>

"ከኢትዮጵያ ሌላ ከAGOA የንግድ ውል እንድትወጣ ተወሰነ....!!!" DW

“ከኢትዮጵያ ሌላ ከAGOA የንግድ ውል እንድትወጣ ተወሰነ….!!!”
DW

በዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያ ከአፍሪቃ እደገት ተጠቃሚነት ደንብ በእንግሊዝኛው ምህጻር AGOA የንግድ ውል እንድትወጣ ወሰነ። ከኢትዮጵያ ሌላ ከAGOA ተጠቃሚነት ጊኒ እና ማሊም መታገዳቸውን ፕሬዝደንቱ ትናንት ይፋ አድርገዋል። ኢትዮጵያ ከዚህ የንግድ ውል ተጠቃሚነቷ እንዳይታገድ የተለያዩ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ዎርልድ ትሬድ ኢንሳይድ የድረገጽ የመረጃ ምንጭ አመልክቷል። የባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያ፣ ጊኒ እና ማሊን ከAGOA ያገደለው ሃገራቱ በውሉ አንቀጽ 506(a) መስፈርት አታሟላም በሚል ነው። ከመጪው ጎርጎሪዮሳዊ አዲስ ዓመት 2022 መባቻ ጀምሮ ውሳኔው ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። AGOA የአፍሪቃ ሃገራት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የጨርቃ ጨርቅ ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ የሚያስገቡበት የንግድ ስምምነት ነው። እንዲህ ያለው ውሳኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ200 ሺህ በላይ በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ የሚሠሩ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን ወገኖች ሕይወት ሊጎዳ እንደሚችል ዘገባዎች ያመለክታሉ።

Filed in: Amharic