>

ከ1928 እስከ 1935፣ ከሃይለስላሴ ጉግሳ እስከ ወያኔ (ደረጀ መላኩ - የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

ከ1928 እስከ 1935፣ ከሃይለስላሴ ጉግሳ እስከ ወያኔ

ደረጀ መላኩ (የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

Tilahunegesses@gmail.com

 


 

 

 

Haile Selassie Gugsa (left) with Italian General Emilio de Bono ( Photo Credit : Wikipedia)

ታሪክ እንደሚያስተምረን ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በግፍ ከወረረች በኋላ የመርዝ ጋዝ ምር ከሰማይ እንደ ዝናብ በማዝነብ ህይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ(ሰዎችን፣ተክሎችን እና እንሰሳትን ጭምር) ስታጠፋ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1935 የምእራቡ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ክህደት ፈጽሞባታል፡፡ እውን እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 2021 ሌላው የምእራባውያን የክህደት አመት ይሆን? ህሊና የፈጠረባችሁ ጠይቁ::

የወያኔ አሸባሪ ቡድን ውሸሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል በሚል እኩይ ስብከቱ የሚታወቀው የጎብልስ ታታሪ ተማሪ ነው፡፡ጎብልስ በትልቅ ውሸቱ የሚታወቅ ሲሆነ፣ወያኔም የለየለት የውሸታሞች ስብስብ ነው፡፡ ጎብልስ እንደሚናገረው ከሆነ‹‹ አንድ ትልቅ ውሸት ከተናገርን በኋላ፣ያንኑ ውሸት ስንደጋግመው በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ይኖረዋል፡፡ የእንግሊዝኛው ቋንቋ የበለጠ ገላጭ ስለሆነ እንደሚከተለው ቀርቧል ‹‹ If you tell a lie big enough and keep repeating it, people will eventually come to believe it ›› የወያኔ አሸባሪ ቡድን በስልጣኑ በቆየባቸው 27 ዓመታት ዴሞክራሲን አሰፍናለሁ በማለት የኢትዮጵን ህዝብ ዋሽቷል፡፡ ለ27 አመታት እየዋሸ የኢትዮጵያን ሀብት የዘረፈ ነውረኛ ቡድንም ነው፡፡ እንደ ጎርጎሲያኑ አቆጣጠር 2018 ከማእከላዊ የመንግስት ስልጣኑ ተሸቀንጥሮ ከወደቀ በኋላ መልሶ አሸናፊ ለመሆን ወረራ ከፈጸመ አንድ አመት ሞላው፡፡ ዛሬ እንደገና ከ30 አመት በኋላ ሌካ አዲስ ትልቅ የውሸት ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ የዘር ማጥፋት ውሸት ጀምረዋል፡፡ ከምእራባውያን የዜና አውታች፣መንግስታዊ ካልሆኑ የውጭ ድርጅቶች፣ በርካታ የምእራባውያን ፖለቲከኞች በመለጠቅ የዘር ማጥፋት ወንጀል አልፈጸምኩም በማለት ይዋሻል፡፡ ሁላችንም እንደምናስታውሰው አንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1991 የቀድሞው ሟቹ ጠቅላይ ሚንሰትር አቶ መለሰ ዜናዊ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ስልጣኑ በወያኔ መዳፍ ስር እንዲወድቅ በመፈለግ የኢትዮጵያን ህዘብ በውሸት አደንዝዘውት ነበር፡፡

የወያኔ አሸባሪ ቡድን በአማራ ክልል እና አፋርክልሎች ውስጥ ወረራ በመፈጸም ሰላማዊ ሲቪል ዜጎቸን ህይወት አጥፍተዋል፡፡ሴቶች እህቶቻችንን፣ልጆቻችንን አሰገድደው ደፍረዋል፡፡ የህዝብ ሀብት የሆኑትን ንብረቶች፣ትምህርት ቤቶችን፣ሆስፒታሎችን፣የጤና ጣቢያዎች፣መንደሮችን እና ከተሞችን ዘርፈዋል፡፡ አጥፍተዋል፡፡ ከዚህ ባሻግር የእርሻ ቦታዎችን ከጥቅም ውጭ አድርገዋል፡፡የገበሬውን አህል ዘርፈዋል፡፡ ገበሬውን ለችጋር ዳርገውታል፡፡ የወያኔ ጭካኔ እና ኢሰብዓዊነት ለከት የለውም፡፡ የወያኔ አሸባሪ ቡድን ላምና በሬዎች በአማራ ክልል፣ግመሎችን ደግሞ በአፋር ክልል ገድሏል፡፡

