>
5:21 pm - Sunday July 20, 6752

"ብኩርናውን የሸጠ የሕዝብ መሪ መሆን አይቻለውም...!!" (ወንድወሰን ተክሉ)

ብኩርናውን የሸጠ የሕዝብ መሪ መሆን አይቻለውም…!!”

ወንድወሰን ተክሉ

*….  የአማራን ብሄርተኝነታዊን የህልውና ትግል ከኤሳዊያን፣ከይሁዳዊያን እና ከጲላጦሳዊያን የማጽዳቱ አስፈላጊነት የቅድሚያ ቅድሚያ ተግባር መሆን አለበት!!!
የአማራን ብሔርተኝነት በመፍጠር የመሰረተ ድንጊያ ያኖሩት ታላቁ ምሁር ፕ/ር አስራት ወልደየስ «የአማራ ሕዝብ ጠላት ሆዳሙ አማራ ነው» ብለውን ነበር።  እስቲ ሆዳም አማራን እና ሆዳምነትን  ዘርዘር አድርገን በማየት ሆዳም አማራ የአማራ ሕዝብ ጠላት ነው ሲባል ይህንን አይነቱን አማራ ለይቶ ማወቅና መለየት አስፈላጊነቱ ጎልቶ ይቀርባልና ሆዳምነት ምን ማለት ነው ብለን ልንጠይቅ እንችላለን።
ታላቁ ፕ/ር አስራት ወልደየስ የአማራን ሕዝብ ጠላት «ሆዳሙ አማራ ነው» ብለው የገለጹትን እኔ ኤሳዊያን፣ይሁዳዊያን እና ጲላጦሳዊያን በሚል አገላልጽ እነዚህን ስብእናዊ ማንነቶችን ከአማራ ብሄርተኝነትና የህልውና ትግሉ መስመር ካላጸዳን በ1966 የጀመረው የህዝባችን ስቃይ፣ጭቆና፣ጭፍጨፋና ባርነት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሸጋገርበትን ሁኔታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ Consciously or unconsciously የምንተባበር የመሆናችንን ሀቅ በግልጽ ለማስፈር እወዳለሁ።
ባርነት  ስል ምን ለማለት እንደፈለግኩ በመጀመሪያ አጠር አድርጌ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።  ባርነት የሚለው ቃል ባሪያ ከሚለው ስርወ ቃል የመጣ ሲሆን ባሪያ ማለትም አንድ ሉዓላዊ የሆነ ግለ ተፈጥሮዓዊ ስልጣንና መብቶቹን ተነጥቆ በራሱ ግለ ፍላጎት፣ፍቃድ፣ዓላማና እምነት የማይኖርና እነዚህን ተፈጥሮዓዊ ስልጣንና መብቶቹን ተነጥቆ በሌላ ሰውም ሆነ ኋይል ፍላጎት ፍቃድና ጥቅም ሲል የሚኖር ተገዢ የሆነ ሰው ጥንት በገንዘብ ሲሸጥና ሲገዛ የነበረን ሰው የሚገልጸውን ባሪያን እና ባርነትን የሚገልጽ ነው። ባርነት እንደጥንቱ ነጩ ጥቁሩን የሚሸጥበትና የሚገዛበት ብቻ ሳይሆን ወይንም በሀገራችንም አንድ ሰው ሌላውን ሰው በገንዘብ ሸጦ ወጥም ገዝቶ የግል ሀብትና ንብረቱ አድርጎት እንደሚገልጸው