>

የዐብይ አሕመድ ተውኔት፣ ገቢር ዐራት (መስፍን አረጋ)

የዐብይ አሕመድ ተውኔት፣ ገቢር ዐራት

 

መስፍን አረጋ


ወያኔ ደብረብርሃን ገባሁ አልገባሁ እያለች በምታስፈራራበት ጊዜ ‹‹የዐብይ አሕመድ የድርድር ተውኔትና የደመቀ መኮንን ሚና›› በሚል ርዕስ ካንድ ወር በፊት በጦመርኩት ጦማር ላይ፣ ዐብይ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚተውነውን ተውኔት በሶስት ገቢሮች ከፍየ የሚከተለውን ጽፌ ነበር፡፡ 

 

  • ገቢር አንድ

 

በመጀመርያ ወያኔን መጣሁብሽ፣ ልመጣብሽ ነው እያለ በባዶ ዛቻ በማስፈራራት ውስጥ ለውስጥ ቆስቁሶ፣ በሰሜን እዝ የሚገኙትን የአማራ የጦር መኮንኖች እንድትጨፈጭፍ አነሳሳት፡፡  በዚህም የአማራ ሕዝብ አያሌ የጦር መሪወቹን እንዲያጣ አደረገ፡፡  ቀጠለና ደግሞ የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በከፍተኛ መስዋእትነት ወያኔን ከሞት አፋፍ እስኪያደርሳት ድረስ አድፍጦ ከጠበቀ በኋላ፣ ሕግ በማስከበር ሰበብ በትግራይ ላይ ዘመቶ ትግራይን በሻሻ አደረጋት፡፡  ትግራይን በሻሻ ካደረገ በኋላ ደግሞ ትግራይ ላይ በሾማቸው ብልጽግናወች አማካኝነት ከወያኔ ጋር ውስጥ ለውስጥ እየተገናኘ፣ ወያኔ እስከ ደብረብርሃን ድረስ በመውረር የአማራን ክልል በሻሻ እንድታደርገው ተስማማ፡፡  በስምምነቱ መሠረት ደግሞ ቃሉን አክብሮ ወያኔ ደብረብርሃን ደጃፍ እስከምትደርስ ድረስ ማድረግ የሚችለውን እገዛ ሁሉ አደረገላት፡፡  የአማራ ክልልም እንደ ትግራይ ክልል በሻሻ ሆነ፡፡ 

 

  • ገቢር ሁለት

 

እባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ እንዲሉ፣ አጭበርባሪው ዐብይ አሕመድ የወያኔን አጭበርባሪነት በደንብ ያውቃል፡፡  ስለዚህም፣ ዐብይ አሕመድን ያስጨነቀው አንድና አንድ ነገር ብቻ ነበር፡፡   እሱም እኔ ቃሌን አክብሬ ወያኔን ደብረብርሃን እንዳደረስኳት፣ እሷም ቃሏን አክብራ ደብረብርሃንን ከመዘበረች በኋላ እዛው ትቆማለች ወይስ ቃሏን በልታ ወደ ኦሮምያ ትገፋለች የሚለው ጭንቀቱ ነበር፡፡  ዐብይ አሕመድ ከወያኔ ጋረ መደራደር የሚፈልገው ይህን ጭንቀቱን ለማስወገድ ሲል ብቻ ነው፡፡  በሌላ አባባል ዐብይ አሕመድ ድርድር ሲል፣ እንደራደር ማለቱ ሳይሆን አስቀድመን በሕቡዕ የተዋዋልነውን ውል ላለማፍረስ በዓለም ሕዝብ ፊት በይፋ ቃል እንግባ ማለቱ ነው፡፡  ወያኔና ኦነግ ሁለቱም ጀቦች (አንዱ የቀን ጅብ ሌላው የጠራራ ጅብ) ስለሆኑና ስለማይተማመኑ ጎን ለጎን እንጅ ፊትና ኋላ አይሄዱም፡፡ 

 

  • ገቢር ሦስት 

 

