>
5:13 pm - Thursday April 19, 8536

ህወሀት “ጦሬን አስወጣሁ!” አሜሪካኖቹም  “ ተደራደሩ “ በማለት ዲፋክቶ የፖለቲካ ጨዋታ ጀምሯል....!!! (ጸጋው መላኩ)

ህወሀት “ጦሬን አስወጣሁ!” አሜሪካኖቹም
 “ ተደራደሩ “ በማለት ዲፋክቶ የፖለቲካ ጨዋታ ጀምሯል….!!!
ጸጋው መላኩ

ህወሓት “ከአማራና ከአፋር ክልል ጦሬን አስወጥቻለሁ፤ ለመደራደር ዝግጁ ነኝ” ሲል አሜሪካኖቹም “ህወሓት ጦሩን ማስወጣቱ መልካም አጋጣሚ ነው፤ ተደራደሩ “በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡
 ለመሆኑ ህወሓት ጦሩን አስወጣ ማለት ፖለቲካዊ ትርጉሙ ምንድን  ነው ? ትግራይ ማለት እኮ የኢትዮጵያ አንዷ አካልና ክልል  እንጂ አንዲት የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆነች ሉዓላዊት ሀገር አይደለችም፡፡
 “ጦር አስወጥተናል ወይንም ባዕዳኑ  ሕወሓት ጦሩን አስወጥቷል  ፣ በማለት  ጉዳዩ  የሁለት ሉአላዊ ሀገራት ጦርነት የማስመሰል ሴራዎች በግልፅ  እየታዪ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስትም ቢሆን እንደዚህ አይነቶቹን አገላለፆች እንደቃላት ግድፈት መመልከት ያለበት ሆኖ አይታይም፡፡
ህወሓት ተደመሰሰ ወይንም ጦሩን አስወጣ ራሱን በራሱ  ያደረጃ አንድ  አማፂ ቡድን መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡  ትግራይንም ቢሆን በመያዣነት (Hosetage)  ያየዘ ፅንፈኛ የዘውጌ ብሄርተኛ ወይንም  Ethnocentric ቡድን ነው፡፡
ነገሩ ይህ ብቻ ሳይሆን  በአንድ ሀገር ውስጥ ያለው መከላከያ ሰራዊት አንድ ሆኖ ሳለ ህወሓት …“የትግራይ መከላከያ ሰራዊት ወይንም TDF” እያለ ሲጠራ ምዕራባዊያኑም ይሄንኑ አገላለፅ “ TDF”እያሉ  ሲቀባበሉት ነበር፡፡
ነገሩ በዚህ ሳያበቃ ህወሓት “የትግራይ ክልላዊ መንግስት የሚለውን”በህገ መንግስቱ ሳይቀር የተቀመጠውን  ስያሜ “… ክልላዊ….”  የሚለውን አንስቶ የትግራይ መንግስትም ማለት ከጀመረ ዋል አደር ብሏል፡፡
አሁን ደግሞ “ጦሬን አስወጣሁ” በማለት የዲፋክቶ የፖለቲካ ጨዋታ ጀምሯል፡፡ ህወሓትስ ፤ ህወሓት ነው፡፡ አሜሪካዊያኑም ሥለጦር ማስወጣት ማወራታቸው ግን ጉዳዩ ጥልቅ ሀገር የማፍረስ ሴራ መሆኑን በግልፅ የሚያመላክት ነው፡፡
Filed in: Amharic