>
5:26 pm - Sunday September 17, 7167

የጦርነቱ ኪሳራ ለምን በጦርነት ሰለባ በሆኑ ክልሎች ላይ ብቻ ይወድቃል? (ሸንቁጥ አየለ)

ጦርነቱ የፌደራል መንግስቱ እና የህዉሃት
— ኪሳራዉ ለምን በጦርነት ሰለባ በሆኑ ክልሎች ላይ ብቻ ይወድቃል?
ሸንቁጥ አየለ

የአማራ ክልል በጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ከጠዬቀዉ በጀት 0.33% ብቻ ተፈቅዶለታል። ከ1% ያነሰ ማለት ነዉ
1–የብልጽግና መንግስት በጦርነት ለወደሙ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋም ብሎ 5 ቢሊዮን ብር መድቧል::በጦርነት የወደሙ የሚባሉት ለአማራ: ለአፋር እና የትግራይ ክልል ናቸዉ::
ይሄ መንግስት መደብኩት የሚለዉ ገንዘብ ለሶስቱ ክልሎች እኩል ቢከፋፈል ለያንዳንዳቸዉ 1.65 ቢሊዮን ብር ይደርሳቸዋል። ለአማራ ክልል 1.65 ቢሊዮን ብር ደረሰዉ ማለት ክልሉ ከጠየቀዉ 500 ቢሊዮን ብር ዉስጥ 0.33% ብቻ ነዉ የተመደበለት ማለት ነዉ።ይሄም ማለት ክልሉ የጠዬቀዉ አንድ ፐርሰንት /1%/ እንኳን አልተፈቀደለትም።
2–የአማራ ክልል በጦርነት በወደሙ በተወሰኑ ወረዳዎች ላይ ብቻ ባደረገዉ ቅድመ ዳሰሳ ለመልሶ ማቋቋም 500 ቢሊዮን ብር(አምስት መቶ ቢሊዮን ብር) ያስፈልገኛል ሲል ጠይቋል:: ይሄም ማለት የአማራ ክልል ከጠየቀዉ 500 ቢሊዮን ብር ዉስጥ የተመደበለት ከ1% እንኳን ያነሰ ነዉ ማለት ነዉ::
3–በርግጥ ይሄ ብር ብዙ ቢመስልም ኢትዮጵያን ለምታህል ትልቅ ሀገር ብዙ ብር አይደለም::በጦርነት የወደሙ አካባቢዎች ቅድሚያ ከተሰጣቸዉ ብር ሞልቷል::ለማሳያነትም ለአንዳንድ አካባቢዎች ለወጣቶች በነፍስ ወከፍ እና በቡድን ትራክተሮች እየተገዙ እየታደሉ መሆኑን ስናይ ይሄ በጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የተጠዬቀዉ ብር ብዙ ብር አይደለም::
4—ሆኖም ቀልደኛዉ ኦህዴድ መር የብልጽግና መንግስት የአማራ ክልል ከጠዬቀዉ በጀት 0.33% (ዜሮ ነጥብ ሰላሳ ሶስት ፐርሰንት) ብቻ ለፕሮፖጋንዳ መስሪያነት ወርወር አድርጎ የብ አዴንን ባንዳ ሹማምንት ምላሽ አፍጥጦ እየተመለከተ ነዉ::
5–ብአዴን እንደሆነ አይበርደዉ አሞክቀዉ::ህዝብ በጦርነት ወድሞ ዝም ነዉ::አማራ በመላዉ ሀገሪቱ ሲጨፈጨፍ እያዬ ጭጭ ነዉ::
————-
6–ለማንኛዉም የብልጽግና መንግስት የሚሰማ ከሆነ ቀልዱን አቁሞ በጦርነት ለወደሙ የአማራ:የአፋር እና የትግራይ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋሚያ አፋጣኝ በጀት ይመድብ::ሀብት ሞልቷል::በብድርም:ህዝብን በማስተባበርም:አለም አቀፍ ማህበረሰብ ብሎም ወዳጅ ሀገራት እርዳታ እንዲያደርጉ በመጠዬቅም ህዝባችንን በአፋጣን የማቋቋም ስራ ይሰራ::
7—አሁን ይሄን የኦህዴድ ካድሬ/የብልጽግና መንግስት ዋነኞቹ ዘዋሪዎች/ ሲያነቡት ምን እንደሚያስብ በደንብ አዉቃለሁ::እኛ ሌላዉ ተበትኖ ቢያልቅ ምን አገባን እያሉ ይሳለቃሉ::
8. ለማንኛዉም በዚህ ጦርነት ከሁሉም ወገን በላይ በጣም ያተረፈዉ ኦህዴድ የመንግስትነት መንበረ መንግስቱን ማስጠበቅ መቻሉን ተረድቶ ይሄ ሁሉ ሀገራዊ ዉድመት የተከናወነዉም በኦህዴድ(በብአዴን ታኮ ያዥነት) እና በህዉሃት መሃከል በተነሳ የስልጣን መነጣጠቅ ጣጣ መሆኑን ተረድቶ በአፋጣን ሀገሪቱን ይሄ አካባቢ ያ አካባቢ ከሚል ዘረኛ ህሳቤ ወጥቶ በጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን እንደገና እንዲገነባ በጥብቅ ሊመከር ይገባዋል::
_____________
9.ጦርነቱ የፌደራል መንግስቱ እና የህዉሃት እንጂ የትግራይ ክልል እና የአማራ ክልል እንዳልሆነ ይታወቃል። ሆኖም ብልጦቹ ኦህዴዶች የጦርነቱን ኪሳራ ለአማራ ክልል እና ለአፋር ክልል አሸክመዉ ዘወር ብለዋል። የወደመዉን ክልል መልሶ ለማቋቋም ከአንድ 1% በታች በጀት ለፕሮፖጋንዳ ማራመጃ ፈደራል መንግስቱን የሚያጦዘዎ ኦህዴድ መድቧል።
10.እንቅልፋሙ ብአዴን ለሽ ብሎ ተኝቷል።ነፈዙ የብአዴን ካድሬ ይሄን ነገር መንግስትን ወጥሮ ከመጠዬቅ ይልቅ አሁን እዚህ እኔ ጽሁፍ ስር መጥቶ እኔን ይሳደባል። የ እንሰሳት እርሻ /አኒማል ፋርም/ የሚለወ መጽሃፍ ዉስጥ ያሉ አሳማዎች በፖለቲካ ንቃተ ደረጃቸዉ የብአዴን ካድሬዎችን እና አመራሮችን ይበልጧቸዉ ይመስለኛል። እነሱ እስካልተራቡ ለሽ ነዉ። ከእንቅልፋቸዉ እንዳይቀሰቀሱም  ሁሉ ዝም እንዲል ከእንቅልፋቸዉ ሲነቁ ዝም በሉ ብለዉ ይጮሃሉ።
Filed in: Amharic