ወያኔ ቃሏን ካከበረችና ከደብረብርሃን ካላለፈች በወረራ ያገኘችውን ሁሉ በስምምነት መልክ ሙሉ በሙሉ ሊያጸድቅላት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነው፡፡  ቃሏን ካላከበረችና ወደ አዲስ አበባ እገፋለሁ ብላ አሻፈረኝ ካለች ግን፣ በተለያየ ሻጥር እጅ እግሩን አስሮ አላላውስ፣ አላንቀሳቅስ ያለውን የአማራን ሕዘባዊ ኃይል መጠነኛ ነጻነት ይሰጠውና ወያኔን ድባቅ እንዲመታት ያደርጋል፡፡  

በዚህ ጦማር ላይ ደግሞ ባሁኑ ወቅት ዐብይ አሕመድ እየተወነው ስላለው ስለ ገቢር ዐራት በጥቂት አወሳለሁ፡፡

 

  • ገቢር ዐራት

 

እንዳያያዟ ከሆነ ወያኔ ያቀደችው ከዐብይ አሕመድ ጋር በሕቡዕ የተዋዋለችውን ውል በግላጭ አፍርሳ፣ ደብረብርሃንን መዝብራ አልፋ፣ አዲሳባ ገብታ ሁሉን በጇ በደጀዋ ማድረግ ነበር፡፡  ይህን አያያዟን በተክክል የተረዳው፣ ለስልጣኑ ሲል ማናቸውንም ነገር ለማድረግ ቅንጣት የማያመነታው ዐብይ አሕመድ ደግሞ፣ ከራሱ በላይ ለሚያፈቅረው ለስልጣኑ ሲል ከፍተኛ ሥጋት አደረበት፡፡   በዚህም ምክኒያት በአማራ ኃይሎች (በተለይም ደግሞ በፋኖ) ላይ የሚሻጥረውን ሻጥር በመጠኑም ቢሆን ጋብ ለማድረግ ሳይወድ በግድ ተገደደ፡፡   የአማራ ኃይሎች ሻጥር ካልተሻጠረባቸው ባጭር ጊዜ ውስጥ ወያኔን ገርፈው እንደሚያባረሯት በርግጠኝነት ስለሚያውቅ ደግሞ፣ በነሱ መስዋዕትነት የሚገኘውን ድል፣ በሱ አዝማችነት የተገኘ ድል ለማስመሰል እዘምታለሁ፣ ዘምቻለሁ በማለት በሰፊው እያስወራ ቱልቱላውን ነፋ፡፡  የአማራ ኃይሎችም ወያኔን እየሸነቆጡ እስከ አለማጣ ድረስ ነዷት፡፡    

ዐብይ አሕመድም በአማራ ኃይሎች ላይ የሚሻጥረውን ሻጥር ለጊዜው ጋብ በማድረግ ብቻ፣ ሁለት ታላላቅ ጥቅሞችን አገኘ፡፡  የመጀመርያው ጥቅም ስልጣኑን ልትመነጭቀው ዙርያውን አሰፍስፋ የነበረችው ወያኔ፣ በአማራ ኃይሎች ከፍተኛ መስዋእትነት ተጠራርጋ፣ ለስልጣኑ እስከማታሰጋበት ርቀት ድረስ እንድትርቅ መደረጓ ነው፡፡  

ሁለተኛው ጥቅሙ ደግሞ በወጉ እንዳይታጠቁ የተሻጠረባቸው የአማራ ኃይሎች በለበንና በውጅግራ ያገኙትን አንጸባራቂ ድል ሰርቆ፣ በድሮን ያገኘው የራሱ ድል አስመስሎ አቅርቦ፣ ጀግና ለመባል የሞከረው ሙከራ በማይናቅ ደረጃ የተሳካለት መሆኑ ነው፡፡  በዚህ ረገድ ደግሞ ዐማራ መስለው ዐማራን ለማስበላት ቆርጠው የተነሱት፣ ዐማራ የለም የሚለው የአንዳርጋቸው ጽጌ ቅጥቅጦች የሆኑት፣ ድነታችንም ሞታችንም በዐብይ አሕመድና በዐብይ አሕመድ ብቻ ነው ያሉት፣ ኢሳቶችና ዜና ቲዮቦች የዋሉለትን ከፍተኛ ወለታ መቸም መርሳት የለበትም፡፡  ዐብይ አሕመድ ግን ያመኑትን ሁሉ በደንደሳቸው የሚጥል ሌንጮ ፈረስ ስለሆነ፣ እነዚህን ሆድአደሮች ፀራማራ ቢሆኑም ኦሮሞ ባለመሆናቸው ብቻ አላምጦ ሲጨርስ አንቅሮ እንደሚተፋቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡      

