>

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በጠና ታመው ሆስፒታል ገቡ...!!! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በጠና ታመው ሆስፒታል ገቡ…!!!
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ

 ቅዱስነታቸው ሰሞኑን የተወሰነ የሕመም ምልክት ቢሰማቸውም፣ አሁን ግን ስለባሰባቸው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል። ከቅዱስነታቸው በጠና መታመም ጋር ተያይዞ ከከንቲባ አዳነች ጋር ተይዞ የነበረው ቀጠሮ ተራዝሟል። ከንቲባ አዳነች በቅዱስ ሲኖዶስ ተገኝታ ማብራሪያ ለመስጠት ዝግጁ እንደነበረች ተገልጿል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሕመም ላይ ሆነው የሲኖዶሱን ምልዓተ ጒባኤ ሲመሩ ቢቆዩም ከትናንት ጀምሮ ሕመሙ ስለጠናባቸው ለሕክምና ወደ ሆስፒታል አምርተዋል። የዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባም በዚህ ምክንያት ተቋርጧል።
ቅዱስ አባታችን በሃሌሉያ ሆስፒታል VIP class ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነና ከኦክስጂን ውጪ እያገገሙ መሆኑን ምንተ ንግበር ለማወቅ ችላለች።
አባቶቻችንን በሰላም ያቆይልን።
Filed in: Amharic