>
5:13 pm - Friday April 20, 2029

የሆሣዕናው ጉዳይ ፋይሉ ተዘጋ፤ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታውንም ተረክበዋል....!!! ዘመድኩን በቀለ

የሆሣዕናው ጉዳይ ፋይሉ ተዘጋ፤ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታውንም ተረክበዋል….!!!
ዘመድኩን በቀለ

 

“መነኩሴው” ሊያገቡ  መሆኑም ተነገረ 
“…የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብርሃም መጫ በጋራ በመሆን ለረጅም ዓመታት ተወርሶ የነበረው የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች የጥምቀትና የደመራ በዓል መክበሪያ ቦታን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራአስኪያጅ ለመላክ ህይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል።
“…የከተማው የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እንደዘገበው ከሆነ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶና የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብርሃም መጫ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በጉልበት የተቀሙትን የራሳቸውን ቦታ በሕጋዊና በሰለማዊ መንገድ ብቻ ለማስመለስ የሄዱበትን መንገድ አድንቀው ያቀረቡትንም የበዓል ማክበሪያ ቦታ ጥያቄ እስኪመለስላቸው ያሳዩትን ትዕግሥት አድንቀው በማመስገን ጭምር ለመላው የሃይማኖቱ ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።
“…የሀዲያና የስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መላአከ ህይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀም በበኩላቸው የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች የረጅም ጊዜ የበዓል ማክበሪያ ቦታ ጥያቄ ምላሸ በማግኘቱ መደሰታቸውን በመግለፅ የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የዘንድሮው በዓል ቀደም ሲል ከጥንት ጀምሮ ይከበርበት ከነበረው የገበያ አካባቢ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ለማክበር ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
“… ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን። ምስጋና ከረፈደም ቢሆን ልባቸው ለዝቦ ፍትሕንና ርትዕን ለቤተ ክርስቲያን ለፈረዱ ለክልሉ መንግሥት ሹመኞች። ምስጋና ቅን ለሆኑ የፕሮቴስታንት ባለሥልጣናት በሙሉ። ምስጋና ለኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ጉባኤ እና ለቀሲስ ታጋይ፣ ምስጋና በዚህ ረጅም ዘመን ሁሉ የማይሰለች፣ የማያቋርጥ ተጋድሎ ሲያደርጉ ለከረሙ ቁርጥ የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ። ምስጋና ለእነ ወንድዬ፣ ምስጋና ለሃገረ ስብከቱ አስተዳደር በሙሉ። ምስጋና ለሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ምስጋና ለማኅበረ ቅዱሳን አባላት፣ ምስጋና ለፅዋ ማኅበራት በሙሉ ይደረሳቸው።
•… ለዚህ ጉዳይ የደከማችሁ ከፍተኛ ማዕረግ ላላቸው የሀዲያ የባህል ሽማግሌዎች በሙሉ።
• ለአዲለላዎች
• ለደዳቾች
• ለአባገዳዎች
• ለገራዶች
• ለአበጋዞች
• ለአስማቼ
• ለዳኛዎች ይድረሳቸው።
“…ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሃገር ውስጥ የሉም። ደቡብ አፍሪካ ናቸው። እዚህ ደስታ መሃል ቢገኙ መልካም ነበረ። ሆሣዕና ዛሬ እንኳ ሊቀጳጳሱን ትፈልጋለች።
“…ይሄን የመሰለ ጣፋጭ ድል የተገኘውም በዋዛ አይደለም። እስከ ዛሬም ድረስ ከፕሮዎቹ ጋር በማበር ቤተ ክርስቲያኒቱን ከውስጥ ሆኖ ሲቦረቡራት የከረመውና “አባ” ብንያም ተብሎ ይጠራ የነበረው መሰሪ የሃገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መነኩሴ ከተባረረ በኋላ የተገኘ ድል መሆኑም ይሰመርበት። “መሰሪው መነኩሴ” ይኸው መርዙ ከከተፋ፣ እሾህነቱ ከተነቀለ በኋላ በሚቀጥሉት ሳምንታት ቆቡን አውልቆ ድል ባለ ሠርግ በዚያው በሆሣዕና ከተማ ሊያገባ መሆኑን ቀደም ብለን ተናግረን የሚሰማን ስላጣን እንጂ እኛ አልተገረም።
“…የደቡብ መንግሥት በነካ እጁ በመሎኮዛ ከለላሃ ቅዱስ ሚካኤል ምእመናንም ላይ የወረሰባቸውን የጥምቀትና የመስቀል ደመራ ማክበሪያ ቦታቸውን በመመለስ እምባቸውን ያብስላቸው ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።
“…በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።” ምሳ 27፥18።
• ሆሣዕናዎች እንኳን ደስ አላችሁ።
Filed in: Amharic