>

"አገራዊ የምክክር መድረኩ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ከአሸባሪው ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድር አይደለም....!!!" የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት 

“አገራዊ የምክክር መድረኩ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ከአሸባሪው ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድር አይደለም….!!!
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
(ኢ ፕ ድ)

አገራዊ የምክክር መድረክ ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ከአሸባሪው ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድር አይደለም” ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ አገራዊ የምክክር መድረኩ ሪፎርም ከተጀመረ ወዲህ  ዘላቂ የሠላም ግንባታ ለማምጣት የታሰበ ነው።
በአሁን ወቅት አንዳንድ ግለሰቦች ጉዳዩን በደንብ ባለመረዳታቸው ከአሸባሪው ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድር አድርገው ማሰባቸው ስህተት እንደሆነ ተናግረዋል።
አገራዊ የምክክር መደረኩ ሁሉን አካታች የሆነ ሠላምና አገረ መንግስት ግንባታ ላይ ያተኩረ እንደሆነና ለዚህም ነጻና ገለልተኛ ተቋም ለመመስረት በሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
መድረኩ እንዴትና በምን አይነት ሁኔታ እንደሚካሄድ የራሱ መመሪያ ተዘጋጅቶለት በነጻና ገለልተኛ ተቋም እንደሚመራም ጠቅሰዋል።
በአዲሱ ገረመው
Filed in: Amharic