>

ምክክር Vs ድርድር...!!! (ኤርሚያስ ለገሰ)

ምክክር Vs ድርድር…!!!
ኤርሚያስ ለገሰ

ሰሞኑን እያወዛገቡ ያሉትን ጉዳዮች ለማጣራት ብዙ ጥረት አድርጌያለሁ። በመጨረሻም የብልፅግና ፅህፈት ቤት የሚሰራ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ባደረሰኝ መልዕክት መሰረት የብልጽግና ስራ አስፈጻሚ ምክክርና ድርድርን ለይቶ ማስቀመጡን ነው።
፩. በምክክር መድረኩ  በሽብርተኝነት የተፈረጁ ቡድኖች አይሳተፉም። ለይስሙላ ከመንግስት ትጥቃችሁን ፈታችሁና ወንጀለኞችን አስረክባችሁ በምክክር መድረኩ ልትሳተፉ ትችላላችሁ የሚል ጥሪ ሊቀርብላቸው ይችላል።
፪. የድርድር መድረኩ ገዥው ፓርቲ በሚያቀርበው ቅድመ ሁኔታ ህውሃት ፍቃደኛ ከሆነ በሁለትዮሽ መድረክ ብቻ (ብልጽግና እና ሕውሃት) መጀመሪያ በሚስጥር (ከኢትዮጵያ ውጭ ሊሆን ይችላል) ፤ ቀጥሎም በይፋ ሊደረግ ይችላል። የውጭ አደራዳሪዎች ይፋዊውን ድርድር ሊመሩት ይችላሉ።
፫. ኢትዮ 360 ደርሶት የተወያየበትና በአሁን ሰዓት በሰፊው የተሰራጨው የፓወር ፓይንት ዶክመንት ምክክርን አሊያም ድርድርን ነጥሎ የተመለከተ ሳይሆን  የሰላም መምጣት የግድና የአገራዊ ሕልውናን ማረጋገጫ መሰረት መሆኑ መግባባት እንዲደረስበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በተጨማሪም በፓወር ፓይንት በቀረበው ኃሳብና ስትራቴጂክ አመራሩ (ስአኮ) በተወያየበት ሰነድ መካከል በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የጎላ ልዩነት እንደሌለ ሰምቻለሁ። ፓወር ፒይንቱ የተዘጋጀው በዛዲግ አብርሃ መሪነት በፓርቲው ፅህፈት ቤት መሆኑ ተነግሮኛል። ለምክክሩም ሆነ ለድርድሩ የሚቀርቡ ስትራቴጂክ አጀንዳዎች ተለይተው ያላለቁ በመሆኑ በሰነዶቹ ላይ እንዳልተካተቱና የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንዳልተወያዩበት ሰምቻለሁ።
Filed in: Amharic