ዐብይ አሕመድ የጭቆናን ምንነት በቅጡ ሊረዳ በማይችልበት ለጋ እድሜው “ያማራ ጨቋኞችን” ለመታገል ጫካ ገብቶ የወያኔን ጡት እየጠባ ባማራ ጥላቻ ተመርዞ፣ በወያኔ እኩይ ባሕርያት ተሰቅዞ ያደገ፣ አማራዊ ናት የሚላትን ጦቢያን አፈራርሶ በሷ መቃብር ላይ የኦሮሞ አጼጌ (Oromo empire) ለመመሥረት ቆርጦ የተነሳ ኦነጋዊ አውሬ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ ወያኔን የሚጠላት በስልጣኑ ስትመጣበትና ከመጣችበት እንጅ፣ በአማራ ጥላቻዋ ሲወዳት ዓይን የለውም፡፡  ስለዚህም የዐብይ አሕመድ እቅድ፣ ወያኔ የኦነግን የበላይነት ተቀብላ፣ በሱ (ማለትም በዐብይ አሕመድ) ሥር ሁና፣ ለስልጣኑ ሳታሰጋ፣ ከአማራ ጋር ተጠግታ አማራን ዘላለም እያስለቀሰች የምትኖር የአጋም እሾህ እንድትሆንለት እንጅ እንድትጠፋ አይደለም፡፡  

   ስለዚህም ፋኖወች ወያኔን እየሳደዱ ወደ አላማጣ ሲቃረቡ፣ ዐብይ አሕመድ ደግሞ ወያኔ ከናካቴው ልትጠፋብኝ ነው የሚል ከፍተኛ ሥጋት አደረበት፡፡  በዚህም ምክኒያት ወያኔን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የማጥፋት ዘመቻው በትክክል ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ ጦርነቱ ቁሟል የሚል መግለጫ ተሸቀዳድሞ አወጣ፡፡  ወያኔን ያጠፋብኛል ብሎ አለመጠን በሚፈራው በፋኖ ላይ ደግሞ መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፈተ፡፡  

ዐብይ አሕመድ የአማራ ሕዝብ መሪር ጠላቶች ከሆኑት ከወያኔና ከኦነግ ከሁለቱም የተቀዳ የሁለት ሰይጣን ነው፡፡  ይህ የሁለት ሰይጣን የጦቢያ መሪ እስከሆነ ድረስ ደግሞ፣ የኣማራ ሕዝብ መቸም ቢሆን ሰላም አያገኝም፣ እንደውም ከናካቴው ጨርሶ ሊጠፋ፣ ማለትም እንደ ሕዝብ ሕልውናውን ሊያጣ ይችላል፡፡  ስለዚህም፣ የአማራ ሕዝብ ለሕልውናው ሲል ማድረግ ያለበትን ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡  አልሞት ባይ ተጋዳይነት ደግሞ በምድር አስከብሮ በሰማይ ያጸድቃል እንጅ በምድር አያስወነጅልም፣ በሰማይም አያስኮንንም፡፡

ከዐብይ አሕመድ በፊት ግን፣ የአማራ ሕዝብ ማትኮር ያለበት፣ ዐማራን እንወክላለን እያሉ፣ የአማራን ሕዝብ በመለስ ዜናዊ ዘመን በወያኔ የቀን ጅቦች፣ በዐብይ አሕመድ ዘመን ደግሞ በኦነግ የጠራራ ጅቦች በሚያስግጡት ብአዴኖች ላይ ነው፡፡  ከነዚህ ፀራማራ ብአዴኖች ውስጥ ደግሞ በኔ አመለካከት ቀንደኛወቹ ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ናቸው፡፡  

