>

"እስክንድር ካሳ ሊሰጠዉ ይገባል - ይቅርታ ሊጠዬቅም ይገባል...!!!" (ሸንቁጥ አየለ)

“እስክንድር ካሳ ሊሰጠዉ ይገባል – ይቅርታ ሊጠዬቅም ይገባል…!!!”
ሸንቁጥ አየለ

*…. ለእስክንድር ብቻ ሳይሆን እንደ እስክንድር ያለ ወንጀላቸዉ ለታሰሩ ንጹሃን የሀገር ተቆርቋሪዎች ሁሉ ካሳ ሊሰጡ እንዲሁም ይቅርታ ሊጠዬቁ ይገባል
“ንጹሃን አለ አግባብ:አለወንጀላቸዉ ከሚታሰሩ ወንጀለኛዉ ያምልጥ” የሚለዉ ታላቅ እና ጥልቅ አባባል ታላቁ የህግ መርህ ነዉ::
እኛ ሀገር ግን ንጹሃን አለአግባብ:አለ ወንጀላቸዉ በተለይም ፖለቲከኞቻችን ዘለላለማቸዉን በእስር ቤት የሚማቅቁበት ሂደት እንደቀጠለ ነዉ:::ንጹሃን ፖለቲከኞች የፖለቲካ ጉዳይ : የሀገር ጉዳይ ስለነኩ ብቻ በእስር ቤት ብዙ ከማቀቁ ብኋላ ነጻ ተብለዉ ይፈታሉ::
—–
ይሄ ሂደት በደርግ:በወያኔ እንዲሁም አሁን ባለዉ መንግስት የቀጠለ ሂደት ነዉ::ቁልፍ የህግ መርህ መሰረትን እና መርህን በማን አለብኝነት የመናድ ብሎም ሊታረቅ ያልቻለ የህግ የበላይነት በጉልበት የበላይነት የተደፈጠጠበት ሀቅ ነዉ::
——-
ሲፈቱ ካሳ አይሰጡም::ይቅርታ አይጠዬቁም::ዝም ብሎ ይፈታሉ:: ይሄም ልብ ይሰብራል::ያሳዝናልም::ይሄዉ ነገር አሁንም እስክንድር ነጋ እና ከርሱ ጋር የታሰሩት ንጹሃን ላይ እንደተለመደዉ ተከስቷል::
እስክንድር ካሳ ሊሰጠዉ ይገባል::ይቅርታ ሊጠዬቅም ይገባል::
—–
እስክንድር ነጋ ንጹህ እንደነበርክ እናዉቃል::እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የታሰርከዉ ለሀገርህ ለኢትዮጵያ ነጻነት ዲሞክራሲን እና እኩልነት በመጠዬቅህ ብቻ መሆኑንም እናዉቃል::
—————-
እስክንድር  ካሳ ሊሰጠዉ ይገባል::ይቅርታ ሊጠዬቅም ይገባል::ለእስክንድር ብቻ ሳይሆን እንደ እስክንድር ያለ ወንጀላቸዉ ለታሰሩ ንጹሃን የሀገር ተቆርቋሪዎች ሁሉ ካሳ ሊሰጡ እንዲሁም ይቅርታ ሊጠዬቁ ይገባል እንጂ ዝም ብሎ የሀገር ጥላ የሆኑ ግለሰቦችን ዝም ብሎ እንደ ጥጃ ማሰር እና መፍታት እጅግ ታላቅ የህግ መርህ ጥሰት ብቻ ሳይሆን እጅግ ትልቅ የህግ መርህ ጥሰት ወንጀልም ነዉ::
————-
ይሄ ሁሉም ሆኖ እስክንድር ለሀገርህ ለኢትዮጵያ ነጻነት ዲሞክራሲን እና እኩልነት የማምጣቱ የቤት ስራ ግን አሁንም ከፊት ለፊትህ ይጠብቅሃል::
————
የኢትዮጵያን አንድነት: ነጻነት:እኩልነት እና ዲሞክራሲ ከሚናፍቁ ሀይሎች ጋር የበለጠ ተባብረህ የመስራት እና የተሻለ ተጽኖ ፈጣሪ ሀገራዊ ሀይል የመፍጠር የቤት ስራ አለብህ::
በእኔ ግምጋሜ የፖለቲካ ቁመትህ ከአዲስ አበባ የገዘፈ: በኢትዮጵያ የነጻነት ማማ ላይ የቆመ የፖለቲካ ሰብእናን የተላበስህ ነህ::አሁን ያለዉ የኢትዮጵያ የተቃዉሞ ጎራ ያንተን ሰብዕና የተላበሱ ሰዎች ሊያሰባስቡት እና ሊያስተባብሩት ይችላሉ::::
Filed in: Amharic