ባሪያ አይነት ትርጉም ያለው ማለት ሳይሆን ማንኛውም ሰው ሆነ ህዝብ ወይም ማህበረሰብ ወደዚህች ምድር ሲመጣ ይዞት የመጣውን ተፈጥሮአዊ የሆነ ሉዓላዊ ስልጣን፣መብት፣ጥቅምና ማንነቱን በነጻነት መጠቀም አቅቶት በሌላ ሰውና ኋይል ተነጥቆ ያለን ተገዢ የሆነ ሰውና ህዝብ በባርነት ውስጥ ያለ ህዝብ ነው በሚል እሳቤ ነው የሕዝባችንን ሁኔታ  በባርነት ውስጥ ያለ በሚል ለመግለጽ የፈለግኩት።
ታላቁ የአማራ ሕዝብ ከ1966 ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በደርግና በኢህአዴግና በብልጽግና በሚባሉ ጸረ አማራ ኋይሎች ስር በባርነት እየማቀቀ ያለ ህዝብ ነው እንጂ በራሱ ጉዳይ እራሱ እየወሰነ እራሱን እየመራ ያለ ሕዝብ ባለመሆኑ በውስጡ በርካታ ኤሳዊያንን፣ይሁዳዊያን እና ጲላጦሳዊያን ተፈጥረው የየራሳቸውን ጨቌኛዊና አስጨቌኛዊ ሚናን ሲጫወቱ ለማየት ችለናል።
አማራ ከ1966 ጀምሮ በጸረ አማራ ኋይል ስር የወደቀ ነው ብንልም ከ1983 ጀምሮ ግን ህዝባችን «የአማራ ሕዝብ ጠላቴ ነች-መቼም ቢሆን እረፍት አንሰጣትም» የሚለውን አቌም የሀገሪቱ ስነ መንግስት መተዳደሪያ ሕገ መንግስት አድርጎ በሚገዛ የለየለት የአማራ ጠላት ኋይል እየተገዛ ያለ ሕዝብ በመሆኑ ይህንን 30ዓመት የአማራ ሕዝብ የባርነት ዘመን ብለን መግለጽ ይቻለናል።
የአማራን የባርነት ዘመን በጉልህ ከሚገልጹ ክስተቶች ውስጥ አማራው ከሁለትሺህ ዘመናት በላይ እውቀቱን፣ባህሉን፣ሀብትና ጉልበቱን እየሰጠ የሀገረ ኢትዮጲያ ስነ መንግስትን በገነባበትና ይህንንም የገነባውን ሀገረ መንግስት ለሺህ ዘመናት ህይወቱን ገብሮ፣ደሙን አፍሥሶና አጥንቱን ከስክሶ በነጻነት ጠብቆ እዚህ ባደረሰበት ሀገር አማራው በዚህ 30ዓመት ውስጥ ከአራቱ ክፍለ ሀገር (በሸዋ፣በወሎ፣በጎንደርና በጎጃም) በስተቀር በተቀሩት አስር/ዘጠኝ ክፍለ ሀገራት ውስጥ የሀገሩ ባለቤት ያልሆነ፣መጤ፣ሰፋሪና የዜግነት መብት የሌለው ህዝብ ተደርጎ በማንነቱና በእምነቱ ብቻ እየተመረጠና እየተለየ የሚጨፈጨፍ ሕዝብ የሆነበትን የባርነት ዘመን ነው ዛሬ ያለንበት አገዛዝ።
