>
5:16 pm - Saturday May 24, 8302

ነውረኛው ብልፅግና! እንካ እውነቱን.....!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

ነውረኛው ብልፅግና! እንካ እውነቱን…..!!!

ጌታቸው ሽፈራው

*….. ነውረኞች ሆይ! አማራና አፋር እየተዋጋ  ከስንቅና ወዘተ ውጭ የረባ አስተዋፅኦ ያላደረገ ከተማ ወዘተ ጠቅሳችሁ አመስግናችሁ ምንም አወንታዊ አስተዋፅኦ ያልጠቀሳችሁለት አማራ ክልል ከመቶ ሀምሳ ሽህ በላይ አርሶ አደር አዝምቶ ነው ያተረፋችሁ!
“ዘላቂ ድል ወደ ብልፅግና” በሚል የተዘጋጀው የብልፅግና ሰነድ፣ “የድኅረ ጦርነት መዛነፎችና እርምቶች” የሚል ርዕስ ተሸክሞ፣ ነገር ግን ገና ከመግቢያው ታሪክ የሚያዛንፍ ነውረኛ አቋም ያንፀባረቁበት ሰነድ ላይ ተወያይቷል። ጦርነቱ አላለቀም፣ በማይጠምሪ፣ በራያ አሁንም ንፁሃንን በማንነታቸው እየተጠቁ ነው “ድኀረ ጦርነት” ምናምን የሚለው።
የአማራ ክልልን የድል ሽሚያ  ወዘተ እያለ የሚወቅሰው ሰነድ ገና በመግቢያው የአማራን ተሳትፎ ክዶ ይጀምራል። ሰነዱ ክልሎችንና ከተማ አስተዳደሮችን ሁኔታ ይጠቅሳል። ታዲያ ከትግራይና ከአማራ ክልል ውጭ ያሉትን በጦርነቱ ያላቸውን በጎ አስተዋፅኦ ይዘረዝራል።  መቸም የትግራይ ክልልን አወንታዊ አስተዋፅኦ አለው ሊል አይችልም። የኢትዮጵያን እዳ ተሸክሞ የከረመውን የአማራ ክልልን ግን አወንታዊ አስተዋፅኦውን አንድም አይጠቅስም። በሰነዱ ክልሎችንና ከተማ አስተዳደርን ስም በርዕስ እንዳስቀመጠ ከስራቸው በጎ አስተዋፅኦቸውን ነው የሚዘረዝረው። አማራ ላይ በቀጥታ የሚገባው ወደ ስጋቱ ነው። ነውረኝነት! ክህደት ነው!
በጦርነቱ መሃል መጓተት ለጠላት ስለሚጠቅመው ያሳለፍናቸውና ከጦርነቱ በኋላ እስከምናምኑ የምንናገረው ጉዳይ ሞልቷል። ለጊዜው ግን በዚህ ሰነድ ያሳዩትን ነውረኝነት ብቻ ጠቅሶ ማለፍ በቂ ነው!
ነውረኞቹ ሆይ!
ሕዝብን እያዘናጋችሁ፣ ሰራዊቱ ከተመታ በኋላ የአማራ ሕዝብ ነው የራበውን እያበላ፣ የታመመውን እያሳከመ የተቀበለው!
ነውረኞች ሆይ! አማራና አፋር እየተዋጋ  ከስንቅና ወዘተ ውጭ የረባ አስተዋፅኦ ያላደረገ ከተማ ወዘተ ጠቅሳችሁ አመስግናችሁ ምንም አወንታዊ አስተዋፅኦ ያልጠቀሳችሁለት አማራ ክልል ከመቶ ሀምሳ ሽህ በላይ አርሶ አደር አዝምቶ ነው ያተረፋችሁ!
ስለ ጦርነቱ ስናወራ አማራ ክልልን ብቻ አልነበረም። ዞን ማመስገን ነበረባችሁ! እንንገራችሁ ወይ? እንንገራችሁ! መነገር ይገባችኋል! አንተ ስታንቀላፋ ዞን ነው ሲመራህ የከረመው! ዞን ነው ቀጥ አድርጎ የመራህ! ክልሉን ተወውማ! ዞን ነው ከእንቅልፍህ የቀሰቀሰህ!
