>

"አብይ አህመድ ስልጣን ላይ ሊቆይ የሚችለው በውጭ ሀይላት ድጋፍ ብቻ ነው...!!!" (አዳነ አጣነው)

“አብይ አህመድ ስልጣን ላይ ሊቆይ የሚችለው በውጭ ሀይላት ድጋፍ ብቻ ነው…!!!”
አዳነ አጣነው

*…. አብይን ከህዝብ የነጠሉት መንግስታት በጊዜአዊነት እንጂ በቋሚነት ወዳጅነቱን አይፈልጉትም፡፡ ሌላ አማራጭ አስቀምጠዋል፡፡
የአብይ አህመድ ስልጣን ከአሁን በኽላ ሊቀጥል የሚችለው በውጭ መንግስታት ድጋፍ ብቻ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ያለው ግንኙነት ተቋርጧል፡፡ከመቅጽበት ከህዝብ ድጋፍ ተነጥሎ በውጭ ሀይላት ድጋፍን አብይ አህመድ አሊ ምርጫየ ነው ብሏል፡፡
የውጭ ስለላ ድርጅቶች “Isolate and Destroy” በሚል ባዘጋጁት ወጥመድ ውስጥ አብይ አሀመድ አሊ ሰተት ብሎ ገብቷል፡፡ አሁን ብቸኛው አማራጭ መነገድ ለአብይ አህመድ የቀረው የስለላ ድርጅቶቹ የሚሰጡትን አላማ በማሳካት ስልጣኑን ለማስቀጥል መሞከር ነው፡፡
የውጭ የስለላ ድርጅቶች አብይ አህመድን ከኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ከውጭ ሀገራት ቁርጠኛ ደጋፊዎቹ ጋርም ነጥለውታል፡፡ አሁን አብይን ከህዝብ የነጠሉት መንግስታት አብይ አህመድን በጊዜአዊነት እንጂ በቋሚነት ወዳጅነቱን አይፈልጉትም፡፡ ሌላ አማራጭ አስቀምጠዋል፡፡
አብይ አህመድ አሊ የህዝብ ተቃውሞ እየበዛ ሲሄድ 2 ካርዶችን ሊመዝ ይችላል፡፟ (1)ሀይማኖታዊ ብጥብጥ ማለትም እሱ በሚመራው ጴንጤኮስታል እና ዋሃቢ ኢስላም ከኦርቶዶክስ ጋር ማጋጨት (2) እንደለመደው በኦርሞ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰዎችን ማስጨፍጨፍ ፡፡እነዚህ ክሰቶችን በቅርብ የምናያቸው ይሆናል፡፡
Filed in: Amharic