>
5:29 pm - Friday October 11, 6115

"እኛ  በአንድ ሰው ፍቅር ወድቀን የምናፈርሳ ሀገር እግዚያር ያኖራታል ማለት ሀገራዊ እብደት ነው:....!!!!" (ጎዳና ያእቆብ)

እኛ  በአንድ ሰው ፍቅር ወድቀን የምናፈርሳ ሀገር እግዚያር ያኖራታል ማለት ሀገራዊ እብደት ነው:….!!!!”
ጎዳና ያእቆብ

ለአብይ አህመድ እና ለኦህዴድ መንግስት ብቸኛ የህልውና አደጋ የኦርቶዶክስን አከርካሪ መስበር ሰሜኑን (አማራና ትግራይን) ማዳከምና ከዚህ በኃላ በኢትዮጵያ ላይ ወሳኝ ሚና እንዳይኖራቸው ማድረግ ነው::
ብዙ የኦርቶዶክስ ቀሳውስት ፓፓሳት ዲያቆናት እና ምእመናን ፈጣሪን ትተው በአብይ አህመድ  አምልኮ ተጠምደዋል::
በሬ ካራጁ እንዲሉ ከአራጃቸው ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ ውስጥ በመግባታቸው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እለት ከእለት ትዋረዳለች:: ትዘረፋለች:: የህውና  አደጋ ውስጥ ገብታለች::
በሆዳም ቀሳውስት ፓፓሳትና ዲያቆናት ሆድ አምላኩ ገንዘብ ሀቁ እና ምቾት ብርቁነት ንፁሀን በእምነታቸው ምክንያት ይታረዳሉ ቤተ ክርስቲያናት ይነድሉ::
እረኞቻችን ናችሁ ምሩን አሰማሩን ስንላቸው ለተኩላ መንጋጋ አጩን:: የአዳነች አቤቤ ድፍረት ከኦርቶዶክስ ጠልነት የካድሬነት ዘመኗ እና ከአብይ አህመድ በኦርቶዶክ ላይ ካለው አቋም ብቻ የመነጨ አይደልም:: ከሀዲዎችን ፓፓስ ቄስ ዲያቆን እያልን መጥራት ካላቆምነው ከኛም ድክመት የሚመነጭ ነው::
አለቅነታቸውን የተዉ እምነታቸው የካዱና አሳድጋ ለወግ ለማእረግ ያበቃቻቸውን እናት ቤተ ክርስቲያን ሊያጠፏት ከተነሱት ጋር አብረው እለት ከእለት የሚያሳንሷት እና የሚያዋርዱ ዲያቆናት ቀሳውስትና እና ፓፓሳት እንደ አረመኔና ቀራጭ እስካልተቆጠሩ ድረስ ውርደቱ ውድመቱና የምእመናኑ መታረድ የሚቀጥል ነው::
ምንደኛ እረኞችን ቀርቶ <<መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።>> ሲል ቅዱስ ይሁዳ በመልእክቱ  አስቀምጧል::
የአማራውና የትግራዩም ጉዳይ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ድንዛዜ የተለየ አይደለም:: በትግራይ በኩል ሊገነጥላቸው ቆርጦ ለተነሳው ለአብይ አህመድ የተመቹ ሆነው ከገነቧት ሀገር እንነጠል የሚሉ ይህ ነው የማይባል ቁጥር ያለው ተጋሩሮች አሉ:: አማራውም አንድ ሳምንት አብይ ያማልዳል:: አንድ ሳምንት ደግሞ አራጃችን አብይ አህመድ ነው በሚል የሚዋልል ስሜት ሀገር በማፍረስ ሂደቱ ላይ አውቀውትም ይሁን ሳያውቁት እየተሳተፏ ነው::
