>

ግምቱ 180 ሚልዮን ብር  የሚሆን የሀገር ሀብት የዐቢይ ሽመልሱ ፕላን ቢ በሆነው  ኦነግ  ( ሸኔ) አማካኝነት ወደመ!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ግምቱ 180 ሚልዮን ብር  የሚሆን የሀገር ሀብት የዐቢይ ሽመልሱ ፕላን ቢ በሆነው  ኦነግ
 ( ሸኔ) አማካኝነት ወደመ!!!
ዘመድኩን በቀለ

ልብበሉ ሰሞኑን ብቻ ‼  -ነጭ ነጩን 
12 ከባድ ማሽኖች ከደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ
1   መሰርሰሪያ ማሽን ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
2   ከባድ ማሽኖች ከዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ
4   ከባድ ማሽኖች ከኩዩ ሲሚንቶ ፋብሪካ 
3   ከባድ ማሽኖች ከምሥራቅ ሲሚንቶ ፋብሪካ በአጠቃላይ ግምታቸው ከ180 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት በዐቢይ ሽመልሱ ፕላን ቢ በሆነው አውዳሚው ኦነግ በዳቦ ስሙ ሸኔ አማካኝነት ተቃጥለው እንዲወድሙ መደረጋቸው ተነግሯል
*…. መንግሥት ለጀርመኑ ዶቸቬሌ ዜና አገልግሎት ” ኦነግ ሸኔ በሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ ንብረቶች ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም” ማለቱን ተከትሎ ይህን የሰሙ በኦሮሚያ የፀጥታ ዘርፍ ውስጥ የሚሠሩ ሃገር ወዳድ ኦሮሞዎች የመንግሥትን ውሸት በመቃወም የደረሰውን ጉዳት በምስል ልከዋል።
…ኦነግ ይህን ሁሉ ውድመት ሲፈጸም እያዩ የመከላከል ተግባር እንዳይፈጽሙ የታዘዙና የሚፈጸመውን ውድመት ከመመልከት በቀር አንዳች እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ትእዛዝ የተሰጣቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት በደርባን ሲሚንቶ ፋብሪካ ጊቢ ውስጥ 300 ያህል የፌደራል ፖሊሶች ደግሞ በዳንጎቴ እና በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ውስጥ ይገኙ እንደነበርም የዓይን እማኞቹ ተናግረዋል።
የኦሮሞ ክልል ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል:: መሪዎቹ እዲስ እበባ ተቀምጠው ኦነግ ክልሉን እያመሰው ነው:: ዛሬ ሰላሌን አልፎ በድራ እልቂት እይፈፀመ ነው::
የደራ ወረዳ 75% ነዋሪው እማራ ነው ነው:
“… ቅር ቢላቸው የበለፀጉ የዐማራ ዳያስጶራዎችን ነው። ሌላም አለ እጨምራለሁ  …‼
• ሸኔ ማነው?
• አባ ቶርቤስ ማነው?
• ተልዕኮ ወስዶ ማነው የሚመራቸው? ተልዕኮአቸውስ ምንድነው። …
“… መንግሥት ለጀርመኑ ዶቸቬሌ ዜና አገልግሎት ” ኦነግ ሸኔ በሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ ንብረቶች ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም” ማለቱን ተከትሎ ይህን የሰሙ በኦሮሚያ የፀጥታ ዘርፍ ውስጥ የሚሠሩ ሃገር ወዳድ ኦሮሞዎች የመንግሥትን ውሸት በመቃወም የደረሰውን ጉዳት በምስል ልከዋል።
“…በቦታው ላይ 300 የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች እና 75 የአካባቢው ሚኒሻዎች ነበርን። ነገር ግን ኦነግ ሸኔዎቹ የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹን የተመረጡ ውድ ንብረቶች አቃጥለው እስኪጨርሱ ድረስ እንዳትነኳቸው ስለተባልን አይናችን እያየ የሃገር ንብረት ወድሟል። ያማል ነው የሚሉት።