ይሰማሃል ዞን ነው ሲመራህ የከረመው‼ በፎቶ ያያያዝኩልህን መረጃዎች አገላብጠህ እያቸው!
1) ክልሉ ብቻ መሰለህ አንተ ነውረኛ ሁላ፣ ዞን ነው ሲመራህ የከረመው። ዞን መርቶሃል።  ደቡብ ጎንደር ዞን አልመራህም? ሰሜን ጎንደር ዞን አልመራህም? ደቡብ ወሎ ዞን አልመራህም? ሰሜን ሸዋ ዞን አልመራህም? ቀጥ አድርጎ ነው እንጅ የመራህ!  የማይፈቀድለትን አዋጅ አውጥቶ ነው የመራህ። የአንተ እንቅልፍ ዞኖቹ አዋጅ እንዲያወጡ አድርጓል። አያይዤልሃለሁማ!
ዞን አዋጅ አያወጣም! ሰሜን ጎንደር ዞን ቃል በቃል የክተት አዋጅ ጥሪ ብሎ አውጆ ነው የመራህ። ዜናውን ወስደህ ዘግበህለታል። አይሆንም አላልክም። እንቅልፍ ላይ ነበርክ። ተቀብለህ ነው የተጠቀምክበት!
ደቡብ ጎንደር ዞን ግን አዋጅ አውጥቶ መርቶሃል። ቀጥ አድርጎ። ጠላት በመንጋ ሲመጣ ደቡብ ጎንደር ዞን “ዘምተህ ከጠላት መሳርያ እንድትታጠቅ አዝዣለሁ” አለ። ይሄ አዋጅ ነው። በፌደራል ሚዲያ ቀጥ ብለህ ነው የዘገብኸው። ስትንቀራፈፍ ዞን ቀድሞህ የዞኑን አዋጅ ይዘህ በዋና ሚዲያህ አስተላልፈሃል።  ደቡብ ወሎ “የክተት ጥሪ” ብሎ አውጂ  ወስደህ ተጠቅመህበታል። ሰሜን ሸዋ  “የክተት አዋጅ” ብሎ አውጆ  ወስደህ ተጠቅመህበታል። አልተቃወምከውም፣ አላቅማማህም። ወስደህ ተግብረሃል! እና ዞን አልመራህም? ቀጥ አድርጎ ነው የመራህ። ሰሜን ጎንደር ከእንቅልህ አልቀሰቀሰህም? ደቡብ ጎንደር አልመራህም? ደቡብ ወሎ አላነቃህም? ሰሜን ሸዋ አላታገለህም? ኧረ ነውርህኮ!
አማራ ክልል ቀጥ አድርጎ መርቶሃል!
ክላሽ አትግዙ ወዘተ እያልክ ሕዝብ ስታደነዝዝ ጦርነቱ ወደየት እንደሚያመራ እንኳን አላወክም። ምሁራኑ፣ አብን፣ ፋኖ ጦርነቱ ሕዝባዊ ነው ሲል አንተ ፀጥ ረጭ ብለህ ነበር። እንዲያውም ጦርነት አያስልግም እያልክ እያዘናጋህ ነበር።  የአማራው ኃይል ጦርነቱ ሕዝባዊ ሆኗል ብሎ ደጋግሞ ተናገረ። ክልሉ ያዘው።
ስማ! ስማ!
ክልል አዋጅ አያወጣም አይደል? አዎ አያወጣም! አንተ ስታንቀላፋ ግን ክልሉ አዋጅ አወጣ! ጥቅምት 21/2014 ዓ/ም “የአስቸኳይ ጊዜ ጥሪ” ብሎ በምክር ቤት  አዋጅ አወጣ። “አዋጅ” የሚለውን ብቻ ነው “ጥሪ” በሚል የቀረየው። አንተ ምን አደረክ? ታውቀዋለህ። ጠቅልለህ ወስደህ አዋህ አወጣህ። ጥቅምት 23/2014 ዓ/ም። መረጃዎቹ ተያይዘውልሃል።
የአማራ ክልልን አዋጅ ወስደህ፣ ቃል በቃል ተጠቀምክበት። አማራ ክልል የትግሬ ወራሪ ጦርነቱን ሕዝባዊ ስላደረገውና በመደበኛ የፀጥታ ኃይል ማሸነፍ ስላልተቻለ በሕዝባዊ ንቅናቄ እገታዋለሁ አለ። አንተ ጥቅምት 23 የአማራ ክልልን አዋጅ ቃል በቃል ወስደህ የአማራ ክልል ያለውን ቃል በቃል ወስደህ “በመደበኛው አደረጃጀት ማሸነፍ አይቻልም” ብለህ አፀደቅክ። አንተ ስታንቀላፋ ሲቀሰቅስህ የከረመውን ሕዝብና ክልል በጦርነቱ አወንታዊ አስተዋፅኦውን እንኳን መናገር አልፈለክም።
በመደበኛ አደረጃጀት ማሸነፍ አይቻልም በተባለው መሰረት አማራ ክልል 150 ሺህ አርሶ አደር አሰለፈ።   አርሶ አደሩ የጦርነቱን ማርሽ ቀየረው። የነበርክበትን መለስ ብለህ እንድታይ ዜናዎቹን አያይዤልሃለሁ። ነውረኛ!
ሰሜን ጎንደር ሀምሌ መጀመርያ አዋጅ አውጆ መርቶሃል! አንተ እያንቀላፋህ ነበር።
ደቡብ ጎንደር ነሃሴ መጀመርያ አዋጅ አውጥቶ መርቶሃል።  አንተ እያንቀላፋህ ነበር!
ደቡብ ወሎ ጥቅምት ወር መጀመርያ አዋጅ አውጥቶ መርቶሃል። ስንዴ እየጎበኘህ ነበር!
ሰሜን ሸዋ ጥቅምት ወር መጀመርያ አዋጅ አውጥቶ መርቶሃል። ክላሽ አትግዙ እያልክ ነበር!
አማራ ክልል ጥቅምት 21/2014 ዓ/ም በምክር ቤት አዋጅ አውጥቶ መርቶሃል! ግራ ተጋብተህ ነበር!
ከዚህ ሁሉ በኋላ ጥቅምት 23/2014 ዓ/ም የግድህን፣ ክልሉ አዋጅ አውጥቶ ዝም ማለት ስለማትችል በሀፍረት ገብተህበታል!
እውነታው በአዋጅ የተቀመጠ ነው! በአዋጅ ያስቀመጥከውን፣ በስልጠና ሰነድ አትሽረውም!
ብልፅግና በስልጠና ሰነዱ የአማራ ክልልን አስተዋፅኦ ዘልሎታል። እንዲያውም በቀል ሊፈፅሙ ነው ሲል ለትግሬ ወራሪ የሚጠቅም ነውረኛ ፍረጃ አምጥቷል።
መደበኛ አደረጃጀት እያለ ይወቅሳል። ግን ይሄ  ሁሉ ነውሩ በአዋጅ ተደንግጎ ተቀምጧል። የአማራ ክልል ጥቅምት 21/2014 ዓ/ም ባወጣው አዋጅ በመደበኛው አደረጃጀት ማሸነፍ  እንደማይቻል ጠቅሶ አዋጅ አውጥቷል። የፈደራል መንግስቱም ጥቅምት 23/2014 ዓ/ም ባወጣው አዋጁ በመደበኛ አደረጃጀት ማሸነፍ እንደማይቻል ጠቅሶ አዋጅ አውጥቷል። የሁለቱም አዋጆች መረጃ ተያይዟል።
በመደበኛ አደረጃጀት ማሸነፍ አይቻልም ሲባል ኢመደበኛ በመሆነ መንገድ ፋኖም ሆነ አርሶ አደር ያሰለፈው አማራ ክልል ብቻ ነው። ሌላ ኢመደበኛ አደረጃጀት ያሰለፈ የለም። በመደበኛ አደረጃጀት ማሸነፍ አይቻልምና አግዙን ሲባል የዘመተው የአማራ ፋኖ እና የአማራ አርሶ አደር ነው። ሌላ አንድ የዘመተ፣ አገር ያዳነ ኢ መደበኛ አደረጃጀት የለም።
ይሄ እውነት በአዋጅ የተቀመጠ ነው። በአዋጅ ያፀደከውን በስልጠና ሰነድ ልትክደው አትችልም።
Filed in: Amharic