የወያኔን የተፈጥሮ ባህሪ ለመረዳት በ15ኛው ክፍለ ዘመን (እ.ኤ.አ.) አፍሪካውያን ከአውሮፓውያን የሚደርስባትን በደል ለመቋቋም ይሰጡት  የነበረውን ምላሽ ማስታወስ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ አውሮፓውያን የባሪያ ንግድ፣ቅኝ አገዛዝ፣ እና የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝን ሲያስፋፉ ወይም ገቢራዊ ሲያደርጉ በታሪክ ውሰጥ አአፍሪካውያን ቃውመው ነበር፡፡ አውሮፓውያን የአፍሪካን የተፈጥሮ ሀብት ሙሉ በሙሉ ለመቦጥቦጥ የአፍሪካውያን ፍላጎት እንቅፋት ይሆንባቸዋል፡፡ አውሮፓውያን በኢኮኖሚ፣ፖለቲካ እና ባህል አኳያ የበለጸጉት አፍሪካውያንን በማድህየት ነው፡፡ አውሮፓውያን የበላይነታቸውን ለዝንተ ዓለም ለማስጠበቅ ሰለሚፈልጉ በአፍሪካ ምድር የስልጣን ጥመኞችን ይመለምላሉ፡፡ ለአብነት ያህል ሞይስ ቾምቤ (Moïse Tshombé )እና ጆናስ ሳቪምቢ (Jonas Savimbi) ለአውሮፓውያን መሳሪያዎች ነበሩ፡፡ እነርሱ የአፍሪካን ህዝብ ፍላጎት ወደ ጎን ገሸሽ አድርገው ለአውሮፓውያን በወርቅ የተሰራ ሳህን አቅራቢዎች ነበሩ፡፡

ለአውሮፓውያን ያደሩትን የአፍሪካ ልጆች ማደን፣በጥቅም መደለል ዛሬም የአውሮፓውያን የየእለት ስራው ሆኖ ቀጥሏል፡፡ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1935 ኢትዮጵያን የወረረው የፋሺስት ጣሊያንም በኢትዮጵያ የሚገዙለትን ባንዳዎች አላጣም ነበር፡፡ አንዱና ዋነኛው ሀይለስላሴ ጉግሳ ነበር፡፡ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1991 ደግሞ ምእራባውያን ፍላጎታቸውን የሚያስፈጽምላቸውን የሀይለስላሴ ጉግሳ የመንፈስ ልጅ ወያኔን አግኝተዋል፡፡ በነገራችን ላይ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በ1935 ሀይለስላሴ ጉግሳ የጦር ወንጀል የፈጸመ ስለመሆኑ ታሪክ ያስተምረናል፡፡ የሀይለስላሴ ጉግሳ የመንፈስ ልጅ የሆነው የወያኔ ቡድን በ2021(እ.ኤ.አ.) የጦር ወንጀል ፈጽሟል፡፡ በተለይም በትግራይ ክልል የሚኖረው ኢትዮጵዊ ወገናችን (ይህ መልእክት የወያኔን አላማ ደግፈው ኢትዮጵያን ያደሙትን አይመለከትም)  የወያኔ አሸባሪ ቡድን የሀይለስላሴ ጉግሳ   የመንፈስ ልጅ መሆኑን መረዳት ያለበት ይመስለኛል ( በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የወያኔን ተንኮልና ደባ በተመለከተ በጥልቀት የተረዳ ይመስለኛል፡፡)

በነገራችን ላይ የፈጠራ ወሬ በመንዛት የወያኔን አሸባሪ ቡድንን የሚደግፉት፣በኢትዮጵያ ላይ ጫና የሚፈጥሩት፣አሳሳችና የውሸት ዜና በማሰራጨት አለምን የሚያደናግሩት  የምእራቡ አለም ፖለቲከኞች፣መንግስታዊ ያልሆኑ የውጭ ድርጅቶች፣ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን፣ጋዜጠኞች ሸፍጥ እምብዛም ላይገርም ይችላል፡፡  የምእራቡ አለም የሚፈልገው ቡድን ስልጣን እንዲይዝ ምኞትና ፍላጎት ካለው ጉዙው እጃቸው ረዥም፣ ሴራቸውም ውስብሰብ ነው፡፡ ምእራባውያን በአንድ ሀገር ብሔራዊ ስሜት ያለው መሪ እንዲበቅል ፍላጎታቸው አይደለም፡፡ የህዝቡን የልብ ትርታ የሚያዳምጥ፣ስነ ልቦናውን በቅጡ የሚረዳ አፍሪካዊ መሪ ለምእራባውያን መሰሪ ተንኮል የሚመች ባለመሆኑ እንዲህ አይነት መሪን ከስልጣኑ ለማውረድ ፊታቸውን  አያዞሩም፡፡ እንደ ጎርጎሲያኑ አቆጣጠር ከ1991 እስከ 2018 የምእራባውያን ወዳጅ የነበረው የወያኔ አሸባሪ ቡድን የማእከላዊ መንግስቱን ስልጣን እንዲቆጣጠር የሚሄዱበት መንገድ ሩቅ ነው፡፡  የዚህ ሁነኛ ምክንያቱ ደግሞ የምስራቅ አፍሪካ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚ እና ባህላዊ ማእከል አድረገው የሚቆጥሯት የኢትዮጵያ መንግስት ጭንቀት ውስጥ የጣለቸው በመሆኑ ነው፡፡ ምእራባውያን ኢትዮጵያ የወያኔ አሸባሪ ቡድንን ማሸነፏ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ማነቃቂያ እንደሆነ በሚገባ የሚረዱ ናቸው፡፡ በምእራባውያን የሚደገፍ ቡድን መሸነፍ ለሌሎች አፍሪካውያን አርአያነቱ የትዬየሌሌ በመሆኑ ኢትዮጵያ የገጠማት ከባድ ፈተና ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ከወያኔ አሸባሪ ቡድን የቅርብም የሩቅ ጠላቶች አሉ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አሳልፎ የሚሰጥ ቡድን ስልጣን እንዲጨብጥ ይረዳሉ፡፡

የኢትዮያ ህዝብ  ምእራባውያን የኢትዮጵያን አንድነትና ሉአላዊነት ለማናጋት ሲሉ ከብዙ አመታት ጀምሮ ኢትዮጵያን የወረሩ ሀገራትንና የተገንጣይ ሀይሎችን  ሲረዱ ስለመቆየታቸው የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ለአብነት ያህል እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1935 ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በግፍ በወረረችበት ኢትዮጵያን አንድነት ባናጋችበት ግዜ በርካታ የምእራብ ሀገራት መንግስታት፣ፖለቲከኞቻቸው፣ ጋዜጠኞች እና ምሁራን ፣አንዳንድ የፋሺስት ደጋፊ ባንዳዎች ድጋፍ ሰጥተዋት እንደነበር ታሪክ ያስተምረናል፡፡ የታወቀው የፋሺስት ጣሊያን የታሪክ ጸሃፊ ኤኔሪኮ ሴሩሊ (Enrico Cerulli) በመጽሐፉ ላይ እንዳሰፈረው ከሆነ ሀይለስላሴ ጉግሳ  ከፋሺስት ደጋፊዎች አንዱ ነበር፡፡

እንደ ጎርጎሮሲኑ አቆጣጠር 1935 የተባበረችው አሜሪካ፣ታላቋ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ኢትዮጵያን በማግለል የባይተዋርነት ስሜት እንዲሰማት ከማድረጋቸው ባሻግር ኢትዮጵያን ለሙሶሎኒ ለማስረከብ ተስማተውም ነበር፡፡ ለአብነት ያህል እንደ ጎርጎሮሲኑ አቆጣጠር ታላቋ ብሪታንያና ፈረንሳይ ‹‹ሆሬ-ላቫል›› (The Hoare–Laval Pact of 1935 ) በሚል ስምምነት ኢትዮጵያ ለሙሶሎኒ ለመስጠት ተስማምተው እንደነበር፣እንዲሁም እንደ ጎርጎሮሲኑ አቆጣጠር በ1938 የተጠቀሱት ሁለቱም ምእራባውያን ሀገሮች ፋሺስት ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ሉአላዊ መብት አላት በማት እውቅና ሰጥተዋት እንደነበር ከታሪክ እንማራለን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበረችው አሜሪካ ፕሬዜዴንት የነበሩት ዝነኛው ሩዝቬልት የገለልተኝነት አቋም ቢኖራቸውም ቅሉ የአሜሪካ ካምፓኒዎች ለጦርነት የሚጠቅሙ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለፋሺስት ጣሊያን ይልኩ ነበር፡፡ እነኚህ ሶስቱ ምእራባውያን ሀገራት ያንዬ ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በግፍ ወራ የመከራ መዓት በቅደመ አያቶቻችን ላይ ስታወርድ ማእቅብ ለማድረግ መንፈሳዊ ወኔ ከድቷቸው ነበር፡፡ የታሪክ ፌዝ ሆነና ዛሬ ኢትዮጵያ የፋሺስት ኢጣሊያ የመንፈስ ልጅ የሆነው የወያኔ አሸባሪ ቡድን የከፈተውን ወረራ ለመቀልበስና ህልውናዋን ለማስከበር በመነሳቷ ብቻ ማእቀብ ጥለውባታል፡፡ በእውነቱ ለመናገር የኢትዮጵያ እድሏ ያሳዝናል፡፡ በነገራችን ላይ ምእራባውያን የወያኔ አሸባሪ ቡድንን ወደውት አይደለም የሚደግፉት፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ከ1991(እ.ኤ.አ.) ጀምሮ ምእራባውያን በአፍሪካ ያላቸውን የኢኮኖሚ፣ፖለቲካዊና ዲፕሎማቲክ የበላይነት ለማስጠበቅ እንደ ትሮይ ፈረስ የሚጋልቡት ስለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የውጭ ሀይሎች በተለይም የምእራቡ አለም ኢትዮጵያን አንገት በማስደፋት፣አሻንጉሊት መንግስት በመመሰርት የአፍሪካን የተፈጥሮ ሀብት መቀራመት እንችላለን ብለው ካሰቡ ዘመናት መቆጠራቸውን የአሁኑ ትውልድ መገንዘብ አለበት፡፡ ምእራባውያን ኢትዮጵያን የሚያደማላቸው የትሮይ ፈረስ ካገኙ የሚተኙ አለመሆናቸውን ዛሬ በገቢርም፣በነቢብም እያሳዩን ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ነው የወያኔ አሸባሪ ቡድን ወደ ስልጣን ለመምጣት ስለሚፈልግ ወይም የቆየ የመገንጠል ህልሙን ለማሳካት ሲል የምእራባውያን አገልጋይ ለመሆን ቃል ገብቷል፡፡

የተባበረችው አሜሪካ የፖለቲካ አርክቴክት የሆኑት ሚስተር አንቶኒ ብሊንከን ‹‹ የሳሙኤል ሆሬን ›› መንፈስ ( ghost of Samuel Hoare ) የሚከተሉ ይመስላሉ፡፡ ወይም የሆሬ-ላቫል ፓክት ቅጂን new version of the Hoare-Laval Pact ገቢራዊ ለማድረግ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ይህም ማለት እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በ1935 ግፈኛውን የፋሺስት ጣሊያንን ደግፈው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ የምእራባውያን ወኪል ወይም ወዳጅ የሆነውን አሸባሪው የወያኔ ቡድን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰሩ ስለመሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ የወያኔ ቡድን እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1991 የነበረውን ሁኔታ ለመድገም የራሳቸውን ጥላ እንኳን መወከል የማይችሉ ዘጠኝ ጎሰኞች ጋር በተባበረችው አሜሪካ ዋሽንግተን ከተማ ስብሰባ ማድረጋቸው ከመገናኛ ብዙሃን ተሰምቷል፡፡ አይበለውና ከተሳካላቸው እነኚህ ስብስቦች የምእራባውያን ጥቅም አስጠባቂ የሆነ  በኢትዮጵያ አሻንጉሊት መንግስት ለማቋቋም ከመርዳት ውጭ ፋይዳ የሌላቸው ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ይህ እውን ይህ የሆሬ-ላቫል ቅጂ? 

2021( እ.ኤ.አ.) የ1935 (እ.ኤ.አ.) የተፈጠረውን ሁነት የሚመልስ ይመስላል፡፡ አንዳንድ የምእራባውያን ደጋፊዎችና ጸሃፊዎች፣ እንዲሁም ጋዜጠኞች በተለይም በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ፣ የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሌሞንዲ ላይ የሚጽፉት ሃሳብ የኤኔሪኮን ዱካ እንደሚከተሉ ያሳየናል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1935 ላይ የፋሺስት ጣሊያን ጦር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ሲያጠፋ ደግፈው የተነሱትን ጋዜጠኞችና ባንዳዎች አቋም ያስታውሰናል፡፡ ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ የወያኔ አሸባሪ ቡድንና አንዳንድ ምእራባውያን ሀገራትና ጋዜጠኞቻቸው በፋሺስት ጣሊያን ግዜ የተፈጸመው አሳዛኝ ዜና ዛሬም እየተደገመ ይገኛል፡፡

በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ቀኝገዢዎችን አሳፍራ የመመለስ ታሪኳ የደመቀና የተከበረ ስለመሆኑ ምንም የሚያከራክር አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን(እ.ኤ.አ.) ጀምሮ ከአውሮፓውያን ጋ ካደረገችው የዲፕሎማቲክ ታሪክ በመነሳት የምንማረው ቁምነገር ቢኖር ምእራባውያን የቆሙት ለኢትዮጵያ ፍላጎት ሳይሆን የራሳቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የቆሙ ስለመሆኑ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና በረዥሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ምእራባውያንም ሆነ ሌሎች ሀገራት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለመድፈር ወይም ለመግፈፍ ሞክረው አልተሳካላቸውም።

 

 

 

Filed in: Amharic