>

ደመቀ መኮንንና ተመስገን ጥሩነህ፤ ያማራ ሕልውና ዋና ጠላቶች! (መስፍን አረጋ)

ደመቀ መኮንንና ተመስገን ጥሩነህ፤ ያማራ ሕልውና ዋና ጠላቶች!

 

መስፍን አረጋ


የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ወይም ኦነግ ሳይሆን ዐብይ አሕመድ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ዐብይ አሕመድን ከጫንቃው ላይ ካወረደ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡  በተለይም ደግሞ ዐብይ አሕመድ ስልጣን ሳይዝ በፊት እዚህ ግባ ይባል ያልነበረው፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ግን እንደ ጨሳፊ (rocket) ተጨስፎ ሰማይ ላይ የደረሰው ኦነግ የሚባለው ውሽልሽል ድርጅት፣ ዐብይ አሕመድ ከሌለ መሬት ወድቆ ይከሰከሳል፣ ወያኔ መለስ ዜናዊን ሲያጣ እንደተከሰከሰው ዓይነት፡፡  

መለስ ዜናዊን ቀጥ አድርጎ ይዞት የነበረው ወያኔ ሳይሆን በአዲሱ ለገሰ ይመራ የነበረው ብአዴን እንደነበረ ሁሉ፣ ዐብይ አሕመድን ቀጥ አድርጎ የያዘው ደግሞ በደመቀ መኮንን የሚመራው ብአዴን ነው፡፡  እደግመዋለሁ፣ ዐብይ አሕመድ ዐማራን መቸም እንዳይነሳ አድርጎ በማዳከም (ከቻለም ደግሞ ጭራሹን በማጥፋት) የኦነግን ዓላማ ለማሳካት ቆርጦ የተነሳ ቀንደኛ ኦነጋዊ ቢሆንም፣ የማስፈጸሚያ መሠረቱ ግን ኦነግ ሳይሆን ብአዴን ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ ኦነጋዊ አውሬ ቢሆንም ጥርሱ ግን ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ ብአዴኖች ናቸው፡፡  ስለዚህም የአማራን ሕዝብ አረመኔነቱ ወደር በሌለው በኦነጋዊው አውሬ በዐብይ አሕመድ እያስቆረጣጠሙት ያሉት ብአዴኖችና ብአዴኖች ብቻ ናቸው፡፡  በመሆናቸውም የአማራ ሕልውና ዋናወቹ ጠላቶች ዋናወቹ ብአዴኖች ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጥሩነህ ናቸው፡፡   

እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ወደውም ሆነ ተገደው (convinced or confused) በሰኔ አስራምስቱ የባሕርዳር ጭፍጨፋ ላይ በተጫወቱት የቀጥታም ሆነ የተዛዋሪ ወሳኝ ሚና አማካኝነት የዐብይ አሕመድ እስረኞች እንደሆኑና፣ ዐብይ አሕመድም የወንጀል ግብራበሮቹ መሆናቸውን እንደ ማስፈራርያ በመጠቀም ሲጠራቸው ወዴት፣ ሲልካቸው አቤት የሚሉ፣ አፋሽ አጎንባሹ የሆኑ፣ ፍጹም ታዛዥ ሎሌወቹ እንዳደረጋቸው የታወቀ ነው፡፡ 

በተለይም ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን ነገረ ሥራው ሁሉ ወሎ የኦሮሞ ነው በሚለው በኦነጋዊው በዐብይ አሕመድ ስብከት ታውሮ ወደ ኦነጋዊነት ተቀይሮ፣ ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ እንዲሉ ከራሱ ከዐብይ አሕመድ በላይ ጽንፈኛ ኦነጋዊ ሁኖ፣ የኦነጋውያንን ፀራማራ አጀንዳ ከዐብይ አሕመድ በላይ የሚያራምድ ያስመስልበታል፡፡  በኔ በኩል ደግሞ አማራ መስሎ አማራን የሚያስበላ ጽንፈኛ ኦነጋዊ ሁኗል ብየ ከደመደምኩ ቆይቻለሁ፡፡  ቀድሞውንም ቢሆን፣ ግለሰቡ በትምህርቱ ብዙም ስላልገፋና፣ ራሱን በራሱ የሚያስተምር ዓይነት ሰው ስላልሆነ፣ በተጨማሪ ደግሞ አንደበተ ጉልድፍ ከመሆኑም በላይ፣ በራስ መተማመን እንደሚጎድለው በግልጽ የሚያስታውቅበት፣ የዣግሬነት (ማለትም የተከታይነት) ሰብዕና (follower mentality) በጽኑ የተጠናወተው፣ ኃላፊነትን መውሰድ እንደ ጦር የሚፈራ ጃግሬ (follower) ስለሆነ፣ ዐብይ አሕመድን የመሰለ አጭበርባሪ ጮሌ በቀላሉ አጭበርብሮ ባርያው እንደሚያደርገው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ 

