>
5:33 pm - Monday December 5, 8721

"አገራዊ ምክክሩ"  ና ነውረኛው ብአዴን....!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

አገራዊ ምክክሩ”  ና ነውረኛው ብአዴን….!!!

አቻምየለህ ታምሩ

ብአዴን የሚባለው የፋሽስት ወያኔ ነውረኛ ድርጀት ልክ እንደ ፈጣሪው ፋሽስት ወያኔ ነውር ጌጡ የሆነ ድርጅት ነው። ከሰባት ዓመት በፊት “እነ ነውር ጌጡ” በሚል ርዕስ በጻፍሑት ዘለግ ያለ ጽሑፍ ብአዴን በነውረኛነት የፋሽስት ወያኔ ታናሽ ወንድም መሆኑንና እነ ነውር ጌጡ የሚለው አገላለጽም ፋሽስት ወያኔን ብቻ ሳይሆን ብአዴን የሚባለውን የፋሽስት ወያኔ ነውረኛ ድርጅት እንደሚያካትት አውስቼ ነበር። ይህ ነውር ጌጡ የሆነ ዘግናኝ ፍጥረት የየብሔር፣ የየብሔረሰብ እና የየሕዝባቸው ጠባቂ ከሆኑ አክራሪ ብሔርተኛ ድርጅቶች እኩል ራሱን እንደ አማራ ሕዝብ ጠባቂ በመቁጠር ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የተባሉትን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ ተቀዳሚ አላማው ነው የተባለለት “አገራዊ ምክክር” መድረክ ተሳታፊ ለመሆን በየደረጃው የጎለታቸውን ግብረበላዎቹን [አመራሮቹን ላለማለት ነው] “እያወያየ” ነው አሉ። በዓለም ላይ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ ውድመትና ተነግሮ የማያልቅ እልቂት እንዲደርስበት ያደረገውን ሕዝብ የምወክል እኔ ነኝ የሚል እንደ ብአዴን ሰዎች አይነት ዘግናኝ ፍጥረት በዓለም ላይ ታይቶና ተሰምቶ ያውቅ ይሆን?

Filed in: Amharic