>

"በመንግሥት ላይ አንድ ሺህ አንድ ፖለቲካዊ  ጥያቄዎች አሉን! የኢትዮጵያችን ህልውና ይቀድማል....!!!" (እስክንድር ነጋ በመግለጫው ከተናገራቸው) 

“በመንግሥት ላይ አንድ ሺህ አንድ ፖለቲካዊ  ጥያቄዎች አሉን! የኢትዮጵያችን ህልውና ይቀድማል….!!!”
እስክንድር ነጋ በመግለጫው ከተናገራቸው፦ 

*…. አሁን የፖለቲካ አጀንዳ ይዘን አይደለም የቆምነው። የኢትዮጵያን አንድነት ጉዳይ ነው የያዝነው።  ወደ ግንባር የምንሄደውም ይሄን አጀንዳ ይዘን ነው። በተጨማሪም መስዋዕትነት እየከፈሉ ላሉ ኢትዮጵያውያን እጅ ለመንሳት ነው።
*…. በመንግሥት ላይ አንድ ሺህ አንድ ፖለቲካዊ  ጥያቄዎች አሉን። ኢትዮጵያችንን አስቀድመን እስሱን እንቀጥላለን። ሀገራዊ ፓርቲም እንሆናለን።
*…. የራስን ዕድል በራስ መወሰ፤ መገንጠል” የሚባለው ጉዳይ ተረት ተረት ነው። ሌሎች አገራት ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ያሰፈኑት መገንጠልን በሕግ በመከልከል ነው።
*…. ሕገ መንግሥቱ ሊፈቅድ ይችላል። ነገር ግን ሕዝብ የተሳተፈበት ሕዝባዊ ሕገ መንግሥት ስላልሆነ አንቀበለውም
*     *     *
ከእስር የተፈቱት የባልደራስ አመራሮች አባላት በአፋር እና አማራ ክልል ወደሚገኙት የተወሰኑ ግንባሮች በመሄድ መስዋትነትን ለከፈሉት እና እየከፈሉ ለሚገኙ ምስጋና እንዲያቀርቡ፣ የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ጎብኝተው እንዲያፀኑ የድርጅታችን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስናል።በዚህም መሰረት ከአርብ፣ ጥር 6 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንቅስቃሴ ይጀምራሉ።
የሰሜኑ ጦርነት መነሻው ህውሃት በጀመረው ቅድመ ማጥቃት እንደሆነ ፓርቲያችን ይረዳል። የፌደራል መንግስቱ በርካታ የአፈፃፀም ችግሮች ቢኖሩበትም ያደረገው የመከላከል ጦርነት ፍትሃዊ እንደሆነ እናምናለን። በዚሁ መሰረት ፣ ፓርቲያችን ፖለቲካዊ ድጋፍ ከማድረጉ በተጨማሪ ቦታው ድረስ በመሄድ ቁሳዊ እገዛዎች አድርጓል።
ሆኖም ፣ መንግስት “ምዕራፍ አንድ” ያለውን ዘመቻ የኢትዮጲያን ሉኣላዊነት ሳያረጋግጥ ማቆሙ ትልቅ አደጋ ያዘለ መሆኑን ገምግመናል። ዘምቻውም ያቆመበትን አመንክዬ ከማስረዳት አኳያም ሆነ እርሱን ተከትሎ ከህዝብ በሚነሳው ተጨባጭ ስጋት ዙሪያ በቂ ምላሽ አልሰጠም። መንግስት “ተከድተናል” ለሚለው የኢትዮጲያ ህዝብ እያስየ ያለውን ንቀት መስተካለል ይገባዋል።
የዘመቻ ፍፃሜ የኢትዮጲያን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥለውን የህውሃት ወታደራዊ አቅም በመስበር መቋጨት ይገባል።
የህውሃት የፖለቲካና የጦርነት ዋነኛ ቀያሾች የሆኑ ጉዳያቸው በሕግ ጥላ ስር ሆነው እየተከታተሉ የነበሩ እስረኞችን ሰሞኑን መፍታት መጀምሩ  የሕግ የበላይነት የጣሰ ውሳኔ ሆኖ አግኝተነዋል በኢትዮጲያ አስተማማኝ ሰላም ሊገኝ የሚችለው መንግስት ተጠያቂነት እና ፍትህን ሲያሰፍን ብቻ ነው።
