>
5:13 pm - Friday April 19, 2554

"ሰው እንዴት አሳዳጊ አባቱ ላይ አልጨከነም ብሎ ያጉረመርማል....!!!" (ዘመድኩን በቀለ)

“ሰው እንዴት አሳዳጊ አባቱ ላይ አልጨከነም ብሎ ያጉረመርማል….!!!”
ዘመድኩን በቀለ

“… ሰዉ ግን ምን እንደነካው አላውቅም። ምን ዓይነት ክፉ ዘመን ላይ እንደደረስንም እንጃ። ከምር ስምንተኛው ሺህማ ሰተት ብሎ ነው የገባው። ሰው እንዴት አሳዳጊ አሳዳጊ አባቱ ላይ እንዲጨክን ይመከራል? አቦይ ስብሐትን የመሰለ የዘር ፖለቲካ ፈጣሪ፣ ሻአቢያን 60 ሺ የትግሬ ገበሬ አስፈጅቶ ከደርግ ከበባ ያዳነ፣ እህቱ የኤርትራው መከላከያ ሚንስትር የስብሐት ኤፍሬም ሚስት የሆነች፣ የሕገ መንግሥታችን ፈጣሪ፣ የአንቀጽ 39 ባለ ሙሉ መብት ባለቤት፣ የኦህዴድ፣ ብአዴን ፈጣሪ፣ የኦነግ አሳዳጊ የጡት አባት፣ የወያኔ መሐንዲስ፣ ልጆቹ ቤተ መንግሥቱን ተቆጣጥረው ሳለ በዚህ ዕድሜው እስር ላይ ይቆይ መባሉ ከምር ደስስ አይልም። ነውርም፣ ኃጢአትም፣ ወንጀልም ነው።
“…ይልቅ መንግሥትን መቃወም ታምራት ነገራ ቢፈታ፣ መዐዛ መሐመድም ብትፈታ ነበር። እነዚህን ሃገር አፍራሽ ወንበዴዎች፣ ፀረ ህዝብ፣ ነፍጠኛ፣ የምንልክ መንፈስ አቀንቃኞች። የወያኔን ሕገ መንግሥት ተቃዋሚዎች፣ የጎሳ ፖለቲካ ተፀያፊዎች፣ ደፋሮች፣ ልበ ሙሉ አፍቃሬ ኢትዮጵያኖች፣ እንደ ቆሻሻ በግሬደር ለሚቀበር ዐማራ ተቆርቋሪዎች፣ እነሱ ቢፈቱ ነበር መንግሥትን መቃወም። እንጂማ ዐቢይ አሕመድ አሊ፣ መኮንን ደመቀ ሀሰን፣ ሙፈርያት ካሚል፣ አባ ዱላ ገመዳ፣ ጃል ዳውድ ኢብሳ፣ አቦይ ስብሀት ነጋን ፈቱ ብሎ ማላዘን ይሄ ከጤነኞች የሚጠበቅ አይደለም። የሕገ መንግሥቱን ፈጣሪ አስሮ፣ ሕገ መንግሥቱ ይፍረስ የሚሉትን ታምራትንና መዐዛን ይፈቱ ማለት ዶማነት ነው። ዴዴብ ሁላ። ዐብይዬ የእኔ ጌታ ይሄን ሾርት ሚሞሪያም ህዝብ እንዳት ሰማ። ዴዴየብ ህዝብ በየሱስ ስም የተወጋ ይሁን። አሜን ነው?
“…አቦይ ስብሃት እንኳን ለቤትዎ አበቃዎ። አሁን ቀረብ ብለው ጂኒው የሰፈረበትን ልጅዎን አብይን ያማክሩት። ዐቢይ ግን መዐዛንና ታምራትን የፈታህ ቀን የመንግሥትህ ፍጻሜ ይሆናል። ይሄንን ዕወቅ። እነዚህን ሁለቱን የኢዜማ፣ የወያኔ፣ የሻአቢያ፣ የኦህዴድና የኦነግ ጠላቶች መፍታት ማለት የሃገሪቱን ዲሞክራሲ ወደ ኋላ መጎተት፣ እድገቷንም በአፍጢሙ መድፋት እንደሆነ እንድታውቅ። በተለይ መዐዛን መፍታት ማለት ኦነግ ላረዳቸው፣ ለፈናቀላቸው፣ ላገታቸው፣ ለደፈራቸው የዐማራ ነገድ አባላቶች ዕውቅና በመስጠት ኦነግን ማሳጣት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል።
• መዐዛና ታምራት በወኅኒ ይበስብሱ ‼
• ጃዋርና ስብሃት ይንገሡ       ‼
• የእኛ የዜጎች ድምፅ ይከበር  ‼
Filed in: Amharic