>

ነፃ ያልወጡት ግፉአንን ነፃ የማውጣት ውለታም ግዴታም አለብን....!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

ነፃ ያልወጡት ግፉአንን ነፃ የማውጣት ውለታም ግዴታም አለብን….!!!
ጌታቸው ሽፈራው

*… ለአብነት ያህል የትግሬ ወራሪ ድንበሩን አልፎ የመጀመርያውን ሰቆቃ የፈፀመው ዛታ፣ ኦፍላ፣ መሆኒ፣ ጨርጨርና አላማጣ አካባቢ ነው። ገና ድንበሩን እንዳለፈ 58 የመሆኒ ከተማና አካባቢው ሙስሊሞችን ፈጅቷል።  “ሸማኔ መጥፋት አለበት” እያሉ እየጨፈሩ በየቤታቸው እየገቡ እየጎተቱ አውጥተው ጨፍጭፈዋቸዋል። ቤታቸው ተቃጥሏል። 
የትግሬ ወራሪ እስከ ሸዋሮቢት፣ ጋይንትና ጭና ድረስ በርካታ ጭፍጨፋና ውድመት አድርሷል። የወልዲያና የቆቦ ሕዝብ በጭካኔ ውስጥ ከርሟል። ጭፍጨፋውና ውድመቱ እንዳለ ሆኖ አብዛኛው ቢያንስ ከዛ ጭካኔ ወጥቷል። ግን እስካሁን ነፃ ያልወጡ ግፉአን ብዙ ናቸው።
ለአብነት ያህል የትግሬ ወራሪ ድንበሩን አልፎ የመጀመርያውን ሰቆቃ የፈፀመው ዛታ፣ ኦፍላ፣ መሆኒ፣ ጨርጨርና አላማጣ አካባቢ ነው። ገና ድንበሩን እንዳለፈ 58 የመሆኒ ከተማና አካባቢው ሙስሊሞችን ፈጅቷል። እንግዲህ ይሄ ገና በገባ ሰሞን መረጃ ነው። ከዛ በኋላ የፈፀመው ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። የአካባቢው ሙስሊሞች በሽመና ስራ ይተዳደራሉ። ይሄን እንደ መጥፎ ቆጥረው “ሸማኔ መጥፋት አለበት” እያሉ እየጨፈሩ በየቤታቸው እየገቡ እየጎተቱ አውጥተው ጨፍጭፈዋቸዋል። ቤታቸው ተቃጥሏል። እነዚህ ግፉአን ከዛ በኋላ፣ የትግሬ ወራሪ ጊዜ ሲያገኝ ምን ሊያደርጋቸው እንደሚችል ማሰብ ይዘገንናል። ትግራይ ውስጥ ሙስሊሞች በሽመና ይተዳደራሉ። ግን አልጨፈጨፏቸውም። የጨፈጨፏቸው የመሆኒ ሙስሊሞችን ነው። መሆኒ አሁንም በጠላት ስር ነው።  “ወደ ትግራይ ላለመግባት” የሚለው መግለጫ እነዚህን ግፉአን አይጨምርም። መጀመርያም መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ወጥቶ ከመሆኒ ወዲያ ነው የተቀመጠው። የትግሬ ወራሪም አማራነታቸውን ሙስሊምነታቸውን ሰበብ አድርጎ፣ አማራ ክልል ላይ እንደፈፀመው ሁሉ ሲፈፅም መከላከያን ተቀብላችኋል የሚል ተጨማሪ ማጥቂያ አክሎባቸዋል።
በተመሳሳይ አሁን በጠላት ስር ባሉት የራያና የዋግኸምራ አካባቢዎች ሰራዊቱን ተቀብለው፣ ከሰራዊቱ ጋር ሆነው የታገሉ ብዙ ሰዎች ዋጋ ከፍለዋል። የዞብል ሰንሰለታማ ተራራዎች ላይ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል። ይሁንና ቤተሰቦቻቸው በጠላት እጅ ወድቀው ተገድለዋል። ተሰቃይተዋል። ከመንግስት ንክኪ አለው፣ ለመከላከያ ምግብ ሰጥቷል እየተባለ ተሰቃይቷል። ተገድሏል። ወጣቶች ተረሽነዋል።
