>

"አከርካሪህ የተሰበረው በድሮን አይደለም፤በተጋድሎ መንፈስ እንጅ...!!!" (መስቀሉ አየለ)

“አከርካሪህ የተሰበረው በድሮን አይደለም፤በተጋድሎ መንፈስ እንጅ…!!!”
(መስቀሉ አየለ)

 

*….. ከምእራቡ አለም ሚዲያዎች እስከ ትግሬ ወራሪዎች ድረስ ሰሞኑን ሲያላምጡ ውለው የሚያድሩት የድሮንን ነገር መሆኑ  ወራሪዎቹ “የተሸነፍነው በድሮን ሃይል ብቻ ነው” የሚል ትርክት ይዘው ብቅ ማለታቸው ማለፊያ ነው።
አንድም ለሶስት አስርተ ዓመታት ያህልግዜ “አማራ ሽንታም ነው” , “ገና ቀሚስ አልብሰን የወጥ ቤታችን ሰራተኛ ነው የምናደርገው” ወ.ዘ.ተ. በሚል በድቡሽት መሬት ላይ የገነቡትን የህዝባቸውን አጓጉል የጀብደኝነት ስሜት ጠብቆ ለማቆየት፤
አንድም “ተዋግቶ ማሸነፍ የእኛ እና የእኛ ብቻ የሆነ የማይሸጥ፣ የማይለወጥ፣ የማይወረስ፣ የማይኮረጅ የግላችንና የግላችን ማንነት ነው” ለማለት፣
አንድም ሌላውን ” ፈሪ፣ ቀሚስ ለባሽ” ለማለት መሆኑ የሚያጠያቅ አይደለም
ነገር ግን የበቀለውን ሁሉ ሳያላምጡ የሚወጡ የእኛ አገር ጦማሪና አክቲቪስቶች ሳይቀሩ በተቀደደላቸው ቦይ እየፈሰሱ እነርሱም ተደርበው ሁሉን ነገር “በድሮን ብቻ የተገኘ ድል” አድርገው ሲበጠረቁ የሚውሉት
ለመሆኑ ጦርነቱ የኮምፒወተር ጌም ነው እንዴ?
ማሸነፍስ ለእኛ አዲስ ነገር ነው እንዴ ?
ከኦሪት ዘፍጥት የጀመረው የጀግንነት ታሪካችን የተቀዳው በድሮን ቴክኖሎጅ ነው እንዴ?
የባንዳስ መዋረድ ዛሬ የመጣ ነው እንዴ?
በእያንዳንዷ የከፍታ ነጥብ ገዥ መሬት ላይ ዋጋ ሳትከፍል፣ ቦምብ ጨብጠህ ምሽግ ሳትደረምስ፣ በጨበጣ ሳትሞሻለቅ፣ ከድሮን ብቻ ተኩሰህ የድል ባለቤት የምትሆነው  ወያኔ አሰልፎ ለመጣው ወደ ሚሊዮን ለሚጠጋ የተባይ ድሮኖቹ ሮኬት በነፍስ የሚተኩሱት ሮኬት ማለት እንዲሁ በካቦርት ቁልፍ ተቀይሮ የሚመጣ ርካሽ ነገር  ይመስለሃል?
ወዳጀ፤ ባጠቃላይ በማንኛውም ጦርነት ውስጥ በጥቅሉ የአርሃይል ሲባል ድጋፍ ሰጭ እንጅ ዋነኛው ተዋናይ አይደለም፤ በሎጅስቲክ አቅርቦት ላይ እክል በመፍጠርና ካምፖችንና የተመረጡ ኢላማችን በመደምሰስ በወገን ጦር ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በመቀነስ ጦርነቱን ሳይራዘም ባነሰ ግዜ ለመጨረስ ማስቻል እንጅ እንደ ተራ ወታደር ወርዶ ሁሉንም ነገር መሸፈን አይደለም፤
 ያ ቢሆን ኖሮ እንደአሜሪካና ሳውዲአረቢያ የመስሉት ዲታ አገራት አንድም ወታደር ሳያስፈልጋቸው ከቪየትናም እስከ አፍጋኒስታን ከሶሪያ እስከ የመን “አሸባሪ”ያሉዋቸውን ሁሉ አከርካሪ ሰብረው የድሉን ዋንጫ ለብቻቸው ያነሱት ነበር። ነገር ግን አልሆነም፤አይሆንምም።
Filed in: Amharic