>
5:21 pm - Monday July 20, 4218

"ድርድር የህወሓትን ስህተት በህወሀት ላይ መድገም....!!!" (ኦሀድ ቢንያም)

“ድርድር የህወሓትን ስህተት በህወሀት ላይ መድገም….!!!”
ኦሀድ ቢንያም

ህወሓት በነዚህ ሶስት አመታት የመርህ፣ የኃላፊነት፣ የራዕይ፣ የርእዮተአለም፣ የሃገር መውደድ፣ ህዝብን የማክበር እና ለትውልድ ግድ የማለት ችግሮች እንዳሉበት በግልጽ አሳይቶ ተሰባብሮ ወድቋል፤ ግን አልሞተም፤
ርዕዮተአለሙን የያዛቸው መንታ አማራጮች ሁለቱም ክፉ መሆናቸው ነው፤ በቅንነት የመጀመሪያውን ከተመለከትነው ርእዮተአለሙ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ይሆናል ያለው የማንነት ተኮር ፖለቲካ ራሱ እንኳን ፍትሓዊ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ሊያደርገው ሳይችል ቀርቶና ተወሳስቦ ውሉ የጠፋበት ልቃቂት ሆኗል፡፡ ራሱን ማንነታዊ ኢምፔሪያሊዝም (Ethnic Imperialism) ወይም ደግሞ ሁሉም የአገሪቷ ሁለንተናዊ ምንነት ለአንድ ገዢ ብሔር እንዲሆን ያደረገ አካሄድን ተከትሎ ነበር፤ (ይህን እንግዲህ ሆኖ ብሎ ያድርገው ወይም ያልተጠበቀው መዘዝ /ramifications/ ይሁን የሚያውቀው ራሱ ነው፡፡) በጥቅሉ ግን በጥላቻ ሃሳቦች የተቀመመው የህወሓት ማንነት ተኮር ፖሊሲ አገሪቷን የከፋ ችግር ውስጥ ከመክተት እና በድንበር ልዩነቶች እንደ የውጭ ጠላት የሚተያዩና የሚተላለቁ ክልሎች ከመፍጠር ውጪ የጠቀመው ነገር የለም፤ በመጨረሻም የራሱን ክልል ትግራይን የአጎራባቾቿ ክፉ ጠላት አድርጎ ወደ ከፋ እና ለመሻር ዘመናት የሚጠይቅ ቁስል አስቀምጦ አልፏል፡፤
በክፉ መልኩ እና መጨረሻ ላይ በተግባር እንዳረጋገጠው ከሆነ ኢትዮጵያን በትኖ የመከራ ማሳ ማድረግ ነበር፤ ደግነቱ አልተሳካም፤ ስለ ራዕይ ካነሳን ደግሞ ዘመን የሚሻገር አልሆነም፤ የህወሃት ራዕይ ራሱን ችሎ የሚቆም ሳይሆን በጠመንጃ ተደግፎ በርካታ ባለራዕዮችን እየበላ የኖረ፣ ማኘክ ከሚችለው በላይ የጎረሰ ድርጅት ሊያሳካው የማይችል ከንቱ የወድመት ፍጻሜን በውስጡ አዝሎ ሲያሳድግ የኖረ ራዕይ ነው፡፡ ራዕዩ ፍጻሜውን ለመቀበል ሲያስቸግርም አፈሙዝ አስፈላጊ ወደሚሆንበት አማራጭ ያስገባ ችግር ሆኖ ተከስቷል፡፡
ሕዝብን እና ህይወትን በማክበር ደረጃ ህወሓት ምን እንደሆነ ከማይካድራ እስከ ጋላኮማ ከሰሜን ዕዝ ጥቃት እስከ ሰሜን ሸዋ ድረስ ባደረጋቸው ኦፕሬሽኖች ማንነቱን አሳይቷል፤ ህወሓት ለሕዝብ ክብር ለህይወት ዋጋ የሌለው የበግ ለምድ ለብሶ የኖረ አስመሳይ ተኩላ መሆኑን ምስክር በማያስፈልገው ሁኔታ አሳይቶናል፤ የ110 ሚሊዮን ሕዝቦች ቤትና መኖሪያ የሆነች አገርን አፍርሶ በትኖና የራሱን ኢምፓየር የማስቀጠል ፍላጉቱ በገሃድ የወጣው ድርጅት፣ ደንበኛ ወንበዴ መሆኑን አስመስክሯል፡፡
ስለሃገር መውደድ ከተነሳ የ27 አመታት አካሄዱና አጨራረሱ ግልጽ የሆነ ማንነቱን አሳይተውናል፤ ስለትውልድ የማሰብን ጉዳይ አሰመልክቶ ምንም ግድ የማይለው ድርጅት መሆኑን የትግራይ ወጣቶችንና የአማራ ወጣቶችን በአፈሙዝ እንዲተያዩ እና ያለምንም በቂ ብቃትና ልምምድ ወደ ጦርነት የማገዳቸው የክልሉ ወጣቶች አሃዝና አቅም በቂ ማሳያ ነው፡፡