የትግሬ ወራሪ  ባለፉት ወራት የአርሶ አደሩን ሰብል ሳይቀር እየጫነ ወስዷል። አርሶ አደሩ በጠላት የተፈፀመውን በደል አልቀበልም ብሎ ዱር ቤቴ ካለ ቆይቷል። መንገድ እየዘጋ ጠላትን አጥቅቷል። ይህ ወገናችን መከላከያ ሰራዊት እየመጣ ነው ሲባል ትልቅ ተስፋ አድርጎ ቆይቷል። ትናንት ሰራዊቱ የያዘውን ይዞ ይቆያል የተባለው ውሳኔ ምክንያቶች ይኖሩታል። ይሁንና ነፃ ያልወጡ፣ ለመከላከያ ሰራዊት ሽፋን ሆነው ከጥቃት ከልለው ያስወጡ፣ መከላከያን አግዛችኋል ተብለው የተሰቃዩ፣ ከመንግስት ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው በደል የተፈፀመባቸው በርካታ ግፉአን ከፊት እንዳሉ ማመን ግን የግድ ይላል።
ሰራዊቱ የያዘውን ይዞ ይቁም የተባለበት ፊት ለፊት የግራካሱ ስልታዊ ተራራ አለ። ጠላት ለአንድ ቀንም ቢሆን ለማደር ምሽግ ሲቆፍር እንደሚውል ይታወቃል። ጊዜ ከተሰጠው ግራካሱ ላይ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ግልፅ ነው። ቆቦን ጨምሮ ብዙ ከተሞች በመድፍ የቅርብ ርቀት ናቸው። ጠላት  እንደ አዲስ ቅስቀሳ ላይ ነው።
በሌላ በኩል  መከላከያ ከቆመበት ፊት ለፊት እጅግ በርካታ ግፍ እየተፈፀመባቸው ያሉ ግፉአንን መርሳት የለብንም። መከላከያ እነዚህን ወገኖች ነፃ የማውጣት ውለታም ግዴታም አለበት። ሰራዊቱ በተለያየ ምክንያት ወደፊት ባይሄድ ግን አማራው ወገኖቹን ነፃ የማውጣት ግዴታ አለበት። ከሌሎች አካባቢዎች ተቀጥቅጦ የወጣ ቡድን አሁንም ወገኖቻችንን የበቀል ማብረጃ እንደሚያደርጋቸው ግልፅ ነው። ይህን ሁሉ ሰቆቃ ያየው አማራ ሌላ አንድ ተጨማሪ ሴት እንድደፈር፣ ሌላ አንድ ተጨማሪ ወጣት እንዲረሸን መፍቀድ የለበትም።
መንግስትም ሰራዊቱም ንፁሃንን ከአሸባሪው ነፃ የማውጣት ግዴታም ውለታም አለባቸው። ቀድሞም የሚጠሏቸው ቢሆንም ሰራዊቱን አገዛችሁ ተብለው ዋጋ ከፍለዋል። የመንግስት ደጋፊ ናችሁ ብለው ስቃይ ደርሶባቸዋል። መንግስት እንደባለፈው ተዘናግቶ፣ ጦርነቱ ከአዲስ አበባ ስለራቀ የግፉአን ሰቆቃ አልሰማው ብሎ ዝም ካለ አማራው ወገኖቹን ለጠላት አስይዞ የሚቀመጥበት ምንም ምክንያት የለም።  መጀመርያውንም መንግስት ጦርነቱን ትቶ ሌላ አጀንዳ ላይ ባተኮረበት “ክተት፣ መክት” እያለ ቀድሞ የከረመው አማራው ነው። አሁን መንግስት ወደኋላ ወደፊት ቢል አማራው በራሱ ተማምኖ፣ ሳይዘናጋ፣ ሴራ ተሰራብኝ ወዘተ ብሎ ሳይቆዝም ወገኖቹን ነፃ የማውጣት ግዴታ አለበት። ለዚህ የሚበቃ የስነ ልቦና ዝግጅት ግድ ይላል። ለዚህ የሚያበቃ ወታደራዊ ዝግጅት ያስፈልገዋል። መንግስት ለዜጎቹ መታመን ካልቻለ አማራው በራሱ መተማመን አለበት።
Filed in: Amharic