…ሲሚንቶ ፋብሪካው 300ውንም የፖሊስ ኃይል ቀልብ የሚችል ነው። በካፌው ተጠቃሚ ናቸው። የኦሮሚያ ፖሊሶች ሳይበሉ በፊት ሠራተኛው ምግብ እንዲበላ አይፈቀድም። ክልክል ነው። ውኃ እንኳ ሃይላንድ ነው የሚጠጡት። ነገር ግን የእንጀራ ቤታቸውን ሽፍታ እየተዟዟረ ሲያቃጥለው ከመመልከት በቀር ምንም ዓይነት ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም። ኦነግ ሸኔዎቹም ወደ ኦሮሚያ ልዩ ኃይል አይተኩሱም ነበር። ብቻ በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት የድርጅቱን የተመረጡ ማሽነሪዎች አውድመው ዘና ብለው ተመልሰው ሄደዋል።
“… አሁን ሠራተኛውም ህዝቡም ኦነግ ሸኔ ከመንግሥት ኃይል ይበልጥ በመንግሥት እንደሚከበር፣ እንክብካቤ እንደሚደረግለት ተመልክቷል። የፌደራል ፖሊስን የሚያዘው የብልፅግናው ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ነው። የኦሮሚያ ፖሊስ የሚታዘዘው በመርዳሳ ነው። መከላከያው የሚታዘዘው በዐቢይ አሕመድ ነው። ሦስቱም አዛዦች ኦሮሞዎች ናቸው። ሠራዊቱ ካልታዘዘ ደግሞ አይተኩስም። አንዳንድ ቦታ ላይ የኦሮሚያ ፖሊሶችና የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ቆመው የሞቀ ወሬ ሁሉ ያወራሉ። ይተዋወቃሉም። እናም ውድመቱ ይቀጥላል። መቻል ነው እንግዲህ።
“…ትናንት ታህሳስ 22/2014 ዓም ጠዋት 3:00 ላይ 14 የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች ታፍነው ወዳልታወቀ ሥፍራ መወሰዳቸው ተሰምቷል። ሠራተኞቹ በቀን ብርሃን ከፋብሪካው በ2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መጠለፋቸው ነው የተነገረው። ልብ በሉ ይሄ እየሆነ ያለው ወለጋ ጫካ ውስጥ አይደለም። ባሌና ቦረናም አይደለም። እዚሁ አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ላይ ነው። ሰሜን ሸዋ ደራ፣ በሰላሌ መስመር ወደ ጎጃም ጎንደር የሚወስደውም ዋናውን አውራ መንገድ ለመዝጋትም የዐቢይ ሽመልሱ ኦነግ ሸኔ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው።
… ወገኖቼ በምዕራብ ሸዋ ኦነግ ሸኔዎቹ ስለሚያርዱት ዐማራ እና የኦርቶዶክስ አማኞች ብዛት ተነግሮ አያልቅም ነው የሚባለው። በምዕራብ ሸዋ የሚገኙ እንደ ደብረ ጽሞና ያሉ ጥንታውያን ገዳማት ገዳማት እና አድባራት ተዘርፈዋል። መነኮሳት፣ ካህናቱና ምዕመናንም እየታረዱ ነው። የሃገሪቱ መሪዎች እስላሞችና ፕሮቴስታንቶች ስለሆነ ለሚታረደው ኦርቶዶክስንና ለሚገደለው ዐማራ ደንታ የላቸውም የሚሉ አሉ። በኦሮሚያ ድምጽ አልባ የዘር ማጥፋት ሥራ እየተካሄደ ነው። ኦርቶዶክሳውያኑና የዐማራ ነገድ ቤተሰቦች ከመታረድ በቀር የሚደርስላቸው አንድም ኃይል እንደሌለ አውቀው ተስፋ ቆርጠው የሞታቸውን ቀን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ነው እየተነገረ ያለው።
“… አዲስ አበባን በዲምላይት በቡናቤት መብራት አፍዘው ገጠሩን በፀጥታ ያለ ግርግር እያጸዱት ነው። ብራቮ አቢይ አሕመድ፣ ብራቮ ሽሜ … ይህን ላሜቦራ ሾርት ሚሞርያም ህዝብ ኮንቪንስ እና ኮንፊዩዝድ እያደረጋችሁ በደንብ አስነጥሱትማ። እስኪነቃ ድረስ ዠልጡት። ኤትአባቴንስና… በሉኝ ውገሩኝ ደብድቡኝ አለ ከበሮ።
… ማነህ ባለ ሳምንት? ተረኛውን ዠልጡት… ኤትአባቱንስና…
Filed in: Amharic