>
5:21 pm - Tuesday July 20, 5137

ተአምራቱ ቀጥሏል...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ተአምራቱ ቀጥሏል…!!!

ዘመድኩን በቀለ

*…. ኦሮሞን ነጻ ለማውጣት ከኢትዮጵያ ጋር የሚጋደለው አጅሬ ኦነግ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በጠመንጃው ላይ አስሮ ለእናት ሃገር ኦሮሚያ ሲዋደቅ ፈጣሪ ያሳያችሁ? … !!!
 
“…የዐብይ አህመድና የሽመልስ አብዲሳ ሹርቤዎቹ ከኢትዮጵያ ጋር ሲዋጉ የሚታጠቁት መሳሪያና … ተሸንፈው ሲማረኩ የሚማረከው መሳሪያ በአስማት እንደሚቀየር አንዳንድ ጩፋናዳንሳ የዥጋቤል ሰዎች ሲመሰክሩ በመሰማት ላይ ነው። አሜን ነው? አጠገብህ ያለውን ሰው ነካ አድርገውና… በየሰሱስ ስም ዴዴየብ ህዝብ የተወጋ ይሁን ብለህ ንገረው… እህእ… ድገመው
“…በነገራችን ላይ ዐቢይ አህመድ ዐማራ ክልል ከትሞ የብአዴን ካድሬዎችን መንፈስ ሲሞላባቸው ውሎና አድሮ በመጨረሻም። “…ወደ ህዝቡ ሁሉ ሂዱ… በእኔ በደመቀና በይልቃል ስም እያስፈራራችሁ የዐማራን ፋኖ ትጥቁን አስፈቱና ባዶ እጁን አስቀሩት። ከዚያ በሱዳን፣ በኦነግና በህወሓት ትጨፈጨፉ ዘንድም ተዘጋጁ ብላችሁ ስበኩልኝ ብሎ ልኳቸዋል አሉ። በድኖቹም እሺ ጌታችን፣ አማላጃችን በማለት ቀበሌ ወርደው ትጥቅ ፍቱ አትፍቱ ንትርክ ላይ ናቸው አሉ።
“…የዐማራ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ መለስ ዜናዊ አስረስ ይቅርታ ዶፍቶር ይልቃል ከፈለ አስረስም በበኩላቸው “… አጎታችን አቶ ስብሃት ነጋና ቤተሰቦቹ ቢፈቱም፣ ሁኔታው ቢያበሳጭም፣ ዐማራ ቢወድምም ልንበሳጭ አይገባም። ገና ምኑን አያችሁትና ነው በአንድ አቶ ስብሃት መፈታት ኮሬንቲ ካልጨበጥን የምትሉት? … ምድረ ዴዴየብ ሁላ ብለው ያስደነግጡናል ብዬ ስጠብቅ ግን አሳቸው እናም አትበሳጩ፣ ገና ጎንደርና ጎጃም መች ወደመ? በማለት ንግግራቸውን መጨረሳቸውን ጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ…  ሃአሃአሃሀአንጥሽሼ…‼
” የዛሬውን የአርከበ እቁባይና የኢሳያስ አፈወርቂ አሽከሮች የወሽካቶቹን የዐቢይ አሕመድና የሽመልስ አብዲሳን ኮሜዲ ተመልከቱልኝማ…
“…ዋልታ ማለት የህወሓት የግል ንብረት ነው። እናም ዋልታ ሆዬ በዛሬው የዜና ዕወጃው ምን ብሎ ቢቀልድ ጥሩ ነው?… 400 ኦነግ ሸኔ ሲደመስስ 115 ደግሞ ተማረኩ ይላል። በፎቶው ላይ እንደምታዩት ከተማረከው የኦነግ ሸኔ መሳሪያ መካከል የሚታየው በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ማንገቻ የተሽቆጠቆጠው መሳሪያም የኦነግ መሳሪያ ነው እያለንም ነው።
“… ያዝ እንግዲህ ኦሮሞን ነጻ ለማውጣት ከኢትዮጵያ ጋር የሚጋደለው አጅሬ ኦነግ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በጠመንጃው ላይ አስሮ ለእናት ሃገር ኦሮሚያ ሲዋደቅ ፈጣሪ ያሳያችሁ? ቀልደኞች። ይሄን መንጋ ሾርት ሚሞርያም ህዝብ ምንአባቱ ያመጣል ብለው እንዲህ ሲያላግጡበት ከማየት የከፋ ምን በደል አለ? ትንሽ ቆይተው ይህቺን የእኔን መረጃ ካዩ በኋላ ዜናውን የተማረኩት “ኦነግ ሸኔና #አማርኛ_ተናጋሪ_ሽፍታዎች” ብለው ከነገ ጀምሮ ባያስተካክሉት ቱ ! ምንአለ ዘመዴ በሉኝ። ታያላችሁ። ሂኢ… እኔ ሙዳቸውን በደንብ እኮ ነው የበላሁት ትልና ክብዶ ክብዶ ትጫወታለህ።
ከምር የበሻሻው አራዳው አሁን አሁን ሙዱ የተባነነበት፣ አኬሩም የወደቀበት ይመስላል። ቀብታ ያነገሠችው ነቢይት ብርቱካን ግን ተጣላችው ይሆን እንዴ?መቀባቷንም የተወች ይመስለኛል።
“…ለማንኛውም መሳሪያውም የኦነግ አይደለም። ከዚያ መከረኛ ከምስኪኑ የዐማራ ገበሬ ሚኒሻ ላይ የተገፈፈ መሳሪያ ነው። ኦነግ ባለ ስናይፐር፣ ባለ ዲሽቃ ባለ ሞርታር እንጂ ባለ ቆመህ ጠብቀኝ አይደለም። የኦነግ ተዋጊዎች ባለሹሩቤ ሉ…ዎች እንጂ እንዲህ እንደሚታዩት ምስኪን ወንዳወንዶች አይደሉም።
“…የእኔ ሥራ ቀደዳችሁን ማጋለጥ… መርዛችሁን ማክሸው፣ አለማስዋሸት ነው። እናንተ ተበርጠቁ… እኔ ጓ ብዬ ብጥረቃችሁን ማጋለጥ ነው። ምድረ በጥራቃ ብጥርቅ ሁላ… ዐቢይ አህመድን እንደ ግል አዳኝ ለተቀበሉት ሾርት ሚሞርያም ሜካፓም ሁላ ዐቢይ አሕመድ አያማልድም ብሎ በድፍረት መመስከር ነው። እዚህ ላይ ስለታማኝ በየነ የዐብይ እግር ላይ መስገድ እና መውደቅ አላነሣሁም። ምኑን ከምኑ እያጋባችሁ ከሰው እንደምታጣሉኝ አልገባኝም። አታጣሉኝ።
“… እኔማ ተይዤ እኮ ነው። ምን እንደሚያስለፈልፈኝ እንጃ… ኤትአባቴንስና… ይበለኝ ‼
ዘመዴ-ነጭነጯን
Filed in: Amharic