ዛሬ ሀገረ መንግስቱን እየገዛ ያለው ኢህአዴግ ቁጥር 2 የሆነውና እራሱን ብልጽግና (ኦህዴድ/ብአዴን) እያለ የሚጠራው ኋይል ሀገረ መንግስቱን እየገዛበት ያለው ሕገ መንግስት የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ከ20ሚሊዮን በላይ የሆነውን አማራን ዜግነት አልባ በማድረግ ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ተወስኖ እንዲታሰር በተደረገበት የሰሜን ሸዋ፣የወሎ፣የጎጃምና የጎንደር ክፍለሀገራት ለአማራው ይበዛበታል በሚል ሰፊ ጸረ አማራ ዘመቻ በከፈተው የለየለት የአማራ ጠላት የኦህዴድ/ብአዴን ብልጽግና እየተገዛ ያለበት አስከፊ የባርነት አገዛዝ ውስጥ እየማቀቀ ያለ ህዝብ ነው።
በ1984 ላይ በታላቁ ምሁር ፕ/ር አስራት ወልደየስ የተጀመረው የአማራ ብሄርተኝነታዊ ንቅናቄና ትግል አማራው ከተጋፈጠው ጠላት አቅም ጉልበትና ኋይል ጋር ሊመጥን በሚችል መልኩ ታግሎ ማታገል ሳይችል ቀርቶ እንደ ኤሊ እየተንቀረፈፈ  እስከ 2008 ድረስ ከተጔዘ በኋላ ሀምሌ 5ቀን 2008 በአማራዊቷ ጎንደር ከተቀጣጠለው የአማራ ሕዝባዊ ተጋድሎ በኋላ ላለፉት አራትና አምስት ዓመታት የህልውናው ትግሉ ከመቼውም ግዜ በላይ ተቀጣጥሎ እየተጧጧፈ ያለበትን ሁኔታ እንረዳለን።
አማራን በጠላትነት ፈርጆ አማራ መጥፋት አለበት በማለት መጠነ ሰፊ የጥፋት ዘመቻን ትናንት ህወሃት ኢህአዴግ እና የዛሬው ኦህዴድ ብልጽግና   ይህንን ጸረ አማራ ዘመቻውን ለመፈጸምና ለማስፈጸም የተጠቀመውና እየተጠቀመ ያለው፦
👉 ሕገ መንግስት
👉 የኢትዮጲያ ህልውና
👉ብአዴን
👉 አዴፓ
👉ሆዳምነትአድርባይነት፣ምን አገባኝነትና እኔ አማራ ሳልሆን ኢትዮጲያዊ ነኝ ባይነትን
👉ኤሳዊያን፣ይሁዳዊያን እና ጴጥሮሳዊያንን  በመጠቀም ነው የትናንቱ ህወሃት/ኢህአዴግ እና የዛሬው ኦህዴድ/ብልጽግና አማራን ከምድረገጽ አጥፍቶ አማራዊ ማንነቱን ሞራሉን ክብሩን፣ታሪኩን እና እምነቱን አፈራርሶና አጥፍቶ ምቹ ተገዢ ባሪያ ለማድረግ እየሰሩ ያሉት።
በዚህ ሰላሳው ዓመት ጸረ አማራዊ አገዛዝ ውስጥ እናትና ልጅ የሆኑት ሁለቱ የአማራ ጠላቶች -ማለትም የትናንቱ ህወሃትና የዛሬው ኦህዴድ ጸረ አማራ ዘመቻቸውን የፈጸሙትና እየፈጸሙ ያሉት በዋነኝነት በሕገ መንግስቱ ቢሆንም እታች ምድር ላይ ወርዶ ጸረ አማራ ዘመቻን በተግባር በመፈጸም ደረጃ ብአዴን/አዴፓ ሆዳም አድርባይ፣ፈሪ ምን አገባኝ፣እኔ አማራ ሳልሆን ኢትዮጲያዊ ነኝ በሚሉ አማራዊያን የተጠቀሙ ሲሆን እነዚህን አማሮች ኤሳዊያን፣ይሁዳዊያን እና ጲላጦሳዊያን ብዬ ነው የምገልጻቸው።
፠ በአማራ ብሄርተኝነታዊ የህልውና ትግል ውስጥ ኤሳዊያኑ፣ይሁዳዊያኑና ጲላጦሳዊያኑ እነማን ናቸው ?
