>

ተማጽኖ ለሽመልስ አብዲሳና "ለኦህዴድ ብልጽግና...!!!" ኤርሚያስ ለገሰ

ተማጽኖ ለሽመልስ አብዲሳና “ለኦህዴድ ብልጽግና…!!!

ኤርሚያስ ለገሰ

የተገለጸው የምርት ውጤት ከነጭ ፕሮፐጋንዳ ያለፈና የሚቆጠር ከሆነ በጣም ደስ ይላል። በተለይም በኢትዮጵያ (ኦሮሚያ) የሚመረተው ምርት ወደ አገር ውስጥ በዶላር ተገዝቶ የሚገባውን ስንዴ አስቀርቶ ምርቱ በመላው ኢትዮጵያ በትራንስፓርት የዋጋ ልዩነት የሚሰራጭ ከሆነ ተስፋ ሰጪ ነው።
እናም የወቅቱ የኢትዮጵያ ገዥ መደብ ለሆነው “የኦህዴድ ብልጽግና” እና ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የማቀርበው ተማጽኖ የሚከተለውን ነው፣
፩ኛ፡ “እናንተ ተዋጉ ፣ እኛ አምርተን እንመግባችኃለን” ባላችሁት መሰረት በጦርነት ለተጎዱ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሚኖሩ ዜጎቻችን በአስቸኳይ ድረሱላቸው።
፪ኛ፡ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ምክንያት በሞት አፋፍ ላይ ለሚገኙት የሶማሌ ክልል፣ የጉጂና ቦረና ነዋሪዎች በአስቸኳይ ድረሱላቸው።
፫ኛ፡ በከተማ ረሃብ ለሚሰቃየው ከተሜ በአስቸኳይ ድረሱለት። በተጨባጭም የኑሮ ውድነቱና የዋጋ ግሽበቱ እንዲቀንስ እድርጋችሁ አሳዩን።
፬ኛ፡ እናንተ ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ መብረቃዊ እምርታ ያመጣችሁበትን ተሞክሮ (የአመራር ስርአት፣ የሕዝብ ተሳትፎ፣ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የዴሞክራሲና የፍትህ ስርዓት፣ ለሰላም የሰጣችሁት ዋጋ፣ የአገር ባለቤትነት ስሜት…ወዘተ) በሰነድ ሰንዳችሁ ለሁሉም ክልል አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት ስልጠና ስጡበት። የገለጻችሁት መሬት የወረደ እውነት መሆኑን ለማሳየት ፍላጎት ላላቸው አካላትና ምርምር ለሚሰሩ ተቋማት ያልተገደበ የመስክ ጉብኝት ፍቀዱ።
Filed in: Amharic