዚህ በፊትም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማጥቂያን በማድረግ መንግስት ሕጉን ስለመጠቀሙ  በወቅቱም በእስረኞቹ ጉዳይ የተቃውሞ መግለጫ ማውጣቱን ጠቅሷል።
ቅሬታችንም ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቦርዱ እና ታስረው ለሚገኙበት ክ/ከተማ ኮማንድ ፖስት ብናቀርብም ብዙዎች እየተፈቱ ባሉበት ወቅት አባላቶቻችንና ደጋፊዎቻችን ሊፈቱ አልቻሉም ።
ይልቁንም ለቀናት ምግብ እንዳያገኙ ተከልክለው የነበረ ከመሆኑም በላይ፣  3ቱ እስረኞች 20 ካሬ በማትበልጥ ቦታ ውስጥ ከ120 የሚበልጡ እስረኞች ጋር መተኛት እና መቀመጥ እንዳይችሉ ተደርገው ኢሰብዓዊ በሆነ አያያዝ ታስረው ይገኛሉ ።
ባልደራስ አገራዊ ዓላማ ይዞ የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፣  ከታቀደለት አላማ ወጪ የፓርቲያችንን አባላት እና ደጋፊዎች ማጥቂያ ተደርጎ ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉ በእጅጉ እንቃወመዋለን ።
በሕጉ መሠረት ስልጣን የተሰጠው መርማሪ ቦርድም፣ የፓርቲውን ቅሬታ ቅድሚያ ሰጥቶ ባይመለከተው እንኳን የእስር ሁኔታቸውን ለመመርመር አለመፈለጉ በፖለቲካ ተፅዕኖ ስር እንደወደቀ ማሳያ አድርጎ ነው ፓርቲው የተረዳው ።
ባልደራስ መልካም ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር፣ በጦርነቱ እየተሳተፉ ላሉ እና ለተጎዱት ወገኖች ድጋፍ የሚውል ከፓርቲው ካዝና እና ደጋፊዎች ሚሊዮኖች የሚያወጣ እገዛ ማሰባሰብ በቻለበት አጋጣሚ ይሄ ችግር መፈጠሩ እና እስራቸው ተባብሶ ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ መያዛቸው፣ የመንግስትን ሃቀኝነት ጥያቄ ውስጥ ከማስገባ በስተቀር፣ አኩርፈን ለህዝባችን ማድረግ ከሚጠበቅብን እንድንጓተት ያደርገናል።
አሁንም ከሕግ ውጪ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ታስረው የሚገኙት አባላት እና ደጋፊዎቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ስንል ለአዲስ አበባ ኮማንድ ፖስት ጥሪ እናቀርባለን።
Filed in: Amharic