እነዚህ ሁለት ብአዴናውያን ወደውም ሆነ ተገደው (convinced or confused) በሰኔ አስራምስቱ የባሕርዳር ጭፍጨፋ ላይ ባንድም በሌላም መንገድ በተጫወቱት ወሳኝ ሚና አማካኝነት የዐብይ አሕመድ እስረኞች እንደሆኑና፣ ዐብይ አሕመድም ግብራበሮቹ መሆናቸውን እንደ ማስፈራርያ በመጠቀም ሲጠራቸው ወዴት፣ ሲልካቸው አቤት የሚሉ፣ አፋሽ አጎንባሹ የሆኑ፣ ፍጹም ታዛዥ ሎሌወቹ እንዳደረጋቸው የታወቀ ነው፡፡

በተለይም ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን ነገረ ሥራው ሁሉ ወሎ የኦሮሞ ነው በሚለው፣ ባጭበርባሪነቱ ወደር በሌለው፣ በኦነጋዊው በዐብይ አሕመድ ስብከት ታውሮ ወደ ኦነጋዊነት የተቀየረና የኦነጋውያንን ፀራማራ አጀንዳ የሚያራምድ ያስመስልበታል፡፡  በኔ በኩል ደግሞ አማራ መስሎ አማራን የሚያስበላ ሕቡዕ ኦነጋዊ ሁኗል ብየ ከደመደምኩ ቆይቻለሁ፡፡  አለበለዚያማ ስልጣን ላይ ከወጣበት እለት ጀምሮ የአማራን ሕዝብ ደም እንባ የሚያስለቅሰውን፣ ኦነጋዊውን አውሬ ዐብይ አሕመድን በሁለት ቀላል መንገደች ከስልጣኑ ማስወገድ ይችል ነበር፡፡ 

አንደኛው መንገድ፣ ብአዴንን ከብልጽግና ማስወጣት ነበር፡፡  ዐብይ አሕመድ በተጭበረበረ ምርጫ ስልጣኑን ከማደላደሉ በፊት፣ አቶ ደመቀ መኮንን ብአዴንን ይዞ ከብልጽግና ቢወጣ ኖሮ፣ የዐብይ አሕመድ ፀራማራ መንግሥት በማግስቱ ይፈርስ ነበር፡፡  ሁለተኛው መንገድ ደግሞ፣ ዐብይ አሕመድን በራሱ ፓርላማ ላይ አንዲት ጥያቄ ብቻ እንዲጠየቅ ማድረግ ነበር፡፡  ጥያቄውም፣ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰላማዊ ተቃውሞ ለማስቆም አልቻልክም ተብሎ ከስልጣን ከወረደ፣  በጠቅላይ ጦር አዛዠነት እመራዋለሁ የሚለውን ጦር በዚህ ደረጃ ለሽንፈት ያበቃው ዐብይ አሕመድ ላንዲት ቀን እንኳን ስልጣን ላይ የሚቆይበት ምክኒያት ምንድን ነው የሚለው ነው፡፡  አቶ ደመቀ መኮንንን ለመምከር መሞከር ግን፣ ውሃ መውቀጥ ነው፣ እንቦጭ ብሎ ይቀራልና፡፡  አውቆ ስለተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም፡፡  

አቶ ተመስገን ጡሩነህ ደግሞ ነገረ ሥራው ሁሉ የረዥም ጊዜ ባልደረባው የነበረውን ዐብይ አሕመድን ለማስደሰት ጠብ እርገፍ ማለት ስለሆነ፣ ከዐብይ አሕመድ ጋር የተለየ ግንኙነት ያለው ያስመስልበታል፡፡  ባጭሩ ለመናገር ይህ ግለሰብ የዐብይ አሕመድ ባልደረባ ብቻ ሳይሆን ጃንደረባም ጭምር ነው፡፡  ለዚህ ይሆናል ወዳጁ ዐብይ አሕመድ ከባሕርዳሩ ጭፍጨፋ በኋላ ለሱ በማይገባው በዶክተር አምባቸው ወንበር ላይ ያስቀመጠው፡፡  በዲባቶ አምባቸው ወንበር ላይ በተቀመጠ ማግስት ደግሞ ፋኖን እያሳደደ መግደልን ዋና ሥራው አድርጎ ተያያዝከው፡፡  የጀነራል አሳምነውን ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በማፈራረስ፣ የአማራ ብሔርተኝነት ያሰጋኛል ያለውን ዐብይ አሕመድን ለማስደሰት ብዙ ርቀት ተጓዘ፡፡  ሽመልስ አብዲሳ የዝዋይና የሻሸመኔ አማሮችን ቆዳ ስላስገፈፈ ብቻ አድናቆቱን ለመግለጽ ባሕርዳር ድረስ ጠርቶ ካባ ደረበለት፡፡  የአማራን ሕዝብ እነ ሽመልስ አብዲሳና ታየ ደንድኣ የሚዘልፉት ሳይበቃ፣ ራሱ አቶ ተመስገን ደግሞ ‹‹ወንጀለኞችን የሚያወድስ ማሕበረሰብ›› በማለት በብአዴን ምክር ቤት ውስጥ ተሳለቀበትና፣ የአለምነው መኮንንን ስድብ ደገመው፡፡     

