>

(መኢአድ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ...!!!

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ …!!!
 
 መኢአድ የሚከተሉትን ጥሪዎች አቅርቧል፡-
1ኛ. መንግስት ህዝብን ከስጋት ዋስትና ከማጣት ስሜት የማስወጣት ተግባሩን በአስቸኳይ እንዲያቆምና ህዝብ በሰላም ተረጋግቶ ኑሮውን እንዲመራ የሚያደርግ መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣
2ኛ. መንግስት ህዝብ አደጋ ሊደርስ እንደሆነ ተረድቶ የሚጠቁመውን ጥቆማ በአስቸኳይ ከጥፋቱ ቀድሞ የሕዝብን እልቂት የሚታደግ ተወርዋሪ ሀገር ወዳድ ኃይል እንዲመድብ፣
3ኛ. መንግስት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ያላቀቀ መሆኑን ተረድቶ በቀጠናው እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ እስከውዲያኛው የሚያስቆም ወታደራዊ የተጠናከረ እርምጃ እንዲወሰድና በቀጠናው ያለውን ህዝባችንን ደህንነት እንዲጠብቅ፣
4ኛ. መንግስት በምዕራብና በመሀል ኢትዮጵያ ያለውን የኦነግ ሸኔን እንቅስቃሴ የሚገታ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣
5ኛ.  መንግስት በጥምር ኃይሉ ላይ የያዘውን አቋም ጦርነቱ ካለማብቃቱ አንፃር በደንብ እንዲያጤነው፣
6ኛ.  መንግስት በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ጣልቃ ገብቶ ተቋማትን ጥያቄ ውስጥ የሚከት አካሄድን አቁሞ የእስረኞችን የመፍታትና የማሰር ጉዳይን ለፍትህ ተቋማቱ እንዲመልስ በአስቸኳይ እንጠይቃለን፡፡
7ኛ.  የብሔራዊ መግባባቱን ጉዳይ ሊመረጥ ላለው ኮሚሽን በገለልተኛነት እንዲተውና ጣልቃ እንዳይገባ እንጠይቃለን፡፡
8ኛ.  ሕዝባችን፡- በጦርነት ምክንያት መንግስት እየፈፀመ ያለው ስህተት እንዳያዘናጋህና ጦርነቱ እንዳላበቃ ተረድተህ ራስህን እና ሀገርህን በንቃት እንድትጠብቅ ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
 “አንዲት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!”
Filed in: Amharic