ህወሓት ፖለቲካን ያለመርህ ሲያካሂድ የኖረ ድርጅት ነው፤ ከማንም ጋር በምንም ለዘላቂ ሁኔታ ተማምኖና ተስማምቶ መሄድ የማይችል የአርቆ የማየት ችግር ያለበት ነው፡፡ ይህም አካሄዱ አንድም የውጭ ወዳጅም ሆነ አጎራባች ወዳጅ ማፍራት ያልቻለ፣ ክልሉን በአጭር ጊዜ ውስጥ የመከራ ደሴት ያደረገ የፖለቲካ አካሄድ እየተከተለ እንደነበረ ያላስተዋለ ጭፍን ድርጅት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ሲጨነቅ እየተደራደረ ሲጠግብ እየተበተ የትግራይን ሕዝብ ወገን አሳጥቶ በዘላቂ ጠላቶች የተከበበ ሆኖ እንዲቀር የሚያደርግ ፖሊሲ አይሉት የቃላጉባኤ ማራቶን ሲመራ የኖረ አሳፋሪ ድርጅት ነው፡፡
ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የአመራሩ ክፍል ኢትዮጵያን የመበተንና እርስ በርሱ ወደተጣላ የጦርነት ቀጠና ለመለወጥ ያላቸውን እቅድ በድፍረት የሚናገሩበትን ሁኔታ ምንነት መገንዘብ ባቃታቸው እኩዮች የተሞላ መሆኑን እና ራሱን እያጸዳ የመሄድአቅሙን አፍቅሮተ-ንዋይና አፍቅሮተ-ሥልጣን የቀሙት ደካማ ድርጅት ሆኖ ተገኝቷል፡፡
እናም ህወሓት ለድርድር እንዲመች ብዬ ነው ከአማራና አፋር ክልሎች የወጣሁት፣ የወልቃይትንም ጉዳይ ያላነሳሁት እያለ እየተመጻደቀብን ነው፤ ለማያውቅሽ ታጠኚ፤ ከህወሃት ጋር ድርድር የራሱን ስህተት በራሱ ላይ መድገም ነው፡፡
ከባድመ ጦርነት በኋላ ህወሓት ከሰራቸውና ለውድቀቱም ለፀፀቱም ምክንያት ከሆኑት ነገሮች አንዱ በኤርትራና በፕሬዚደንቷ ላይ የወሰደው አቋም ነው፡፡ ከአላስፈላጊው የባድመ ጦርነት በኋላ ድርጅቱ በጉሮ ወሸባዬዎቹ ቀናት “ኤርትራንን ሻዕቢያን አከርካሪያቸውን ሰብሬያቸዋለሁ፤” ከዚህ በኋላ ማንም አይችለኝም በሚል ትዕቢት ጦርነቱን በድንገት አቁሞ ወደኋላ አፈገፈገ፤ ምንአልባት በነበረው ወታደራዊ አቅም አስመራ ገብቶ የ ኤርትራን መንግስት አፍርሶ አዲስ መንግስት ፈጥሮ ሊመጣ የሚችልበት እና ኤርትራ ሳትረጋጋ እንድትቆይ ማድረግ የሚችልበት አቅም ነበረው፡፡ ያለኃጢያታቸው ኢሳያስን የሚያክል ስትራቴጂስት ጠላት አድርጎ ትቶ መውጣቱ ከ22 አመታት በኋላ የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ካምፖችን ባጠቃበት ማግስት የኤርትራ ወታደሮች አዲግራት ከተፍ ሲሉ ምን ይሰማው ይሆን? እሱን አያድርገኝ ከማለት ውጪ ምንስ ሊባል ይችላል?
ያኔ አቅም በነበረው ወቅት (መላምታዊ እንሁንና) ኢሳያስ አፈወርቂን የማስወገድ ስትራቴጂ እርምጃ ወስዶ ቢሆን የኤርትራ ወታደሮች በምዕራብ ትግራይ በኩል አንድም የሱ ኃይል ወደሱዳን እንዳይገናኝ የሚያደርገው ደንቀራ የመፈጠሩን ዕድል ያጠብለት ይሆን? ጦርነቱ ሲበረታ መውጫ መግቢያ ሲጠፋ “ወጭት ጥዶ” እያለቀሰ ባልደቆሰው ጨው ከመንገብገብ ውጭ ለአጽናኝ በማይመች ሁኔታ እንደጻድቃን ገብረኪዳን በከዘራ እየኳተነ ራሱን አያገኘውም ነበር፡፡
ህወሓት በአሁኑ ሰዓት የተወጋ አውሬ ሆኗል፤ ወደ ዋሻው ተመልሶ በድርድር ክኒኖች ራሱን ለማከም ተጋድሞ ዉሃ ስጡኝ እያለ ነው፡፡ ፌዴራል መንግስት የራሱን የህወሓትን ስህተት በህወሓት ላይ የሚደግመው አይመስለኝም፤ ነገር ግን ካደረገው የተኣማኒነት ችግር ያለበት ድርጅት ከቁስሉ አገግሞ ሲወጣ “ያኔ ነበር መጨረስ የነበረብን፤” የሚያስብል ጸጸት ውስጥ አገሪቷን እና ትውልድን ሊከት የሚችል ችግር መፈጠሩ አይቀርም፤

Filed in: Amharic