ወያኔና ኦነግ እስካፍንጫቸው በሚታጠቁበት ጊዜ የአማራ ሕዝብ ራሱን ለመከላከል እንዳይታጠቅ አንቆ መያዝ ብቻ ሳይሆን፣ የታጠቀውንም እንዲፈታ የቻለውን ሁሉ አደረገ፡፡  ይህን ሁሉ ካደረገ በኋላ ደግሞ የአማራ ሕዝብ ዱላ ብቻ ይዞ ድሽቃ ከታጠቀው ከወያኔ ጋር ሲፋለምና እንደ ቅጠል ሲረግፍ ለማየት የቋመጠ ይመስል፣ ከጦርነቱ አስቀድሞ ወያኔን እንሰብረዋለን፣ እንቀብረዋለን እያለ የፌስቡክ ጉራውን እያከታተለ ነዛ፡፡  በዚያ ደረጃ ሲፎክር የነበረ ሰው ደግሞ ወያኔ የአማራን ድንበር ጥሶ ደብረብርሃን እስኪደርስ ድረስ፣ ከጌታው ከዐብይ አሕመድ ጋር እተሰወረበት ተሰውሮ፣ ድምጹን አጥፍቶ አድፍጦ ተቀመጠ፡፡  የአማራ ሕዝብ ወያኔን ወደ መቃበሩ የመሸኘት ዘመቻ ሲጀምር ደግሞ ካደፈጠበት ቡትርፍ ብሎ ወጥቶ ዘመቻውን ባጭሩ ለማስቀረት መልከስከስ ጀመረ፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ወያኔን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳይገላገል፣ ከደመቀ መኮንን ቀጥሎ ከዐብይ አሕመድ ጋር የሚመሳጠረው ሁለተኛው ብአዴናዊ ፀራማራ አቶ ተመስገን ጡሩነህ ባይሆን እንጅ ቢሆን አያስገርምም፡፡   

ስለዚህም፣ ለሕልውናው የሚታገለው የአማራ ሕዝብ በመጀመርያ ደረጃ ማድረግ ያለበት አቶ ደመቀ መኮንንና እና አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ እንዲሁም ዳግማዊት ሞገስንና ብናልፍ አንዷለምን የመሳሰሉት የነሱ ብአዴናዊ ጀሌወች፣ በአማራ ሕዝብ ላይ ለፈጸሟቸው ከባድ ወንጀሎች ጊዜው ሲደርስ የሚጠየቁ ወንጀለኞች እንጅ፣ የአማራ ሕዝብ ወኪሎቹ እንዳልሆኑ ማወቅ ለሚገባቸው ሁሉ አስቀድሞ ማሳወቅ ነው፡፡  በሁለተኛ ደረጃ ማድረግ ያለበት ደግሞ፣  አማራን ንከሱ በተባሉ ቁጥር ካደፈጡበት ቡትርፍ እያሉ ለሚወጡት ለነዚህ ፀራማራ ውሾች ቁብ ሳይሰጥ፣, ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበበት ያለውን ከፍተኛ ተጋድሎውን፣ በከፍተኛ ደረጃ አጠናክሮ መቀጠል ነው፡፡  ብአዴኖች ለአማራ መርዝ በሆኑ ዛፎች ዙርያ የተጠመጠሙ ጥገኛ ሐረጎች ስለሆኑ፣ ዛፎቹ ሲቆረጡ እነሱም ባጭር ጊዜ ውስጥ ደርቀው ይከስማሉ፡፡