 ኤርትሬው በረከት ስምዖን በአማራ ሕዝብ ላይ የሠራው ትልቁ ወንጀል፣ ብአዴንን የሞላው የጃግሬኔት ሰብዕና አለመጥን የተጠናወታቸውን የደመቀ መኮንንን ዓይነት መፃጉወች በማሾ እየፈለገ መሆኑ ነው፡፡  ታምራት ላይኔ፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ አለምነው መኮንን፣ ካሳ ተክለብርሃን ወዘተ፣ አማራ ጠል ጌቶቻቸውን ለማስደሰት ሲሉ ማናቸውንም ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ ለመፈጸም ቅንጣት የማያቅማሙ ታዛዥ ውሾች ነበሩ፡፡  ለምሳሌ ያህል የ2000 ዓ.ም የሕዝብ ቆጠራ ባለሙያ የነበረችው ግለሰብ የአማራ ሕዝብ በሦስት ሚሊዮን ገደማ መቀነሱን ለመለስ ዜናዊ ፓርላማ ስታስረዳ፣ ከጎኗ ተቀምጦ የነበረው አዲሱ ለገሰ ፀራማራ ሥራየን በሚገባ ሠርቻለሁ በሚል የመኩራራት ስሜት መለስ ዜናዊን በፈገግታ ሲመለከተው ያስተዋለ ሰው፣ ይህን የወያኔ ውሻ መቸም ቢሆን ይቅርታ አያደርግለትም፡፡  ዐብይ አሕመድና ደመቀ መኮንን ግን የአማራን መከራና ፍዳ በማየት እየተዝናና ተቀማጥሎ እንዲኖር ፈቅደውለታል፡፡    

የብአዴኑ መሪ አቶ ደመቀ መኮንን እወክለዋለሁ የሚለውን ሕዝብ ውነትም የሚወክል ቢሆን ኖሮ፣ የአማራን ሕዝብ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ የሚያስጨፈጭፈውን ኦነጋዊውን ዐብይ አሕመድን በሁለት ቀላል መንገደች ከስልጣኑ አስወግዶ ከአማራ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ወርውሮ መጣል ይችል ነበር፡፡ 

  አንደኛው መንገድ፣ ብአዴንን ከብልጽግና ማስወጣት ነበር፡፡  ዐብይ አሕመድ በተጭበረበረ ምርጫ ስልጣኑን ከማደላደሉ በፊት፣ አቶ ደመቀ መኮንን ብአዴንን ይዞ ከብልጽግና ቢወጣ ኖሮ፣ የዐብይ አሕመድ ፀራማራ መንግሥት በማግስቱ ይፈርስ ነበር፡፡  ሁለተኛው መንገድ ደግሞ፣ ዐብይ አሕመድን በራሱ ፓርላማ ላይ አንዲት ጥያቄ ብቻ እንዲጠየቅ ማድረግ ነበር፡፡  ጥያቄውም፣ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰላማዊ ተቃውሞ ለማስቆም አልቻልክም ተብሎ ከስልጣን ከወረደ፣  በጠቅላይ ጦር አዛዠነት እመራዋለሁ የሚለውን ጦር በዚህ ደረጃ ለሽንፈት ያበቃው ዐብይ አሕመድ ላንዲት ቀን እንኳን ስልጣን ላይ የሚቆይበት ምክኒያት ምንድን ነው የሚለው ነው፡፡  አቶ ደመቀ መኮንን ግን አውቆ ስለተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም፡፡  

