>

" ዐምሓራን አንድ አደርገን ኢትዮጵያን እናድናለን!"  ባዮቹ ዛሬ ለአራጆቹ ቢላ አቀባይ ሆነው አረፉት...?!?   (መስከረም አበራ)

ዐምሓራን አንድ አደርገን ኢትዮጵያን እናድናለን!”  ባዮቹ ዛሬ ለአራጆቹ ቢላ አቀባይ ሆነው አረፉት…?!?
መስከረም አበራ

ህይወትን የሚነጥቅ ዋና ችግር እያለ የሌለ ችግር ተፈጥሮ እሱን ላጥፋ ማለት የልግመት ምልክት ነው። የአማራ ህዝብ የችግሩ  ብዛት ራስ  ያዞር ይሆናል እንጅ ችግር አጥቶ አዲስ ችግር የሚፈጠርለት ህዝብ አይደለም። የዚህ ህዝብ ችግር በህይወት የመኖር መብትን መነፈግን የሚያክል ትልቅ ችግር ነው።
የአማራ ህዝብ ወቅታዊ አንገብጋቢ ችግር ሁለት ነው።
 1ኛው ክልሉ ድረስ መጥቶ ሊያጠፋው፣ የሚታከምበት ሆስፒታል ፣ልጆቹን የሚያስተምርበት ትምህርት ቤት እንዳይኖረው የሚያደርገው የወያኔ ፍላፃ ሲሆን
 2ኛው “ለምን አማራ ሆነህ ሳለ በወለጋ፣በቤኒሻንጉል ወዘተ የተገኘህ?” ብሎ በቢላዋ የሚያርደው ስልጣን ላይ ቂብ ያለው አስተሳሰብ ነው።
ለአማራ ህዝብ ቆሜያለሁ የሚል ፖለቲከኛ በአሁኑ ወቅት ከዚህ የባሰ ችግር ከታየው ራሱን ያጋልጣል እንጅ ላለመሞት የሚደረገውን የአማራ ህዝብ ትግል ማጓተት አይችልም።
 በአብን ሊቀመንበርነቱ ላይ ሚኒስተርነት የተደረበለት ወንድም በለጠ ሞላ ከላይ ከተጠቀሱት አማራውን በጋራ የሚያንገላቱ  አንገብጋቢ ችግሮች ይልቅ የሸዋ፣የወሎ፣ የጎጃም፣የጎንደር ንዑሳዊ ህብረቶች ያለመኖር እና በአማራ ክልል ውስጥ ብዝሃነት ባለመስተናገዱ መጣ ያለው ፣ለእሱ ብቻ ዝሆን አክሎ የታየው ችግር አሳስቦታል። በጣም ይገርማል!!!
 በውስጡ ላሉ ብሄረሰቦች የራስ አስተዳደር ሰጥቶ የሚያኖረው የአማራ ክልል ብዝሃነትን ያለማስተናገድ ችግር በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች አማራ መሆን ወንጀል ሆኖ የሚያሳርድ ከመሆኑ ብዝሃነትን ያለማስተናገድ እሳቤ በልጦ ታየው። ወደ ነገስታት እልፍኝ ጠጋ ብለው፣ወንበር ላይ ሆነው  የሰፊውን ህዝብ ችግር ሲያዩት እንዲህ ሆኖ ይታያል ማለት ነው???? ለማንኛውም የአማራ ህዝብ የሚፈልገው ወጣት አዲሱ ለገሰ አይደለም!
የዐምሓራ በደልም ይሁን የኢትዮጵያ መፍረስ ቅንጣት ታህል የማያሳስበው ገረዱ ብአዴን፣ ዛሬ ደግሞ የዐምሓራዉ እና የፋኖ አንድነት እንቅልፍ ሲነሳው፣ የለመደ የክህደት ሰይፉን ስሎ ብቅ ብሏል።
አጤ ምኒልክ ቤተ መንግስት የተቀመጠው የኦነግ ገዢ ኀይል አማራው የተደራጀ እና አንድ የሆነ ሲመስለው፣ ያዘነ በመምሰል የአዞ እምባውን እያነባ አንዴ “የልማት ማህበር” ፣ሌላ ጊዜ ደግሞ “የሰላም ማህበር” በሚል ሰበብ፣ አሽከሩን ብአዴንን በአስቸኳይ ይልክና የተደራጀውን ዐምሓራ ለመበተን ይጥራል።ይህ አልሳካ ካለው ደግሞ “ግልፅ ጦርነት ውስጥ እንገባለን።” በሚል እብሪት ሰራዊት አዝምቶ የአንድነት ምልክት ናቸው ተብለው የተለዮትን በግልፅ ይገድላል።ያስገድላል።
ከሰሞኑን የዐምሓራው የጦር ሜዳ ጀብዱ እና የአንድነት እንቅስቃሴ ቁርጠት የሆነበት ኦህዴድ ብልፅግና አንዴ ግልገል ብአዴኖችን(የአብን አመራር የነበሩና የግምጃ ቤት ሃላፊ የሆኑ) ወሎ በመላክ፣እንዲሁም የዐማሓራ ማጥፊያ እና የኢትዮጵያ ማፍረሻ የሆነው “ሕገ ትህነግ”(ሕገ መንግስቱ) ላይ ዕጁን ጭኖ መሃላ በመፈፀም ሚኒስትርነት ሹመት የተቀበለውን ግለሰብ መጠቀሚያ በማድረግ፣ ዐምሓራው በጦርነቱ ካስተናገደው ጥቃት በላይ ሌላ ጥቃት ይዘው ይልከሰከሱ ይዘዋል።
በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ዋልታና ማገር በሆነችው አጤ ቴዎድሮስ የትውልድ ቦታ ጎንደር ብቅ ብለው”የጎንደር የሰላምና የልማት ማህበር” በሚል ይችን ታላቅ የተቀደሰች ስፋራ ጭራሽ ከኢትዮጵያዊነት ማውረዳቸው ሳያንስ በጎጥ ሊያደራጇት እነ ነውር ጌጡ ሲፍጨረጨሩ ውለዋል።የሚገርመው ነገር ደግሞ ይህንን በሰላም ስም የተደራጀ ማህበር የሚመሩት፣የንግድ ሚንስትሩ መላኩ አለበል እና ማጎንበስ ጌጡ አገኘው ተሻገር መሆናቸውን ስንሰማ፣እነሱ ናቸው ጅሎች ወይስ እኛ ወደሚለው ጥያቄ ገብተናል።
በዚህ ተገርመን ሳንጨርስ አመሻሹን ደግሞ በዐምሓራ ስም ምለው ተገዝተው አብን የተሰኘ የፖለቲካ ድርጅት በመመስረት የግል ስልጣን እና ጥቅም ማግኛ መሰላል ያደረጉ ግለሰቦች(በለጠ ሞላ) ጭራሽ “የወሎ ህዝቦች፣የሸዋ ህዝቦች እና የጎንደር ህዝቦች እያሉ፣ ክደው ስልጣን መቀበላቸው ሳያንስ የዐምሓራ ሱፐር ከፋፋዮች ሆነው መጥተዋል።
ዐምሓራን አንድ አደርገን ኢትዮጵያን እናድናለን፤ብሎም የአፍሪካ አለኝታ እንሆናለን ብለው ሲያለግጉ የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ምላሳቸውን ውጠው ላለፉት 30 ዓመታት በማንነቱ እንደ ቅጠል ለሚረግፈው ዐምሓራ ዛሬም ለገዳዮቹ ዱላ አቀባይ፣ለተጠቂው ደግሞ ነጣጣይ ሆነው መጥተዋል።
ዐምሓራ ሆይ መዳኛህ ክንድህና ዕምነትህ ብቻ ነው
ዛሬ ክደውህ ወንበር ላይ ፊጥ ያሉ እፉኝት ልጆችህ እውነት፣እውነት እልሃለሁ ይፈጠፈጣሉ።ብቻ አንተ አንድነትህን አፅና።
Filed in: Amharic