>
5:21 pm - Monday July 20, 7007

“ትዕዛዝ አልደረሰንም” - አማራን ማስጨፍጨፊያ ኦነግ/ኦህዲዳዊ ሥልት! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

ትዕዛዝ አልደረሰንም” – አማራን ማስጨፍጨፊያ ኦነግ/ኦህዲዳዊ ሥልት!

 

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ma74085@gmail.com


አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት አማራን ራሱን ሳይቀር ከሥሩ አሰልፎ የመጨረሻውን ዘመቻ ለመጀመር ፊሽካውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኘው የአራት ኪሎው ዘንዶ ልክ እንደጥንቱ ደራጎን የኢትዮጵያውያንን ሥጋና ደም የዕለት ከዕለት ግብር አድርጎ አለልክ እየተቀለበ በከፍተኛ ደስታ ተውጦ ጮቤ እየረገጠ ይታያል – በአጨብጫቢዎች ብዛትም ሰክሮ የሚሆነውን አጥቷል፡፡ ይህ የሰው ደምና ሥጋ ጠጥቶና በልቶ የማይረካና የማይጠግብ ደራጎን አማራን በአክራሪ ኦሮሞና በወያኔ ትግሬ ሁለት ነበልባላዊ እሳቶች መሀል ጥዶ በነዚህ ነዲዶች እየተቃጠለ መፈጠሩን ከሚራገመው ንጹሕ አማራ በሚወጣ የሲቃ ድምጽ መዝናናቱን ቀጥሏል፡፡ በሰው ስቃይ የመደሰቱን ገሃነማዊ ተፈጥሮውን ደግሞ በአስመሳይ የፌዝኝነትና የሸንጋይነት ተፈጥሮው በመሸፈን በርካታ አማሮችን እያነሆለለ አሽቃባጮቹ አድርጎ አማራውን በአማራ ላይ ማዝመት ችሏል፡፡ ይህ እውነት ቢወዱትም ቢጠሉትም ያለና በገሃድ የሚታይ አሳዛኝ እውነት ነው፡፡ 

አንድ ጤናማ ኢትዮጵያዊ አሁን በሀገራችን ውስጥ እየሆነ ያለውን አስቀያሚ ታሪካዊ ክስተት ሁሉ እየተመለከተ የዘንዶው ደጋፊና ተባባሪ ሆኖ የሚሊዮኖችን ዕልቂትና የንብረት ውድመት እንዲሁም ከገዛ ቀዬ መፈናቀል “የኢትዮጵያ ትንሣኤ ምልክት ነው” ሊል አይችልም፡፡ እንደዚያ የሚል ቢኖር ከለየለት ዕብድ ወይም በድግምት ከታሰረና ጠበል ከሚያሻው ምስኪን ሰው ተለይቶ ሊታይ አይገባውም፡፡ አማራውና ትግሬው በኦሮሙማ የፖለቲካ ሤራ ሲጨራረሱ እያዬ፣ በወለጋና በሌሎች ኦሮምኛ በሚነገርባቸው አካባቢዎች የሚኖረው አማራ በኦነግ ሸኔ በየቀኑ አንገቱ ሲቀላና ንብረቱ ሲወድም ሲዘረፍ እያዬ፣ በፌዴሬል ተብዬው የሥልጣን ቦታዎች የሚሾመው ሁሉ በአብዛኛው አክራሪ ፕሮቴስታንት ኦሮሞ መሆኑን እየታዘበ፣ ማንን እያለገለ እንዳለ የማያውቅ የኦሮሙማ ፓስተር ስብከቱና “የትንቢቱ ቃል” ሁሉ ለዘንዶውና ለነገዱ አጋድሎ በግልጽ ሴተኒዝምን እያስፋፋ እያዬ፣ አዲስ አበባ ቀስ በቀስ በኦሮምያ ክልል እየተጠቀለለች መምጣቷን እያዬ፣ የጥቂት መቶ ብሮች ጉቦ ሽቅብ ተወንጭፎ ለትንሽ ጉዳይ ሳይቀር በመቶ ሽዎችና በሚሊዮኖች መሆኑን እያዬ፣ ብአዴን ተብዬው አጎዛ ድርጅት ለኦህዲድ/ኦነግ ሰግዶ የኦሮሙማ ምንጣፍ ጎታች መሆኑን እያዬ … ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል አንድ ዜጋ በዘንዶው አምልኮት ታውሮ “ከእገሌ አመራር ጋር ፉልዱረት(ወደፊት)!” ብሎ ክችች ካለ ምንም በማያጠራጥር ሁኔታ ጤንነቱ የተቃወሰ ነው፤ ከዚህ አንጻር “My Dragon…” ማለቴ … “My PM is on duty!” ለሚሉ ልበ ሥውራን ምሁር ተብዬዎች ማዘን ተገቢ ነው፡፡ ስም መጥራት ሳያስፈልግ ከኢዜማ እስከ አብን፣ ከግንቦት ሰባት እስፈ የካቲት 11፣ ከአርቲስት እስከ አክቲቪስት፣ ከዲፕሎማ እስከ ፕሮፌሰርነት …. ከሞላ ጎደል በሚዲያ እየወጣ ለዘንዶው የሚያሽቃብጠው ሁሉ በነገይቷ ኢትዮጵያ እንዲኖር ከፈለገና ጠባቧን ድልድይ ተሻግሮ ከተራፊዎች ጋር የሚመደብ ከሆነ አስቀድሞ የአእምሮ ቀዶ ህክምና ያስፈልገዋል፡፡ አፎምያን ከደራጎን ላንቃ ያወጣት ቅዱስ ጊዮርጊስ መሆኑን ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ይናገራሉ፡፡ ኢትዮጵያን ደግሞ አማራ የተባለ የዘመናት የበቀልና የጥላቻ ውጤት ገፈት ቀማሽ ነገድ ከዚህ ዘንዶ ጉሮሮ አውጥቶ ለትንሣዔዋ ያበቃታል፡፡ ይህም ቀን በብርሃን ፍጥነት እየመጣ ነው፡፡ ይህ ከራሱ ጀምሮ ተቆጥሮ የማይዘለቅ ጠላት ያለው ሕዝብ ዕድሜ ለጠላቶቹ አሁን ወደአንድነት እየመጣ ነው፡፡ ትንቢት ይዘገያል እንጂ እንዲቀር የሚያደርገው አንድም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ማመን ደግሞ ከአላስፈላጊ ጀብደኝነትና የጥፋት መንገድ ይታደጋልና ጥሩ ነው፡፡ እውነቱ ይህ ከሆነ ዘንዳ አማራን እንደግፈው፡፡

“ትዕዛዝ አልወረደልንም” የሚባል የመከላከያ ነጠላ ዜማ መስማት ከጀመርን ስድስት ወር ገደማ ሆነን፡፡ ወያኔን በቀደመው የትግራይና ወሎ-ጎንደር ክፍለ ሀገራት ወሰን ማስቆም እየተቻለ በዚህ ትዕዛዝ መሠረት መከላከያው ብቻ ሣይሆን የአማራም ጦር እንዳይዋጋ ሽባ እየተደረገ በማይታመን መብረቃዊ ፍጥነት ወያኔ አዲስ አበባን እንድትጠጋ ተደረገ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ በ17 ቀናት ጦርነት ባዶ እጇን ቀርታ የነበረችው ወያኔ ዘንዶውና ሼሪኮቹ በውስጥ መስመር ባደረጉት በዓላማ ትስስር ላይ በተመሠረተ (more of telepathic) ስምምነት ቁጥር ሥፍር ከሌለው አበረታች ንጥረ ነገር (ሀሽሽ) ጀምሮ እስከ ከባድ መሣሪያና ስንቅ እንዲሁም የሳተላይት ምስል መረጃ ድረስ በገፍ እንዲደርሳት ተደርጎ ይቺው ጉደኛ አማራና አፋር ላይ ዘምታ ያደረገችውን አደረገች፡፡ ያኔ በአማራው “ፈሪነት” ኦሮሙማዎች ሣቁ፡፡ ያኔ በአማራ ውድመት ምዕራቡም አውሮፓም ጥርሱን ተነቅሶ ሣቀ፡፡ ያኔ በኦርቶዶክስና በአማራ መቀመቅ መውረድ አሜሪካ ከት ብላ ሣቀች፡፡ ያኔ ግብጽ፣ ሱዳንና ዐረቦችም ጥርሳቸውን ጉራማይሌ ተወቅረው ሣቁ፡፡ ሁሉም የአማራና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጠላት በዕቅዳቸው ስኬት አንዱ ከሌላው እየተያዬ ተሣሣቀ፤ ተሣለቀ፡፡ ከአድማስ ወዲያ ማዶ ሀገር ያለ የማይመስለው ንጹሕ የአማራ ገበሬም የቁም ስቅሉን አዬ፡፡ ዓለም ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ በደልና ስቃይ በወያኔና ተባባሪዎቿ አማካይነት ደረሰበት፡፡ ያን ሁሉ ግፍና በደልም ፈጣሪ መዝግቦ ያዘው፡፡ ብድራቱን ለመክፈልም ቀጠሮ ያዘላቸው፡፡ ቀጠሮውም እየደረሰ ነው፡፡ አንቸኩላ!! እኔ አልቸኩልም፡፡ ….

ወያኔ አሁን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥታ ወደኋላዋ አፈግፍጋለች – ራሷ እንደምትለው ለሥልትም ይሁን እርሷና ዘንዶው ለሚያውቁት ሌላ ጉዳይ – ግዴለም – ብቻ አፈግፍጋለች፡፡ ዘንዶው ግን ወያኔ ወሎንና ጎንደርን ጨርሳ ሳትለቅ ጦርነቱን አቁሙ ብሎ አዘዘ፡፡ ወልቃይትና አላማጣ-ኮረም እስከአሸንጌ ሐይቅ በተጋሩ ምስክርነት ራሱ የትግሬ አካል ሆነው እንደማያውቁ የተመሰከረለት ሃቅ ነው – መለስ የወሰደውን መሬት ልጁ ዘንዶው ለትግራይ ሊያጸድቅ በከንቱ መፍጨርጨሩ ነው አሁን፡፡ ነባሩን ታሪካዊ እውነት ትግሬዎችም የሚያውቁት መሆኑ እንዳለ ሆኖ ወያኔ አንዳችም ምድራዊና ክልላዊ ህግ ሳይገዛት እስከደብረ ብርሃን የሚገኝን ሕዝብ አራቁታና ንብረት ዘርፋ ወይ አውድማ ከተባረረች በኋላ እገባችበት ገብቶ ወንጀለኛን መያዝና ለፍርድ ማቅረብ፣ የተዘረፈ ንብረትንም መመለስ ሲገባ የተሟሟቀን ጦር እዚያ ማስቆም በየትኛውም መለኪያ ፍች-አልባ ነበር ወይንም ነው – ያ ዓይነቱ ትዕዛዝ ለወያኔ ለራሷ ዕንቆቅልሽ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የቃቃ ጨዋታ ነው እሚመስለው ያን መሰሉ ወታደራዊ አመራር፡፡ ይህ የዘንዶው ትዕዛዝ ታዲያ ደባ መሆኑን እንኳንስ አማራው ጀምጀሙና ሙርሲው ያውቁታል፡፡ ዘንዶው በርሱ ቤት ሤራውን ማንም የማይደርስበት ልዩ ዐዋቂ ነው፤ ተንኮሉ የማይታወቅበት ብልጥ ነው፤ ለአማራ የሚዘረጋው ወጥመድ ሁሉ የማይነቃበት እጅግ “ጥበበኛ” እንደባብ ተስለክላኪ ፍጡር ነው፡፡ የሚገርም ተፈጥሮ ያለው ታዳጊ ዘንዶ ስለመሆኑ በበኩሌ መመስከር እችላለሁ፡፡ ወያኔ ቤት ማደግ ወያኔን የሚያስንቅ እስከዚህን ብልጣብልጥ እንደሚያደርግ አላውቅም ነበር፡፡ 

ያቺ ወያኔን ያለ ብዙ ጦርነት አዲስ አበባ ጥግ እንድትደርስ ያደረገችው ትዕዛዝ ሰሞኑን በወልቃይት በኩል ልትደገም እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡ የአብንን ሰዎችና የግንቦት ሰባትን መሠሪ የአማራ ጠላቶች በዙሪያው የኮለኮለው የአማራን ደም ጠጥቶ የማይጠግበው ዘንዶ አማራን በወልቃይት በኩል በሚተም የወያኔ ጀሌ ጎንደርንና ባህር ዳርን አልፎ ደብረ ማርቆስን ረጋግጦ ጎሃ ጽዮን ድረስ ልክ እንደወሎውና እንደሰሜን ሸዋው የቀረችዋን የአማራ ጥሪት ሊያወድም ሕዝቡንም ሊጨፈጭፍና ሊያዋርድ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህን የሚያደርገውም የአማራን ጦር እንደለመደው ከአካባቢው በማስወጣትና ቅን ታዛዡን መከላከያን በመተካት በዚያች በተለመደች “ትዕዛዝ አልደረሰንም” የተበላ ዕቁብ ዓይነት ማጨናበሪያው አማራን የዶጋ ዐመድ ለማድረግ በማቀድ ነው፡፡ ይህን መሰል ቁጭ በሉ ከሞት የተረፈው አማራ ይቀበለዋል ወይንስ አይቀበለውም የሚለውን ቆይተን የምናየው ነው፡፡ የዘንዶው ዕቅድ ግን ይሄው ነው፡፡ ዕቅዱ ግቡን እንደሚመታለትም በጣም እርግጠኛ ነው፤ ምክንያቱም “ሲጠሯቸው አቤት፤ ሲልኳቸው ወዴት” የሚሉ ቅን የብአዴን አጋሰሶች አሉት፡፡  እነዚህ ብአዴናውያን የሚባሉ የሰው ግማሾች አማራን እንዳዋረዱት ማንም አላዋረደውም፡፡ ለአማራ ተቆርቋሪ ናቸው የሚባሉትን ደግሞ ዘንዶው ለዓላማው ስኬት ሲል አስቀድሞ ውጧቸዋል፡፡ አማራ አሁን ባዶውን ነው ፤ ባዶ እንደሆነ ግን አይቀርም፡፡ ዘንዶውን የሚሰለቅጥ መብረቅ ከላይ ወርዷል፡፡

ወደዝምዝማቱ እየመጣሁ ነው ትንሽ ታገሱኝ፡፡ አማራን ለማጥፋት ከአማራ ጠላት ጋር የተሰለፋችሁ ሁሉ ወደኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ ስማችሁን መጥራት አልፈልግም – ጠርቻችሁም አልዘልቀውም፡፡ ግን ግን ስማችሁን ቄስ ከመጥራቱ በፊት ለዚህ ሞልቶ ለማይሞላ ከርሳችሁ ስትሉ፣ ረክቶ ለማይረካ የሀብትና የሥልጣን ፍቅር ስትሉ ከገባችሁበት አዘቅት በቶሎ ውጡ፡፡ የነገድ ተዋፅኦዋችሁ ምንም ይሁን ምን – ሲፈልግ አማራነታችሁ 10 በመቶም ይሁን 86 በመቶ – አማራነት ይበልጡን በአስተሳሰብና በአመለካከት ላይ የተመሠረተ እንጂ እንደውሻ ደምና አጥንትን በማነፍነፍ ላይ የተመረኮዘ አይደለምና እየሸጣችሁት ወደምትገኙት ኢትዮጵያዊነት ፈጥናችሁ ተመለሱ፡፡ ይሉኝታና ሀፍረት አይያዛችሁ፡፡ አማራም ሆነ ኢትዮጵያ ይቅር ባይ ናቸውና ይቅርታን አታጡም፡፡ አንዳንዶቻችሁ ልጆች እንደመሆናችሁ ልጅነት ደግሞ ለዝናና ለሥልጣን ጉጉ ሊያደርግ ስለሚችል ስህተታችሁ ይገባናልና ወደጤናማው መንገድ ለመመለስ ጊዜ አትፍጁ፡፡ ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር ተዋርዳችሁ የሞት ሞት ከምትሞቱ ከኢትዮጵያ እናታችሁ ጋር ሆናችሁ ለክብራችሁ ስለክብር ተዋድቃችሁ በክብር ሙቱ፡፡ ያኔ ዘላለማዊ የሀፍረት ማቅ ሳይሆን የምን ጊዜም የክብር አክሊል ትቀዳጃላችሁ፡፡ ያኔ “እገሌ ባባቱ እንዲህ ያለ ዘር ነበር፤ እገሌ ደግሞ በአያቱ እንዲህ ያለ ነገድና ጎሣ ነበር” እያለ ምናልባትም እናንተ ባላሰባችሁት መንገድ ዘር ማንዘራችሁን እየጎተተ የሚዘባበትባችሁ አቃቂረኛ አይኖርም፡፡ እናታችሁን በቁራሽ እንጀራ አትለውጧት፤ እንደዔሣው አትሁኑ፡፡ የዓላማ ጽናታችሁን በፍርፋሪ ሥልጣን አትቀይሩት፡፡ ሁሉም ያልፋል – ሀብትና ሥልጣንም፡፡ ትናንትን አስታውሱ፤ ዛሬን ተመልከቱ፤ ስለነገም አስቡ፡፡ ሰው ሆኖ መገኘት ዕዳ ቢሆንም ሰው ለመሆን ሞክሩ፡፡ በሰው ቁስል ደግሞ እንጨት አትስደዱ፡፡ መስከረም አበራን እዩ፤ እስክንድር ነጋንም እዩ፡፡ በነሱ አትቀኑም? 

እንግዲህ ኢትዮጵያ ልትነሣ፣ ጠላቶቿም አፈር ከድሜ ሊግጡ የቀረው ጊዜ በጣም – እጅግ በጣም አጭር መሆኑን ልናገርና በሚታየኝ ሁለንተናዊ እውነት ልሰናበት፡፡ ወያኔ ያለች የምትመስለው የውሸት ነው – አልሞት ባይ ተጋዳይ ከሆነች ጥቂት ቀናት ምናልባትም ሣምንታት አለፉ፡፡ እርሷን ጃዝ ብለው አማራን እያስጨረሱ የሚገኙ ወፍራም የሆኑ ያህል የሚሰማቸው ግን ከንፋስ የቀለሉ የአማራ ጠላቶችም ቀናቸውን የሚጠብቁና የትም የማይደርሱ ዳግማዊ ወያኔዎች ናቸው፡፡ የሚወጣና የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል፡፡ እነዚህን ከፈጠረቻቸው ከወያኔ ውድቀት እንኳን ቅንጣት መማር ያልቻሉ የታሪክ አተላዎችን ዳግማዊ ወያኔ ስል ከነሙሉ ወያኔያዊ ጥቅም፣ ክብርና ሞገሱ ጭምር ማለቴ ነው፡፡ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ወያኔ ያየችውን ክብርና ሞገስ ከነሙሉ ግርማ ሞገሱና ጥቅሙ አይተዋል፡፡ አራት ዓመት መፈራትና አፄ በጉልበቱ ሆኖ መንገሥ ቀላል አይደለም፡፡ ይሁንና የነሱም መጨረሻ ከወያኔ ቢብስ እንጂ የሚሻል አይሆንም፡፡ ደስ የሚለውና ማንም በድርድር የማያስቀረው አንድ እውነት አለ፡፡ እሱም ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሉንም እንደሥራው የሚከፍልና ጊዜውን ጠብቆ በምሕረት እጆቹ የሚዳብሳት አምላክ ያላት መሆኑ ነው – ለዚህ እውነት ታሪክን አንብብ፤ ዐዋቂ ሰውም ጠይቅ፡፡“ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል” ይባላልና ቀጣዩን መራር ሀገራዊ እውነት ተመልከቱልኝና የኢትዮጵያን ትንሣኤ መቃረብ ተረዱልኝ፡፡

ጴንጤ እየተመረጠ የሚሾምባት፣ ኦርቶዶክስ እየተመረጠ የሚታረድባት፣ ኦሮሞ እየተመረጠ የሚሾምባት፣ አማራ እየተመረጠ አንገቱ በሠይፍ የሚቀላባት፣ ወጣት ባለጊዜ እየተመረጠ የሚሾምባት፣ ያልተማረ ደነዝ እየተመረጠ ሥልጣን የሚይይዝባት፣ የሀብት ክፍፍሉን የቀን ጅቦች የሚያደላድሉባት፣ እውነተኛ ባንዲራ እየተቀማና እየተቃጠለ በቤተ ሙከራ ተሠርቶ እንደቡና ቁርስ በከዚህ መልስ የሚታደል መናኛ ጨርቅ የሚውለበለብባት፣ ሀገሩን ወዳድና ዐዋቂ ዜጋ እየተመረጠ የሚታሰርና የሚገደልባት፣ ሙሰኛ እየተመረጠ የሚሾምባት፣ ወጥቶ መግባት ብርቅ የሆነባት፣ ከዘንዶው ጋር ወልዶ አሳዳጊ ጌታን በካድሬነት ያገለገለ በኩራዝ እየተፈለገ የሚሾም የሚሸለምባት፣ ከተረኛው ነገድ ውጪ ሌላው ከሀብትም ከሥልጣንም የሚባረርባትና ከዚያም ባለፈ እንደሰው የማይቆጠርባት፣ በአንዲት መናገሻ ከተማ የሁለት መንግሥታት አዛዥነት የነገሠባት፣ ሥርዓት አልበኝነት የሰፈነባት፣ ጠያቂና ተጠያቂነት የጠፋባት፣ ርሀብና በሽታ የሚፏልሉባት፣ ድህነትና የኑሮ ውድነት አለቅጥ የሚዘባነኑባት፣ ሞት የረከሰባት፣ ሰው ሆኖ መፈጠር የሚያስረግምባት፣ የጦርነትና የዕልቂት ዐዋጅ የሚጎሰምባት፣ የውሸት ዲግሪና የፈጠራ ትርክት የሚናኝባት፣ በሀሰት ታሪክ በቆሙ ሀውልቶች ሕዝብ እንዲባላ የሚደረግባት፣ ዕውቀት ዕርሙ የሆኑ ማይምና ደመነፍሳዊ ወጣቶች በሕዝብ ደም የሚጨመላለቁባት፣ አለቃና ምንዝር የተናናቁባት ….ሀገር እንዳለች አትቆጠርምና እውነተኛዋ ኢትዮጵያ ልትነሣ የግድና የጊዜ ጉዳይም ነው፡፡ እርግጥ ነው ከዚህ ሁሉ ሃቅ አኳያ ስንታዘብ ጨለማው ደንግዟል፡፡ የጨለማው መጠንከርም የንጋትን መቃረብ ይጠቁማል፡፡ እንግዲያውስ …. የቆመ የሚመስለው ይጠንቀቅ!! ከአስመሳዮችና ከእበላ ባይ ሆዳሞች ራሳችንን እንጠብቅ፡፡ ከይሁዳዎች ራቅ እንበል፡፡ ለወራት ዕድሜ ብለን የታሪክ ትዝብት ውስጥ አንግባ፡፡ የተሳሳቱ ወገኖቻችንን ፈለግ አንከተል፡፡ ብቻችንን የሆንን ቢመስለንም ወይም ብንሆንም እንኳን ከእውነቱ አናፈንግጥ፡፡ ዛሬ አያጥበርብረን፡፡ በሆድ ማሰብን እናቁም፡፡ በቃ፡፡

Filed in: Amharic