ፓስተር ቢኒያም ታሰሩ…!!!
ዮሴፍ ይጥና
*…. በሃይማኖት ሽፋን ቅጥ ያጣው የተረኝነት አባዜ በየቀኑ ነውር እየፈለፈለ ቀጥሏል ። ደመነፍሳዊው መንጋ በዚህ የእውር ድምብር አካሄድም የጌታን ስም እየጠራ ደስታውን ሲገልፅ ማየት ያሸማቅቃል ። ይህ የለየለት ኤልዛቤላዊ ብልግና አክዓባዊ ድንቁርና ነው !!!
ለእነርሱ ያላጨበጨበ ፣ ለእነርሱ ያላሸረገደ ፣ እንደ እነርሱ ግጭት ያልቀሰቀሰ ፣ እንደ እነርሱ በስሜት ዳንኪራ ያልረገጠ ፣ እንደ እነርሱ በተረኝነት ያላበደ ፣ እውነትን የሚናገር ፣ ከተበደሉት ጎን የሚቆም ፣ በማስረጃ የሚሞግት ይታሰራል !!!
በሃይማኖት ሽፋን ቅጥ ያጣው የተረኝነት አባዜ በየቀኑ ነውር እየፈለፈለ ቀጥሏል ። ደመነፍሳዊው መንጋ በዚህ የእውር ድምብር አካሄድም የጌታን ስም እየጠራ ደስታውን ሲገልፅ ማየት ያሸማቅቃል ። ይህ የለየለት ኤልዛቤላዊ ብልግና አክዓባዊ ድንቁርና ነው !!!
ፓስተር ቢኒያም የያዘው እውነት ነው ። እውነት በመናገሩ ሲዝቱበት የነበሩ በርካቶች ናቸው ።እሱም ማንንም ሳይፈራ እውነትን የሙጥኝ አለ ። በተረኝነት የሰከሩር ቅርብ አዳሪዎች ፣ ከትላንት ገዢዎች ያልተማሩት ፣ በሃይማኖት ውስጥ የተሸሸጉ ወንበዴዎች ፣ በጌታ ስም የሚሸቅጡ ጋንግስተሮች ፣ በወንጌል ስም ወንጀል የሚፈበርኩ ጥጋበኞች ፓስተር ቢኒያምን አሳስረውታል ።
ተረኝነት እዚህ ደርሷል ፣ በሃይማኖት ሽፋን የተባባሰው እብደት ፈውስ እርቆት ቀጥሏል ።ሁሉን የሚያውቅ ፣ በሁሉም ላይ የሚፈርድ እግዚአብሔር ደግሞ ከመንበሩ ሆኖ እየተመለከተ ነው !!!
ወየው ለነጋችሁ !!! ይህ ጥጋብ ይበርዳል !!!
በሃይማኖት ስም የሚካሄድ ዘረኝነትና ተረኝነት የተወጋ ይሁን !!! አሜን !!!