አቶ ተመስገን ጡሩነህ ደግሞ ነገረ ሥራው ሁሉ የረዥም ጊዜ ባልደረባው የነበረውን ዐብይ አሕመድን ለማስደሰት ጠብ እርገፍ ማለት ስለሆነ፣ ከዐብይ አሕመድ ጋር የተለየ ግንኙነት ያለው ያስመስልበታል፡፡  ባጭሩ ለመናገር ይህ ግለሰብ የዐብይ አሕመድ ባልደረባ ብቻ ሳይሆን ጃንደረባም ጭምር ነው፡፡  ለዚህ ይሆናል ወዳጁ ዐብይ አሕመድ ከባሕርዳሩ ጭፍጨፋ በኋላ ለሱ በማይገባው በዶክተር አምባቸው ወንበር ላይ ያስቀመጠው፡፡  በዲባቶ አምባቸው ወንበር ላይ በተቀመጠ ማግስት ደግሞ ፋኖን እያሳደደ መግደልን ዋና ሥራው አድርጎ ተያያዝከው፡፡  የጀነራል አሳምነውን ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በማፈራረስ፣ የአማራ ብሔርተኝነት ያሰጋኛል ያለውን ዐብይ አሕመድን ለማስደሰት ብዙ ርቀት ተጓዘ፡፡  ሽመልስ አብዲሳ የዝዋይና የሻሸመኔ አማሮችን ቆዳ ስላስገፈፈ ብቻ አድናቆቱን ለመግለጽ ባሕርዳር ድረስ ጠርቶ ካባ ደረበለት፡፡  የአማራን ሕዝብ እነ ሽመልስ አብዲሳና ታየ ደንድኣ የሚዘልፉት ሳይበቃ፣ ራሱ አቶ ተመስገን ደግሞ ‹‹ወንጀለኞችን የሚያወድስ ማሕበረሰብ›› በማለት በብአዴን ምክር ቤት ውስጥ ተሳለቀበትና የአለምነው መኮንንን ስድብ ደገመው፡፡     

ወያኔና ኦነግ እስካፍንጫቸው በሚታጠቁበት ጊዜ የአማራ ሕዝብ ራሱን ለመከላከል እንዳይታጠቅ አንቆ መያዝ ብቻ ሳይሆን፣ የታጠቀውንም እንዲፈታ የቻለውን ሁሉ አደረገ፡፡  ይህን ሁሉ ካደረገ በኋላ ደግሞ የአማራ ሕዝብ ዱላ ብቻ ይዞ ድሽቃ ከታጠቀው ከወያኔ ጋር ሲፋለምና እንደ ቅጠል ሲረግፍ ለማየት የቋመጠ ይመስል፣ ከጦርነቱ አስቀድሞ ወያኔን እንሰብረዋለን፣ እንቀብረዋለን እያለ የፌስቡክ ጉራውን እያከታተለ ነዛ፡፡  በዚያ ደረጃ ሲፎክር የነበረ ሰው ደግሞ ወያኔ የአማራን ድንበር ጥሶ ደብረብርሃን እስኪደርስ ድረስ፣ ከጌታው ከዐብይ አሕመድ ጋር እተሰወረበት ተሰውሮ፣ ድምጹን አጥፍቶ አድፍጦ ተቀመጠ፡፡  የአማራ ሕዝብ ወያኔን ወደ መቃበሩ የመሸኘት ዘመቻ ሲጀምር ደግሞ ካደፈጠበት ቡትርፍ ብሎ ወጥቶ ዘመቻውን ባጭሩ ለማስቀረት መልከስከስ ጀመረ፡፡  

የአማራ ሕዝብ የሕልውና አደጋውን ማስወገድ የሚችለው ዐብይ አሕመድን ከጫንቃው ላይ አውርዶ በመጣል ብቻ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድን መጣል የሚችለው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተደግፎ የቆመባቸውን የግራና የቀኝ ምርኩዞቹን በመቀማት ብቻ ነው፡፡  እነዚህ ሁለት ምርኩዞቹ ደግሞ ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ናቸው፡፡  ስለዚህም ያሁኖቹ የአማራ ሕልውና ዋና ጠላቶች ዋናወቹ ብአዴኖች ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ናቸው፡፡ 

  

መስፍን አረጋ:- mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic