>
5:14 pm - Friday April 20, 0159

"ጦርነቱ ይቁም አይቁም በሚል  የብልፅግና አመራሮች  ተከፋፈሉ... !!!" (ወልቃይት ጠገዴ አማራ ሚድያ)

“ጦርነቱ ይቁም አይቁም በሚል  የብልፅግና አመራሮች  ተከፋፈሉ… !!!”

ወልቃይት ጠገዴ አማራ ሚድያ

 
*… የአማራ ክልል መንግስትም ክልላችን ከወራሪው ሳናፀዳ የሚቆም ጦርነት የለም ብሏል! ሕዝብ መጠየቅ፣ መንቃት አለበት፣ ዳግም መበላት የለበትም 
 
*… የአማራ ማህበረሰብ ወያኔ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እነርሱን እንዲተዋቸው፡፡ “አብይና ኦህዴዶች ይደርሳሉ፣ አሁን ወያኔ ላይ እናተኩር” እየተባለ ለአመታት እንዲቀጠል ነው የሚፈልጉት
ዶር አብይ አህመድ ለመከላከያ ባለህበት ቁም፣ ተኩስ አቁም:  የሚል ትእዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ ከብዙ አቅጣጫ ከፍተኛ ተቃውሞን እያሰተናገደ ነው። ብዙዎች  ሕወሃትን ለማስቀጠል  ፣ የአማራንና የአፋር ክልል ሕዝብ በዘላቂነት በስጋት እንዲኖር ለማድረግ፣ የተወሰደ ውሳኔ  ነው እያሉ ነው።
ይህን ትእዛዝ  የብልጽግና የስራ አመራር ፣ ወይንም የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ወይንም ፓርላማው ተነጋገረውበት የተሰጠ ትእዛዝ ወይም ውሳኔ  አይደለም።፡ ሙሉ ለሙሉ የዶር አብይ አህመድ የግሉ ውሳኔ ነው።
በአሁኑ ወቅት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ የሚሰጡት የተምታቱ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ የመንግስት ሃላፊዎች አስተያየቶች  እንደሚያመላክቱት፣ በዚህ ጉዳይ ላይ የብልጽግና መንግስት እርስ  በርሱ በጣም የተከፋፈለ ነው።
ለምን ይሄን ትእዛዝ እንደሰጠ ዶር አብይ ለማስረዳት ረጅም ሃተታ ያለበት አንድ ጦማር ፌስ ቡኩ ላይ ለጥፏል።
በዚህ ጦማር ዶር አብይ አንድ ቦታ “አሸባሪውን ሕወሐት ከአማራና ከአፋር ክልሎች በማስወጣት የመጀመሪያውን ግብ አሳክቷል” ሲል ፣  ሌላ ቦታ ደግሞ “ጠላት ከወረራቸው አካባቢዎችም ተጠራርጎ ወጥቷል” ሲል ጦርነቱ ማለቁንና መቀልበሱን ነው የገልጸው።
ለዚህም እንደ ምክንያት አድርጎ የጠቀሰው በዋናነት እራሱን ነው። “ይሄንን ወረራ ለመቀልበስ እንዲቻል፣ ለዝግጅት በቂ ጊዜ ወስደን፣ የአመራር ጥበብን፣ የተቀናጀ ዕቅድንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም፣ የደረሰብንን ወረራ ስንከላከል ቆይተን የጥፋት እርምጃውን ቀልብሰነዋል” ይላል። በኔ አመራር ብቃት፣ እኔ ከቱርክ ባስመጣሁት ድሮችን ወዘተ ማለቱ ነው። “እኔ መሪያችሁ ባልሆን ኖሮ ፣ ባልዘምት ኖሮ …ይሄኔ ኢትዮጵያ አትኖርም ነበር” ብሎ የሚያስብ ይመስለኛል።
እውነታው ግን ከወዲህ ነው። የአየር ኃይል ድሮኖችና ጀት ጥቃቶች ትልቅ ሚና የነበረባቸው ቢሆንም፣  ወያኔ አዲስ አበባ እንዳትገባ ያደረጉት በዋናነት የአፋርና የአማራ ህዝባዊ ኃይሎች ናቸው። ዶር አብይ አህመድ እነዚህ ኃይሎች ባይኖሩ ኖሮ አገር ጥሎ ኢሜሪት ነበር ይሄን ጊዜ።
ታዲያ እውነታው ይሄ ሆኖ እያለ  ዶር አብይ አህመድ፣ በዋናነት ጦርነት የተቀለበሰው በአፋር፣ በአማራ ሚሊሺይዎች፣ በፋኖዎች፣ በአማራና በአፋር ልዩ ኃይሎች፣ በራሳ ገበሬዎች፣ በራያ ፣ በጎንደር ገበሬዎችና በአፋር አርብቶ አደሮችች፣ በአጠቃላይ  በሕዝብን ኃይል መሆኑን ለመግልጽ ለምን አልቻለም ? መንግስት የተፈጠረውን አደጋ በመደበኛ ሰራዊት መመከት አንችልም በሚል ለሕዝብ ጥሪ ማቅረቡን እንኳን ዶር አብይ መልሶ ለማስታወስ ለምን አልሞከረም? ለምንስ በዚህ መልኩ መመጻደቅና ራሱን ማግነንና መካብ ፈለገ ?
ሌላው ዶር አብይ ውሳኔውን  ለማስረዳት በለቀቀው ጦማር በርካታ ውሸቶችንም አካቷል። “(ወያኔ) ከወረራቸው ቦታዎች ተጠራርጎ ወጥቷል” ያለው ለምሳሌ ማየት እችላለን:: ፍፁም ውሸት ነው። አሁንም ወያኔ ወራ በያዘችው ቦታዎች ላይ አለች። በስሜን ጎንደር አዳርቃይት ወረዳ ወያኔ አሁንም አለች። በጠለምትና በራያ አሁንም አለች።
ወገኖች፣
1ኛ ስለ ብልጽግና ፓርቲ ብዙ ውስጥ ውስጡ የማናውቀው ነገር አለ። ብዙ እየተዋሸን ነው። ሕዝብ መጠየቅ፣ መመርመር መችል አለበት። የፖለቲካ ድርጅቶች በድፍረት መንግስት ቻሌንጅ ማድረግ መቻል አለባቸው። ኢዜማ፣ አብን ብልጽግናን አምናችሁ መቀመጥ የለባችሁም። አንዳንድ አመራሮቻችሁ ስልጣን ስላገኙ።
2ኛ መንግስት ወር በፊት ጉድ እንዳደረገን ደግመን ጉድ መሆን የለብንም። መደራጀት፣ መታጠቅ፣ መንቃት አለብን።
አብን፣ እንደገና በቶሎ እንዲሰባሰብ ቢጠይቅና የብልጽግና መንግስት በወሰደው አቋም ላይ ውሳኔ ማሳለፍ ቢቻል ጥሩ ነው።
የአብይ መንግስት ብቻዉን ወስኖ ህዝቡን ለመከራ ዳርጓል፡፡ አሁንም ህወሃት እንድትቀጥል ያደረገው ውሳኔም ፍጹም የተሳሳተ ውሳኔ ነው፡፡ በሕዝብ ላይ የተፈጸመ ክህደት ነው፡፡ ሕዝቡ ተረጋግቶ እንዳይኖር፣ ልማት ላይ እንዳያተኩር፣ ከአሁን ለአሁን ዛሬ፣ ወይም ነገ ወያኔ መጣች ብሎ በስጋት እንዲኖር የሚያደርግ ነው፡፡ ጦርነቱን በዘላቂነት የሚያስቀጥል ነው።
እነዶር አብይ ያንን ይፈልጉ ይሆናል፡፡ የአማራ ማህበረሰብ ወያኔ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እነርሱን እንዲተዋቸው፡፡ “አብይና ኦህዴዶች ይደርሳሉ፣ አሁን ወያኔ ላይ እናተኩር” እየተባለ ለአመታት እንዲቀጠል ነው የሚፈልጉት፡ በአዲስ አበባ፣ በሸዋ ፣ በድረዳዋ፣ በሃረር ወዘተ የፈለጉትን ለማድረግ እንዲያመቻቸው፡፡ ሰዎቹ አቅደው ነው የሚንቀሳቀሱት፡፡
አብኖች ከሞቱበት ተነስተው አሁንም የህዝብን ጥያቄ ይዘው እንዲነሱ እጠይቃለሁ፡፡ አቶ በለጠንና አቶ ዩሲፍን በማሰናባት አዲስ አመራር በቶሎ በመመረጥ የፖለቲካ ትግሉን መመራት መጀመር አለባቸው፡፡
በተለይም በአስቸኳይ የኦህዴድ ብልሽኛና ውሳኔ መቃወም አለባቸው
Filed in: Amharic