ሁሉም በተባበረ ክንድ የአብይ አህመድ ኢትዮጵያን የማፍረስና ኦርቶዶክስን የማዳከምና የማጥፋት እኩይ ተልእኮውን እንዲያሳካ እያገዝነው ነው:: <<የማያስተውል ትውልድ ይገለበጣል>> ቅዱሱ መፅሀፍ እንደሚል ትውልዱ እየተገለባበጠና ሀገር በላያችን ላይ እየፈረሰች ነው::
በስሌት ሳይሆን በስሜት እየተነዳን ነውና መጨረሻችን እሮሮና ጥርስ ማፏጨት መሆኑ አይቀርም::
እግዚያር ወዶ የሚያኖራት ሀገር የለም ባይ ነኝ:: ሲጀመር እግዚያር ቢጠብቀን ኖሮ  የሰው ስጋ የሚበላና ውሀ ቀጠነ ብሎ የሚተራረድ ጦርነት ወይም ሞት የሚል ህዝብ ባላደረገን ነበር::
ሁሉም የራሴ የሚለውን ጉድፍ እያሽሞነሞነ በሌላው ላይ ጣቱን ሲጠቁም ውሎ የሚያድር ግብዞች እንደ አሸን ባልበዛ ነበር:: እኔና የኔ በሚል ወረርሽኝ ባልተጥቃን ነበር::
ማስተዋል ማጣታችን እግዚያር አብሮን እንዳለ ሳይሆን እንዴት ከኛ እንደራቀ የሚያሳይ ነው:: እንዲህ እግዚያር የእግሩ መረገጫ ያደረጋትን እየሩሳሌምን ሲሶውን ለሰይፍ ሲሶውን ለረሀብ እና ሲሶውን ለግዞትና ለስደት ባልዳረገ ነበር:: ለ1900 አመታት ርስቴና ህዝቤ ያላቸውን እስራኤላዊያንን ሀገር አልባ ባላደረጋቸው ነበር:: መቅደሷ በእሳት እንዲጋይ ባልፈቀደ ነበር::
እግዜር የስነምግባር እጦትና የስንፍና መደበቂያ አይደለም::
እኛ  በአንድ ሰው ፍቅር ወድቀን የምናፈርሳ ሀገር እግዚያር ያኖራታል ማለት ሀገራዊ እብደት ነው::
አማላዩን እና የበግ ለምድ የለበሰን ተኩላ በበጎች ላይ ሾመን ስናበቃና ተኩላዬን አትንኩብኝ የሚል ሀገር ወዳድ ነን የሚሉ አእላፍ ዜጎች አፍርተን የምን እግዜርን ማስቸገር ነው?!
ኦርቶዶክሳዊያን ሆይ! በአዳነች አቤቤ ላይ ብስጭትህን ማጉረፍ ተውና ከሀዲ ሙአዘ ጥበባትን አስወግድ:: እንኳን ሊሞት ይቅርና ሆድ አምላኩ ምቾት ብርቁ ከሆኑ ፓፓሳት ፅዳ:: ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ለአብይ አህመድ ከሚዘምሩ ቀሳውስት ፅዳ:: ቤትህን አፅዳ:: ፍርድ ከቤትህ ጀምር::
ከዛ በኃላ እነ አዳነች አቤቤንና አብይ አህመዶች ለመቋቋም አቅም ይኖርሀል:: በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛ majority ሆነህ አንጋሽ መሆን ስትችል ሁሌ  አልቃሽ መሆን አይመጥንህም:: መፍትሄም አይሆንህም::
ማስለቀስ ስትችል የምን ማልቀስ ነው?! አብይ አህመድ እንደሆነ የፈለገ ያህል ብትሰግድለት ብታጎበድድለት ኦርቶዶክስ አማራና ትግሬ ከሆንክ ልታስደስተው የምትችለው በመጥፋትህና በመጥፋትህ ብቻ ነው:: ወይ ቆመህ እምብኝ በል:: ካልሆነ አርፈህ ጥፋ!!!
Filed in: Amharic