>

"አቢቹ ከብዙ ችግሩ ጋር ግንባር ሄዶ ግንባሩን ሰጥቶ ኢትዮጵያን ከመበታተን የታደገ መሪ ነዉ...!!!" መኮንን ብሩ (ዶ/ር)

“አቢቹ ከብዙ ችግሩ ጋር ግንባር ሄዶ ግንባሩን ሰጥቶ ኢትዮጵያን ከመበታተን የታደገ መሪ ነዉ…!!!”
መኮንን ብሩ (ዶ/ር)

መይሳዉ ካሳ ለኢትዮጵያ ሲል በመቅደላ ተራራ አፋፉ ላይ ጥይቱን ጠጥቶ ተሰዋ። ትዉልድም ታሪክም ጀግንነቱን ሲዘክረዉ ኖሯል፤ ይኖራልም። የሸዋዉ ንጉስ እና በኋላም የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት እምዬ ሚኒሊክም በአድዋ ኮረብቶች ላይ ተዋድቀዉ ነጭ ነጫጭቦችን ለኢትዮጵያ ሲሉ በዚያ የጨለማ ዘመን አንበርክከዉ የመላዉ ጥቁር ሕዝብ ፋና ወጊ ሆነዋልና ትዉልድም፤ የጀግኖቹ መፍለቂያ ሀገር ኢትዮጵያም በምፅሃት ምድር እና ሰማይ እስኪያልፉ ድረስ ሲዘከሩ ይኖራሉ። ባላቤታቻዉ ድንቋ ጣይቱም፤ ልጃቸዉም ዘዉዲቱም፣ ወጣቱ ሕልመኛም እያሱ ታሪክ ያስታዉሳቸዋል።
ተፈሪ መኮንንም በዲፕሎማሲዉ ስለ ኢትዮጵያ ሲሉ ተዋድቀዋል። በስደት ተንገላተዋል። ከአፍሪካ ሕብረት እስከ ዤኔቭ ያሰሙት የነፃነት ድምፃቸዉ እና ሮሮቸዉ ለዘመናት ሲያስተጋባ ይኖራል።
መንጌም ለእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ የተዋደቀ አቀኛ መሪ ሆኖ የሚዘከር ብቻ ሳይሆን ለጥቁር አፍሪካዊያን ነፃ መዉጣት ሲል ከዙንባቡዬ እስከ ደቡብ አፍሪካ ያሉ የነፃነት ታጋዬችን አሰልጥኖ ያስታጠቀ ጀግና በመሆን ይዘከራል። በቀይ ሽብር ከጎደፈዉ ማንነቱ ባሻገር የካራማራና የሰሜን ኤርትራ ተራሮች ጀግንነቱን ሁሌም ይዘክራሉ።
መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያዊ መሪ ወይም ኢትዮጵያዊ ሆኖ አያዉቅምና  ታሪክ ዘመኑን የጭለማ ዘመን ብሎ ይሰርዘዋል። አልያም ሃያ ሰባት ዓመታቱ የኮዳ ማንጠልጠል ቆርፂ ቆርፂ ዘመን ልክ ጣሊያን ለአምስት ዓመታት በወረራ ኢትዮጵያ የቆየችበትን ዘመን ተምሳሌት ይሆናል:: ኃይለማሪያምም ቢሆን ወኔ አልባ የባዶ ዘመን መገለጫ አድርጎት ያልፋል።
አቢቹ አባ ቢያ አባ መላ ደግሞ የቀድሞዉን የጀግንነት ማንነታችንን ያስቀጠለ ኩሩና ቆራጥ ኢትዮጵያዊ አድርጎ ታሪክ ይዘክረዋል። ማንም ወሮበላና አጭበርባ ዲሲና ቨርጂኒያ ተቀምጦ ዛሬ ምን ተወራ ብሎ ቡና ቁርስና ቡና በሌለበት ሐሜት እንደሚተረተረዉ ሳይሆን አቢቹ አባ ቢያ አባ መላ በአፋር ወንበዴን ድል ነስቶ በሰሜን ሸዋ ተቅማጥ አሲዟቸዉ በጋሽና ወንበዴን አይቀጡ ቅጣት የቀጣ የዘመናችን ዐፄ ወይንም በአሜካኖቹ አጠራር አብርሃም ሊንከናችን ሆኖ ይዘከራል። ሊንከን ብዙ ኃጥያት የተሸከመ ግን አሜሪካንን ከመበታተን የጠበቀ የባሪያ አሳዳሪ ነበር። አቢቹ አባ ኪያ አባ መላም ከብዙ ድክመቱ ጋር ለኢትዮጵያ ግንባሩን ሰጥቶ ኢትዮጵያን ከመበታተን የታደገ መሪ ነዉ። ነጮች የሚያንቆለጳጵሱት ሊንከን በርካታ መቶ ሺዎችን ገብሮ ነዉ ታላቋን ሀገር አሜሪካ ለዛሬ ያቆየዉ። በአቢቹ አባ ቢያ አባ መላም ዘመን ብዙ መቶ ሺዎች ተሰዉተዋል። ኢትዮጵያ ግን ተርፋለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሆይ ላደረጉት ኢትዮጵያን የማስቀጠል ተጋድሎ አመሰግናለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር።
Filed in: Amharic