በመጨረሻም፣ ለአማራና ለትግሬ ሕዝብ፣ ባጠቃላይ ደግሞ ለሐበሻ ሕዝብ አጭር መልዕክት፡፡  የአማራና የትግሬ የጠብ ምንጮች ወያኔና ብአዴን ናቸው፡፡  ወያኔ መቸም በማይድን የአማራ ጥላቻ በጠና የታመመ የጥላቻ ጽኑ ሕመምተኛ ነው፡፡  ስለዚህም የትግሬ ሕዝብ በዚህ ጽኑ ሕመምተኛ ምክኒያት ከወንድሙ ከአማራ ሕዝብ ጋር እየተጨፋጨፈ እራሱንም ወንድሙንም እንዳያጠፋ ከፈለገ ይህን ሕመምተኛ፣ የማንንም ድጋፍ ሳይፈልግ እሱ ራሱ ማጥፋት አለበት፡፡  

ብአዴን ደግሞ አማራን ከሚጠሉት በላይ አማራን እየጠላ ለሆዱ የሚያድር፣ የሆድ አደርነት ጽኑ ሕመምተኛ ነው፡፡  ቀንደኞቹ ብአዴኖች ደግሞ አማራን የሚጠሉት በሆድ አደርነት ብቻ ሳይሆን በመርሕ ደረጃ የሆነ፣ አማራ ሳይሆኑ አማራን እንወክላለን እያሉ የሚያጭበረብሩ ቀንደኛ ፀራማሮች ናቸው፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ብአዴን በሚባለው የሎሌነት ጽኑ ሕመምተኛ ምክኒያት ከወንድሙ ከትግሬ ሕዝብ ጋር እየተጨፋጨፈ እራሱንም ወንድሙንም እንዳያጠፋ ከፈለገ ይህን ሕመምተኛ፣ የማንንም ድጋፍ ሳይፈልግ እሱ ራሱ ማጥፋት አለበት፡፡  ወያኔና ብአዴን ከጠፉለት ደግሞ የአማራና የትግሬ ሕዝብ እዳው ገብስ ነው፡፡   

አማራና ትግሬ በጥቅል ሐበሻ

ርስበርስ ተናክሰህ በምክኒያት ተልካሻ

ስትዳከምለት በስተመጨረሻ

ሥጋህን ጋግጦ የቦረና ውሻ

ለሃች ይቀብርሃል እሶፍ ኡመር ዋሻ፡፡

 

ሐበሻ ትግሬ ሆይ የመቀሌ አስመራ

ካበሻ ወንድምህ ከአማራ ጋራ

ከቶ ምን አረገው ጥልህን መራራ?

እስኪ መልስልን ባጭሩ አብራራ፡፡

ሐይማኖት ነው ባህል፣ ቋንቋ ወይስ ፊደል

የቱ ነው ምክኒያትህ ለማይታረቅ ጥል?

 

በስልጣን የመጣን በስልጣን የሚገል

ያማራ፣ አሮሞ የትግሬ ቅልቅል

የሆነ ገዥ መደብ ለሠራብህ በደል

ተጠያቂ አድርገህ አንዱን በመነጠል

ለምን ትጠላለህ አማራን በጥቅል?

ኦሮማራ ምንትስ እያለ በመቅጠፍ

ዛሬ እየመሰለ አንተን የሚደግፍ

ነገ እየገጠመ ካማራ ጋር አፍላፍ

ከወንድምህ ጋር አንተን ሲያጨፋጭፍ፣

 

ኦነግ የሚሰኘው ኦሮሞን ሳያቅፍ

ያንተነትህ ጠላት ውሻው አባ ቦትርፍ

እንደሚጋግጥህ ምንም ሳያስተርፍ

አታነብም እንዴ ከግድግዳው ጽሑፍ?

 

ይቅር ተባብለው ለትናንቱ ዛሬ 

ድርና ማግ ሁነው አማራና ትግሬ

ድነው እንዲያድኑ ጦቢያን ከኬኛ አውሬ፣

የሁለቱም ባንዶች ብአዴን ወያኔ

ባስቸኳይ ይመቱ ባስፈላጊ አዳፍኔ፡፡ 

      

መስፍን አረጋ :mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic