>

ቀንዱ ላይ የተንጠለጠሉት እነ አሜሪ!? (ሞሀ ሞሰን)

ቀንዱ ላይ የተንጠለጠሉት እነ አሜሪካ⁉

ሞሀ ሞሰን

አሜሪካና ወዳጆቿን፣ እንዲሁም ተላላኪ ሚዲያዎቻቸውን እጅግ አብዝቶ የሚያሸብራቸው ከ3 ዓመት ወዲህ በሶስቱ መሪዎች የታየው ሰላምና ፍቅር ነው። ፋርማጆ፣ ዐብይ እና ኢሳያስ ያላቸውን የእርስበርሰ ግንኙነት ከመጠየቅ ተሻግረው ይበሳጫሉ! የነሱን በሰላማችን መቅናት እንደቀጠናው መናጋት እንድንቆጥርላቸው ይለፋሉ!
ከኤርትራ የሚሱት ወሬዎች ሁሉ ይረብሿቸዋል። ከኢትዮጵያና ቀንዱ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሀገራት ላይ ሁሉ ጨርቃቸውን ይጥላሉ። አውሮፓ ህበረት ኤርትራን ለምን ይረዳታል ይሉናል
የዘገባዎቻቸው ተንኮለኛነትና አነካኪነት ሲበዛ እኩይነታቸውን ይናገራል። ሚዲያ ነን የሚሉ አፎቻቸውም፣ በዜና ፈንታ ቀጠናው ጦር መሳሪያ ያርከፈክፋሉ! ሽብር ማቀነባበር ዋና ስራቸው ይመስላል። ከቀጠናው የሚነሳው ፍትሀዊ ጥያቄ ሁሉ ለእነሱ ቀጠናውን ለቀውስ መዳረግ ተብሎ ጉድ ጉድ እየተባለ ይተረጎምብናል።
የዘ ኢኮኖሚስቱ ቶም ጋርድነርና መሰሎቹም፣ ዘጋርዲያን ላይም ብቅ ብለው ኢትዮጵያ ጥቅሟን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ትግል ጭምር ቀጠናውን ለማመስ አንደተነሳች አድርገው የነገሩን ከዓመት በፊት ነው።
የማርቲን ፕላውት ግን ከሁሉም ይለያል! የኤርትራኸብ ድረገጽ ባለቤቱ ማርቲን ፕላውት የማይደረድረው የማስፈራሪያ መአት የለም። “የአፍሪካ ቀንድ አለቀለት!” ሲለን ሁለት ዓመት አለፈው። የእነ ሬኔ ሌፎ ትዊት ጭምር በምስክርነት እየቀረበ ማስፈራሪያና ውሸቱን ይግቱናል።
ከኤርትራ ጋር የተባበሩት መንገስታት የፈረደውን ተቀብለን ቀጠናውን ወደሰላም ለማምጣት ትልቁን እርምጃ የተራመደው ጠቅላይ ሚኒስትር እየወቀሱ … ቦታውን ከጦር ካምፕነት ነጻ አላደርግም ያለውን ቡድን ግን ለመኮነን ዜናቸው አይታዘዝላቸውም።
ዛሬ ፊታቸውን ያዞሩባት ሶማሊያ የራሳቸው የከሳሾቹን ግፍ አድምቆ የሚተርክ ነው። #ሶማሊያን እርስ በ’ርስ ከጌቶቻቸው ከነ አሜሪካ ጋር ሆነው፣ ሲያጋጩና ሲያጋድሉ የከረሙት ሰው በላዎቹ ህወሓቶች መሆናቸውን እንድንረሳ ይጋጋጣሉ። ጭራሽ የነሱን መወገድ ለቀጠናው መተራመስ ዋነኛ ምክንያት አድርገው ይደልቃሉ። የህወሓትን ሞት ለመከላከል ከሚያቀርቡዋቸው ተራና ቀሽም መከላከያዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው፣ “ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ማዕከል ናት፣ ህወሓትን መንካት ቀጠናውን ያናጋዋል” የሚለውን ብንፈትሸው መልሱ አሳፋሪ ነው። እኛም እዚህች ጋር ሳቃችንን እንደምንም ተቆጣጥረን፣ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ብንሰነዝርላቸው፣ መልሱን አይደለም ከቀንዱ ከየትም አያመጡትም
– ቀጠናው ከአለም በስደተኞች ብዛት ከዋናዎቹ ተርታ አይደለምን?!
– በውስጥም ወደውጭም በማሳደድ የሚወዳደረው አለ!?
– ስንቱ ጎረቤት ነው በሰላም ተግባብቶ የሚኖረው? !?
– ኤርትራ ለ20አመት ተከርችማ ተቀምጣ፣ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ልትሚያ ውስጥ አልነበረችም!?
– ሶማሊላንድ ለሩብ ክፍለ ዘመን ያለእውቅና አይደል እንዴ ያለችው?!
 – ሶማሊያ በቋፍ፣
– ጅቡቲ በወታደራዊ ፍጥጫ፣
– የመን በማያባራ ጦርነት፣
– ደቡብ ሱዳን እንደ እድር በየሳምንቱ ጠብ፣
– ሶማሊያ ከኬኒያ አንዲት ቀን ሰላም ውለው አያድሩም።
– ሰሜን ሱዳን ገና ድክ ድክ እያለች፣ ደቡብ ሱዳን ሶማሊያ እና የሳህል ቀጠና በሰላም አስከባሪ አይደለም እንዴ ውሎ አዳሩ?…
እና ሰላም ምንድነው!?
ምኑ ነው የሚናጋው!?
በየዓመቱ ድርቅ፣ ጎርፍ፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ … እየወገረው፣ ህገወጥ ንግድ ህጋዊ ሆኖ፣ ሀገራዊ እዳ አጉብጦት፣ መዋቅራዊ ሙስና ከራስ አስከ እግሩ ወርሮት፣ በስርአታዊ መበስበስ ወላልቆ፣ በጎሳ ጦርነቶች ቀን ከሌት እየባነነ፣በዘር ተኮር ፖለቲካ ሰርክ እየታመሰ፣ የህጻናት መቀንጨር እንደ ተላላፊ በሽታ ከአመት አመት እያዳከመው፣ የትምህርት ሽፋኑ ከአለም ዝቅተኛው አይደለምን!? …
— ታዲያ ምኑ ነው የሚናጋው!?
▬▬▬▬▬▬▬
#NoMore #USA #HornOfAfrica #Eritrea #Somalia #WakeUpAfrica
Filed in: Amharic