በታላቁ ምሁር ፕ/ር አስራት ወልደየስ የተገለጸው የአማራው ጠላት «ሆዳም አማራው ነው» የሚለው አገላለጽ  ብኩርናውን ስልጣንና ማእረግን በአንድ የምስር ወጥ ምሳ እንደሸጠው ሆዳሙ ኤሳው – የአማራ ኤሳዊያን ብዬ የምገልጻቸው በአማራ ኤሊት፣በአማራው ምሁራን ስብስብ፣በተቃዋሚው ጎራና በፌዴራሉ መንግስት ውስጥ ተሰግስገው ያሉትን አማራ ተወላጅ የሆኑ ባለስልጣናትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ይመለከታል።
የአማራ ይሁዳዊያን ስንል ደግሞ የአለምን አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ ዓለምን የማዳን ኋይልና ስልጣንን አውቆ ደቀመዝሙሩ እስከመሆን ደረጃ ላይ ደርሶ ይህንን የዓለምን አዳኝ መሲህን በሰላሳ ዲናር አሳልፎ የሸጠው ይሁዳ ተግባርና ስብእናን የሚወክሉ አማራዊያን ከአማራ አብራክ ተወልደውና በአማራ አስተዳደግ አድገው የታላቁን የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ አቅም፣ ብቃት፣ኋይል፣ታሪክ፣ሀገራዊ ድርሻና ሚናን ጠንቅቀው አውቀው በአንድ መንገድም ሆነ በሌላ መንገድ ይህንን ህዝብ በፖለቲካ፣በማህበራዊ ዘርፍና መሰል ለመምራት ተንቀሳቅሰው ታማኝነታቸውን ግን ለቅንጥብጣቢ ግለ ስልጣንና የቁስ ጥቅም ብለው ለአማራ ጠላት አድርገው ትግሉን እንደ ግመል ሽንት የኋሊት በመመለስ ተግባር ላይ የተሰለፉት የአማራ ይሁዶች ብለን እንለያቸዋለን።
የአማራ ይሁዳዊያንን ለምሳሌ ለማሳየት ያህል፦
👉 የኤፌሶንን/አጣዬ ከተማን ከኦህዴድ ጋር ተስማምቶ ያስወደመውና በመተከልና በወለጋ በግፍ ለተጨፈጨፉ ሺህ አማሮች ጭፍጨፋ ሽመልስ አብዲሳንና አሻድሌ ሁሴንን ጠርቶ በመሸለም ያመሰገናቸው አገኘሁ ተሻገር
👉 ፋኖ አስቻለው ደሴን ጨምሮ በርካታ ፋኖዎቻችንን የገደለው ተመስገን ጥሩነህ
👉 ጀግናችንን ብ/ጄ አሳምነው ጽጌን፣ዶ/ር አምባቸውን፣ምግር እና  እዘዝ ዋሴን በማስገደል የተሳተፉትን ደመቀ መኮንን፣ተመስገን ጥሩነህ፣አገኘሁ ተሻገር
👉 ታማኝነታችን ለአማራ ሕዝብ እና ለአብን ዓላማ ብቻ ነው ብለው የገቡትን ቃል ጥሰው ለግል ስልጣንና ቅንጥብጣቢ ጥቅም በመለወጥ ለጸረ አማራው የኦህዴድ/አዴፓ ብልጽግና  የገበሩትን በለጠ ሞላ፣ዩሱፍ ኢብራሂምና ጣሂር መሀመድ
👉 እንደ ተቌም – በአማራ ስም የሚንቀሳቀሰውና እራሱን የአማራ መሪ የሚለው ብአዴን/አዴፓ ታማኝነቱንና አገልጋይነቱን ለአማራ ህዝብ ሳይሆን ለለየላቸው የአማራ ጠላቶች ህወሃትና ኦህዴድ በማድረጉ – ብአዴን ትልቁ ይህዳ መሆኑን ነው ለአብነት ያህል ማስቀመጥ የሚቻለው።
መጨረሻ ላይ አማራዊያን ጲላጦሶች ብዬ የምገልጻቸው ኢየሱስን ከስቅላት ማዳን የሚያስችል ስልጣን እያለው ግን የኢየሱስን ንጽህናን አይቶና አውቆ መስክሮ እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ ብሎ እጁን ታጥቦ እራሱን ለማንጻት እንደሞከረው በፍልስጥኤም የሮም ሀገረ ገዢ እንደነበረው ጲላጦስ – አማራ ሆነው በከፍተኛ መንግስታዊ ስልጣን፣ማህበራዊ ተቀባይነት  እያላቸውና የአማራን ሕዝብ ፍትሃዊ ትግልና ፍትሃዊ ብሄርተኝነትን እያወቁ በምንም ማድረግ አልችልም ተልካሽ አመክኒዮ ዝም ጭጭ ብለው እራሳቸውን ላራቁ የአማራ ተወላጆችን የሚገልጽ ነው።
፠ የአማራን ብሄርተኝነታዊ የህልውናን ትግል ከኤሳዊያን፣ይሁዳዊያን እና ጲላጦሳዊያን ማጽዳት የሚገባን አሁን ዛሬ ነው!!
የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጥ- የሚለው የመሲሁ ህያው ቃልና አንድ ባሪያ ለአንድ ጌታ እንጂ ለሁለት አሳዳሪ ጌቶች ታማኝ ሆኖ አገልጋይ መሆን አይቻለውም እንዳለን የአማራን ሕዝብ የህልውናን ትግል ታግሎ በማታገል ለሁለንተናዊ  ድል ለማብቃት የመስፈርቶች ሁሉ ቁንጮ መስፈርት የሚሆነው ታማኝነትን ለአንድ የአማራ ሕዝብ ትግልና ሁለንተናዊ ጥቅም፣መብትና ስልጣን ብቻ ባደረገ ሰውና ሃይል እንዲመራ በማድረግ እንጂ ለአማራ ሕዝብ  ጠላት ከሆነ ማንኛውም ሃይል (ህወሃት፣ብአዴን፣ኦህዴድ፣ኦነግ…../ኢህአዴግ/ብልጽግና)ጋር ታማኝ አገልጋይ ሹመኛና ተጠቃሚ በሆነ ሰውና ቡድን በመምራት አይደለም።
የአማራ ሕዝብ ከሚታገለው ኋይል ጋር ታማኝ አገልጋይና ሹመኛ ሆኖ እንዴት ነው መልሶ የአማራ ህዝብ ብሄርተኛዊ የህልውና ትግልን ታግሎ ለማታገል የሚቻለው ?? የአማራ ህዝብ ጥያቄና የአማራ ጠላቶች ህወሃት፣ኦህዴድ፣ብአዴን፣ኦነግ እና ሕገ መንግስቱ እጅግ የተቃረኑ እሳትና ጭድ የሆኑ ጠላታሞች የሆኑ ሁለት የተለያዩ ፍላጎቶችና ዓላማዎች መሆናቸውን እውቅና የሰጠ አማራዊ አስተሳሰብና አሰላለፍ ነው የሚያስፈልገው።
የአማራን ተፈጥሮአዊ የጋን፣መብትና ስልጣንን ለህልውናዊ ዓላማው ጠላት አድርጎ በመፈረጅ ሕግ አውጥቶ የሀገር መተዳደሪያ ያደረገን ሃይል የአማራ ሕዝብ ብሄርተኝነታዊ የህልውና ትግልና ጥያቄ አጋርና ደጋፊ አድርጎ የመቀበል ሁኔታ የህልውናውን ትግል ለስኬት እንዳይበቃ አድርጔል። በተለይም ዛሬ የአማራ ሕዝብ በኦህዳድ/ብአዴን ብልጽግና አስወራሪነት እና በጭራቌ ወያኔ ወራሪነት በተፈጸመብን አሰቃቂ የጣምራ ጥቃት ግዛታችንን ለ30ዓመት ወደ ሃላ የመለሰ ሁለንተናዊ ውድመት የደረሰብን ከመሆኑ አኴያና ዛሬም ይህው የአማራ ጠላት የሆነው ብልጽግና መራሹ መንግስት ጦርነቱ ሰሜን ወሎንና ሰሜን ጎንደር በወያኔ ስር እንዳለ ጦርነቱ ቁሞ ወደ ድርድር እንግባ ብሎ በወሰነበት ሁኔታ በቀጣይ የአማራ ህዝብ የተጠናከረ የህወሃት ዘመቻ በሰሜን እና የተጠናከረ ኦህዴዳዊ/ኦነግ ዘመቻ በደቡባዊ የኢትዮጲያ ግዛት ውስጥ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ እንዲሁም በሸዋና በወሎ እንደሚከፍት ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ በሆነበት ሁኔታ የአማራ ብሄርተኝነታዊ ትግል፣ አሰላለፍና አስተሳሰብ እጅግ በበሰለ ሁኔታ ምጡቃዊ የሆነ ትግል እንዲያደርግ ይጠበቅበታል።
ይህንንም ምጡቃዊ የህልውናን ትግል ታግሎ በማታገል ሊመራ የሚገባው አስተሳሰባዊ ኋይል ታማኝነትን ለአማራ ህዝብ ተፈጥሮአዊ ስልጣንና መብት እውን ለማድረግ ተጸንሶ ላለ የአማራ ጥያቄ ብቻ ያደረገ መሆን አለበት።
 
Filed in: Amharic