ከዚህ አንፃር ገዥው ፓርቲ በጦርነቱ የተጎዱትን አግልሎ ራሱን ብቸኛ የጉዳዩ ባለቤት አድርጎ ተጠያቂነት ፍትህን ባላሰፈነ ሁኔታ ክስ ለማቋረጥ የሰጠው ውሳኔ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ተቀባይነት የለውም።
የሰሞኑ የብልፅግና ፓርቲ ውሳኔ ውሳኔ ኢትዮጲያዊነትን ጎልቶ የተንፅርባረቀበትን የፀረ-ህውሃት ህዝባዊ አንድነት አቋምን ቀጣይነት የሚያሳጣ እና የኢትዮጲያን ፖለቲካ የሚያወሳስብ ነው። ይህ ህጋዊነትን ያልተላበሰ ውሳኔ አገሪቱን ግልፅ ለሆነ አደጋ አጋልጧል።
ከተቋረጡ ክሶች ጋራ በተያያዘ በሕዝቡ ዘንድ የተነሳው ተቋውሞ፣ ከተጠያቂነት ከፍትህ አኳያ እንጅ፣  ከቂም በቀል እና ከጥላቻ አለመሆኑን ግልፅ ሊሆን ይገባል።
በባልደራስ ላይ ለበቀል የተወሰደው ህገ-ወጥ እርምጃ ተቀልብሶ በእስር ላይ የሚገኙ አምስቱ አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በእስር እንዲለቀቁ በጥብቅ እናሳስባለን።
በአጠቃላይ፣ በሀሰት የተከሰሱት አመራሮቻችንን እና አባሎቻችን በሚመለከት፣ መንግስት ይቅርታ ጠይቋቸው፣ ካሳ ሊከፍላቸው ይገባል በክስ ሂደቱ በተጨባጭ እንደታየው በመንግስት በኩል አንድም ሚዛን የሚደፋ ማስረጃ አልቀረበም። እውነታውን ህዝብ ያውቀዋል።
የምክክር ኮሚሽኑ እና ሂደቱን በተመለከተ መመሟላት ያለባቸው ነጥቦች
1. የኢትዮጲያን አንድነት እና ሉዓላዊነት ማስቀጠል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል
2. በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መቀበል የሚሉት ናቸው። ፖርቲያችን የእስካሁን ጉዞ ገምግሞ ተከታዬችን ምክረ ሃሳቦች ያቀርባል
3. የምክክሩ ባለቤት ህዝብ፣ የፖለቲካ ኃይሎች እና የሲቪክ ተቋማት እንጅ ፣ አንድ ፓርቲ 90% በላይ አብላጫ ወንበር የያዘበት ፓርላማ ስላልሆነ ሂደቱን ሁሉም ባለድርሻዎች በባለቤትነት የሚመሩበት ሁኔታ መፍጠር
4. የምክክር ሂደት ግልፅ ተዓማኒ እና ከገዥዎች ፓርቲ ተፅእኖ ነፃ እንዲሂን ማድረግ
5. የምክክር ሂደቱን ግልፀኝነት ለመፍጠር የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በታዛቢነት እንዲጋበዙ የሚሉት ናቸው።
በመጨረሻም ድርጅታችን ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የገዥው ፓርቲ ብትር ሲያርፍበት ቆይቷል። ያለምንም ማጋነን ምንም ፋታ አግኝቶ አያውቅም።ይህም ሆኖ ግን የድርጃታችን አባላት ቁርጠኝነት ከጊዜ እየጨመረ እንጅ እየላላ አልሄድም። በዚህም መሰረት ትግላችንን ከመቼውም በላይ አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን ከአብራኩ ለፈለቅነው ለኢትዮጲያ ህዝብ እናረጋግጣል።
Filed in: Amharic